ትንቢተ ኢሳይያስ 47

AMHNIVአማርኛ15 ጥቅሶች3:10 አዳምጥ
አዳምጥ 3:10 · መደበኛ · አስደናቂ በBiblight ይክፈቱ

1“አንቺ የባቢሎን ድንግል ልጅ ሆይ፤ ውረጂ፤ በትቢያ ላይ ተቀመጪ፤ አንቺ የባቢሎናውያን ልጅ ሆይ፤ ከዙፋንሽ ውረጂ፤ መሬት ላይ ተቀመጪ፤ ከእንግዲህ ውብ ወይም ለግላጋ፣ ተብለሽ አትጠሪም።

2ወፍጮ ወስደሽ እህል ፍጪ፤ መሸፋፈኛሽን አውልቂ፤ ቀሚስሽንም ከፍ ከፍ አድርጊ፤ ባትሽን ግለጪ፤ እየተንገዳገድሽ ወንዙን ተሻገሪ።

3ዕርቃንሽ ይገለጥ፤ ኀፍረትሽ ይታይ፤ እበቀላለሁ፤ እኔ ማንንም አልተውም።

4የሚቤዠን የእስራኤል ቅዱስ፣ ስሙ የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር ነው።

5“አንቺ የባቢሎናውያን ልጅ ሆይ፤ ወደ ጨለማ ግቢ፤ ዝም ብለሽም ተቀመጪ፤ ከእንግዲህ የመንግሥታት እመቤት፣ ተብለሽ አትጠሪም።

6ሕዝቤን ተቈጥቼ ነበር፤ ርስቴን አርክሼው ነበር፤ አሳልፌ በእጅሽ ሰጠኋቸው፤ አንቺ ግን አልራራሽላቸውም፤ በዕድሜ በገፉት ላይ እንኳ፣ እጅግ ከባድ ቀንበር ጫንሽባቸው።

7አንቺም፣ ‘እስከ መጨረሻው፣ ለዘላለም ንግሥት እሆናለሁ!’ አልሽ፤ ሆኖም እነዚህን ነገሮች አላስተዋልሽም፤ ፍጻሜያቸው ምን እንደሚሆንም አላሰብሽም።

8“አሁንም አንቺ ቅምጥል ፍጡር፣ በራስሽ ተማምነሽ የምትቀመጪ፣ በልብሽም፣ ‘እኔ ነኝ፣ ከእኔ በቀር ሌላ የለም፤ ከእንግዲህ መበለት አልሆንም፤ የወላድ መካንም አልሆንም’ የምትይ ስሚ!

9እነዚህ ሁለት ነገሮች፣ መበለትነትና የወላድ መካንነት፣ አንድ ቀን ድንገት ይመጡብሻል፤ የቱን ያህል አስማት፣ የቱንም ያህል መተት ቢኖርሽ፣ በሙሉ ኀይላቸው ይመጡብሻል።

10በክፋትሽ ተማምነሽ፣ ‘ማንም አያየኝም’ አልሽ፤ ደግሞም፣ ‘እኔ ነኝ፣ ከእኔ በቀር ሌላ የለም’ ባልሽ ጊዜ፣ ጥበብሽና ዕውቀትሽ አሳሳቱሽ።

11ጥፋት ይመጣብሻል፤ ነገር ግን በአስማትሽ እንዴት እንደምታርቂው አታውቂም፤ ወጆ ከፍለሽ ለማስወገድ የማትችዪው፣ ጒዳት ይወድቅብሻል፤ ያላሰብሽው አደጋ፣ ድንገት ይደርስብሻል።

12በይ እንግዲህ፣ “ከልጅነትሽ ጀምሮ የደከምሽባቸውን፣ አስማቶችሽን፣ ብዙ መተቶችን ቀጥዪባቸው፤ ምናልባት ይሳካልሽ፤ ምናልባትም ጠላቶችሽን ታሸብሪባቸው ይሆናል።

13የተቀበልሽው ምክር ሁሉ ድካም ብቻ ሆኖ አስቀርቶሻል፤ እነዚያ ከወር እስከ ወር ከዋክብትን አንጋጦ በማየት የሚተነብዩ፣ ኮከብ ቈጣሪዎች እስቲ ይምጡ፤ ከሚደርስብሽም ነገር እስቲ ያድኑሽ።

14እነሆ፣ እነርሱ ገለባ ናቸው፤ እሳት ይበላቸዋል፤ ከነበልባሉ ወላፈን የተነሣ፣ ራሳቸውን ማዳን አይችሉም። ሰው የሚሞቀው ፍም አይኖርም፤ ተቀምጠው የሚሞቁትም እሳት የለም።

15ከልጅነት ጀምሮ አብረሻቸው የደከምሽው፣ አብረሽ የተገበያየሻቸው፣ ሊያደርጉ የሚችሉት ይህንኑ ብቻ ነው። እያንዳንዱ በስሕተቱ ይገፋበታል፤ አንቺን ግን የሚያድን የለም።

ማብራሪያ

47:1-6 ባቢሎን በታላቅ ጭንቀት ውስጥ ባለች ሴት ምሳሌነት ተስላለች። እርሷ ትዋረድ ዘንድና መከራን ትቀበል ዘንድ ተወስኖባት ነበር፤ መሬት ላይ ተቀምጣ፣ በወፍጮ የምትፈጭ ሆና ተስላለች፣ ይህም ከሁሉ ዝቅተኛውና እጅግ አድካሚው አገልግሎት ነው። እግዚአብሔር በበቀሉ ጻድቅ ነበርና ማንም ሊጋፋት አይገባም። ነቢዩ የሠራዊት ጌታን፣ የእስራኤልን ቤዛና ቅዱስን በመጥቀስ በደስታ ፈነደቀ። እግዚአብሔር ክፉ ሰዎች በሕዝቡ ላይ እንዲያሸንፉ ብዙ ጊዜ ይፈቅዳል፤ ነገር ግን በጭካኔ የሚያስጨንቋቸው ይቀጣሉ።

ሙሉ ማብራሪያውን ያንብቡ ድምፅ፣ ሙሉ ማብራሪያ እና ከመስመር ውጭ ንባብ

ትርጉሞች8 · 6

AMHEVG አንቺ ድንግል የባቢሎን ልጅ ሆይ፥ ውረጂ በትቢያም ላይ ተቀመጪ፤ የከለዳውያን ሴት ልጅ ሆይ፥ ከዚህ በኋላ ቅልጣናምና ቅምጥል አትባይምና ያለ ዙፋን በመሬት ላይ ተቀመጪ። አማርኛ ENGNIV “Go down, sit in the dust, Virgin Daughter of Babylon; sit on the ground without a throne, Daughter of the Babylonians.… English BCV “ኣቲ ድንግል ጓል ባቢሎን፥ ውረዲ፤ ኣብ ሓመድ ከዓ ተቐመጢ፤ ደጊም ምልክዕትን ሕንቅቕትን፥ ኣይትበሃሊን ኢኽሞ፥ ኣቲ ድንግል ጓል ባቢሎን፥ ብዘይ ዙፋን ኣብ ምድሪ ተቐመጢ። ትግርኛ GAZBIB “Yaa intala Baabilon, yaa ishee takkaa hin tuqamin jirtuu, ka'ii gad bu'ii awwaara keessa taa'i! Yaa intala Kaldootaa, … Afaan Oromoo BCV GIZ ረዲ ወንበሪ ውስተ ምድር አንቲ ድንግል ወለተ ባቢሎን፤ ንበሪ ውስተ መሬት ወአልብኪ መንበረ ወለተ ፋርስ ወኢትሰመዪ እንከ ልሕደ ወሥብሕተ። giz GAZGAZ “Yaa intala Baabilon, yaa ishee takkaa hin tuqamin jirtuu, ka'ii gad bu'ii awwaara keessa taa'i! Yaa intala Kaldootaa, … Afaan Oromoo BCV aksum “ኣቲ ድንግል ጓል ባቢሎን፥ ውረዲ፤ ኣብ ሓመድ ከዓ ተቐመጢ፤ ደጊም ምልክዕትን ሕንቅቕትን፥ ኣይትበሃሊን ኢኽሞ፥ ኣቲ ድንግል ጓል ባቢሎን፥ ብዘይ ዙፋን ኣብ ምድሪ ተቐመጢ። ትግርኛ SWAHSUV Haya, shuka, keti mavumbini, Ewe bikira, binti Babeli; Keti chini pasipo kiti cha enzi, Ewe binti wa Wakaldayo; Maana h… Kiswahili