ትንቢተ ኢሳይያስ 48

AMHNIVአማርኛ22 ጥቅሶች4:12 አዳምጥ
አዳምጥ 4:12 · መደበኛ · አስደናቂ በBiblight ይክፈቱ

1“የያዕቆብ ቤት ሆይ፤ እናንት በእስራኤል ስም የተጠራችሁ፣ ከይሁዳ ዘር የተገኛችሁ፣ እናንት በእግዚአብሔር ስም የምትምሉ፣ በእውነት ወይም በጽድቅ ሳይሆን፣ የእስራኤልን አምላክ የምትጠሩ ይህን ስሙ!

2እናንት የቅድስቲቱ ከተማ ነዋሪዎች ነን ብላችሁ ራሳችሁን የምትጠሩ፣ በእስራኤል አምላክ የምትታመኑ፣ ስሙ የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር የሆነው የሚለውን አድምጡ፤

3የቀደሙትን ነገሮች ከብዙ ዘመን በፊት ተናግሬአለሁ፤ ከአፌ ወጥተዋል፤ እንዲታወቁም አድርጌአለሁ፤ እኔም ድንገት ሠራሁ እነርሱም፤ ተፈጸሙ።

4የቱን ያህል እልኸኛ እንደ ነበርህ ዐውቃለሁና፤ የዐንገትህ ጅማት ብረት፣ ግንባርህም ናስ ነበር።

5ስለዚህ እነዚህን ነገሮች ገና ድሮ ነገርሁህ፤ ከመፈጸማቸው በፊት አስታወቅሁህ፤ ይህም፣ ‘ጣዖቶቼ ይህን አደረጉ፤ ከዕንጨት የተቀረጸው ምስልና ከብረት የተሠራው አምላኬ ይህን ወስኖአል’ እንዳትል ነው።

6እነዚህን ነገሮች ሰምተሃል፤ ሁሉንም ተመልከታቸው፤ ራስህ ትክክለኛነታቸውን አትመሰክርምን? “ከአሁን ጀምሮ አዳዲስ ነገሮችን፣ የተሰወሩብህን ያላወቅሃቸውን ነገሮች እነግርሃለሁ።

7እነርሱም የተፈጠሩት አሁን እንጂ ጥንት አይደለም፤ ስለ እነርሱም ከዛሬ በፊት አልሰማህም። ስለዚህ፣ ‘አዎን፤ ስለ እነርሱ ዐውቃለሁ’ ማለት አትችልም።

8አልሰማህም ወይም አላውቅህም፤ ጆሮህ ከጥንት የተከፈተ አልነበረም፤ አንተ አታላይ እንደ ነበርህ፣ ከልጅነትህ ጀምሮ ዐመፀኛ መባልህን ዐውቄአለሁና።

9ስለ ስሜ ስል ቍጣዬን አዘገያለሁ፤ ስለ ምስጋናዬም ስል ከአንተ እገታዋለሁ፤ ይኸውም እንዳልቈርጥህ ነው።

10እነሆ፤ እንደ ብር ባይሆንም አንጥሬሃለሁ፤ በመከራ እቶን ፈትኜሃለሁ።

11ስለ ራሴ፣ ስለ ራሴ ስል አደርጋለሁ፤ ራሴን ለውርደት እንዴት አሳልፌ እሰጣለሁ? ክብሬን ለማንም አልሰጥም።

12“ያዕቆብ ሆይ፤ የጠራሁህ እስራኤል ሆይ፤ ስማኝ፤ እኔ እኔው ነኝ፤ ፊተኛው እኔ ነኝ፤ ኋለኛውም እኔ ነኝ።

13ምድርን የመሠረተች የእኔው እጅ ናት፤ ሰማያትን የዘረጋችም ቀኝ እጄ ናት፤ በምጠራቸው ጊዜ፣ ሁሉም በአንድነት ይቆማሉ።

14“ሁላችሁም በአንድነት ተሰብሰቡ፤ አድምጡም፤ ከጣዖቶች አስቀድሞ እነዚህን የተናገረ ማን ነው? የእግዚአብሔር ምርጥ ወዳጅ የሆነ፣ እርሱ በባቢሎን ላይ ያቀደውን እንዲፈጽም ያደርገዋል፤ ክንዱም በባቢሎናውያን ላይ ይሆናል።

15እኔ፣ እኔው ራሴ ተናግሬአለሁ፤ በርግጥ እኔ ጠርቼዋለሁ፤ አመጣዋለሁ፤ ሥራውም ይከናወንለታል።

16“ወደ እኔ ቅረቡ፤ ይህን ስሙ፤ “ከመጀመሪያ ጀምሮ በስውር አልተናገርሁም፤ ሲፈጸምም እኔ እዚያው ነበርሁ።” አሁንም ጌታ እግዚአብሔርና መንፈሱ ልከውኛል።

17የተቤዠህ፣ የእስራኤል ቅዱስ፣ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ “እኔ እግዚአብሔር አምላክህ፣ የሚበጅህ ምን እንደሆነ የማስተምርህ፣ መሄድ በሚገባህ መንገድ የምመራህ ነኝ።

18ትእዛዜን ሰምተህ ብቻ ቢሆን ኖሮ፣ ሰላምህ እንደ ወንዝ፣ ጽድቅህም እንደ ባሕር ሞገድ በሆነ ነበር።

19ዘርህ እንደ አሸዋ፣ ልጆችህ ስፍር እንደሌለው ትቢያ በሆኑ ነበር፤ ስማቸው አይወገድም፤ ከፊቴም አይጠፋም።

20ከባቢሎን ውጡ፣ ከባቢሎናውያንም ሽሹ! ይህን በእልልታ አስታውቁ፤ ዐውጁት፤ እስከ ምድር ዳርቻ ድረስ ተናገሩ፤ “እግዚአብሔር ባሪያውን ያዕቆብን ተቤዥቶታል” በሉ።

21በምድረ በዳ ሲመራቸው አልተጠሙም ነበር፤ ውሃ ከዐለት አፈለቀላቸው፤ ዐለቱን ሰነጠቀ፤ ውሃውም በኀይል ፈልቆ ወጣ።

22“ለክፉዎች ሰላም የላቸውም” ይላል እግዚአብሔር።

ማብራሪያ

48:1-8 አይሁድ ከያዕቆብ ዝርያ በመሆናቸው ይኩራሩ ነበር፤ እንዲሁም የእግዚአብሔርን ስም እንደ አምላካቸው ይጠቀሙ ነበር። በኢየሩሳሌም እና በቤተ መቅደሱ ይኮሩ ነበር፤ ሆኖም በሕይወታቸው ውስጥ ቅድስና አልነበረም። በሃይማኖት ቅን ካልሆንን፣ የእግዚአብሔርን ስም በከንቱ እንጠራለን። ከመፈጸሙ ከረጅም ጊዜ በፊት እግዚአብሔር እንዴት እንደሚይዛቸው በትንቢት ተገልጾላቸው ነበር። ሰዎች በራሳቸው እንዳይመኩ ለመገሰጽ እግዚአብሔር በቂ የሆነውን ተናግሮአል እንዲሁም አድርጎአል፤ ይህ ደግሞ የኩሩዎችን ኃጢአትና ጥፋት የከፋ ያደርገዋል። ኋላም ሁሉም አፍ ይዘጋል፣ ሁሉም ከእርሱ ፊት ዝም ይላል። ሁላችንም የተወለድነው የዐመፅ ልጆች ሆነን ነው። የዘር ኃጢአት ባለበት ቦታ ሁሉ፣ የግብር ኃጢአት ይከተላል። የእያንዳንዱ ሰው ሕሊና ለመጽሐፍ ቅዱስ እውነት አይመሰክርምን? ጌታ ይመርምረን፣ የቃሉም ፈጻሚዎች ያድርገን።

48:9-15 እኛ እግዚአብሔር ለምን ምሕረትን እንዲያደርግልን የምንማፀንበት በራሳችን ምንም ነገር የለንም። እርሱ የሚምረውና የሚታገሠው ለራሱ ምስጋና፣ ለምሕረቱ ክብርም ሲል ነው። ሰዎችን በችግር ውስጥ እንዲያልፉ የሚያደርጋቸው ለበጎነታቸው ሲል ነበር። ሊያነጻቸው ነበር፣ ነገር ግን ሰዎች ብርን ሙሉ በሙሉ እንደሚያነጹት አይደለም። እግዚአብሔር ያን እርምጃ ቢወስድ ኖሮ፣ ሁሉም ዝገት ናቸውና በጽድቅ ሊወገዱ ይችሉ ነበር።

ሙሉ ማብራሪያውን ያንብቡ ድምፅ፣ ሙሉ ማብራሪያ እና ከመስመር ውጭ ንባብ

ትርጉሞች8 · 6

AMHEVG እናንተ በእስራኤል ስም የተጠራችሁ ከይሁዳም ውኆች የወጣችሁ፥ በእግዚአብሔር ስም የምትምሉ፥ በእውነት ሳይሆን በጽድቅም ሳይሆን የእስራኤልን አምላክ የምትጠሩ፥ አማርኛ ENGNIV “Listen to this, O house of Jacob, you who are called by the name of Israel and come from the line of Judah, you who ta… English BCV ኣቱም ብስም እስራኤል እትፅውዑ፥ ካብ ዓይኒ ማይ ይሁዳ ዝፈልፈልኩም፥ ብስም እግዚኣብሄር እትምሕሉ፥ ብሓቅን ብፅድቅን ደኣ ኣይኮነን እምበር፥ ንኣምላኽ እስራኤል እትፅውዑ፥ እዙይ ስምዑ። ትግርኛ GAZBIB Yaa ijoollee Yaaqoob warri Israa'el jedhamtan, warri gosa Yihudaa keessaa dhalattan, isin warri maqaa Waaqayyootiin kak… Afaan Oromoo BCV GIZ ስምዑ ዘንተ ቤተ ያዕቆብ እለ ተሰመይክሙ በስመ እስራኤል፤ ወእለ ወጽእክሙ እምይሁዳ፤ ወእለ ትምሕሉ በስመ እግዚአብሔር አምላከ እስራኤል፤ ወተዘከርኩክሙ አኮ በጽድቅ ወአኮ በርትዕ። giz GAZGAZ Yaa ijoollee Yaaqoob warri Israa'el jedhamtan, warri gosa Yihudaa keessaa dhalattan, isin warri maqaa Waaqayyootiin kak… Afaan Oromoo BCV aksum ኣቱም ብስም እስራኤል እትፅውዑ፥ ካብ ዓይኒ ማይ ይሁዳ ዝፈልፈልኩም፥ ብስም እግዚኣብሄር እትምሕሉ፥ ብሓቅን ብፅድቅን ደኣ ኣይኮነን እምበር፥ ንኣምላኽ እስራኤል እትፅውዑ፥ እዙይ ስምዑ። ትግርኛ SWAHSUV Sikieni haya, enyi watu wa nyumba ya Yakobo, mnaoitwa kwa jina la Israeli, mliotoka katika maji ya Yuda; mnaoapa kwa ji… Kiswahili