ትንቢተ ኢሳይያስ 39

AMHNIVአማርኛ8 ጥቅሶች1:58 አዳምጥ
አዳምጥ 1:58 · መደበኛ · አስደናቂ በBiblight ይክፈቱ

1በዚያን ጊዜ የባቢሎን ንጉሥ፣ የባልዳን ልጅ፣ መሮዳክ ባልዳን የሕዝቅያስን መታመምና መፈወስ ሰምቶ ስለ ነበር፣ ደብዳቤና ስጦታ ላከለት።

2ሕዝቅያስም መልእክተኞቹን በደስታ ተቀበለ፤ ለእነርሱም በግምጃ ቤቱ ውስጥ ያለውን ብሩን፣ ወርቁን፣ ቅመማ ቅመሙን፣ ምርጡን ዘይት እንዲሁም የጦር መሣሪያውን በሙሉ፣ ያለውንም ንብረት አንዳች ሳያስቀር አሳያቸው። በቤተ መንግሥቱም ሆነ በግዛቱ ሁሉ ሕዝቅያስ ያላሳያቸው ነገር አልነበረም።

3ከዚያም ነቢዩ ኢሳይያስ ወደ ንጉሡ ሕዝቅያስ መጥቶ፣ “እነዚያ ሰዎች ምን አሉህ? ወደ አንተ ዘንድ የመጡትስ ከየት ነው?” አለው። ሕዝቅያስም፣ “ወደ እኔ የመጡት ከሩቅ አገር፣ ከባቢሎን ነው” አለው።

4ነቢዩም፣ “በቤተ መንግሥትህ ያዩት ምንድን ነው?” አለው። ሕዝቅያስም፣ “በቤተ መንግሥቴ ያለውን ሁሉ አይተዋል፤ ከንብረቴ ያላሳየኋቸው ምንም ነገር የለም” አለ።

5ኢሳይያስም ሕዝቅያስን እንዲህ አለው፤ “የሰራዊት ጌታ የእግዚአብሔርን ቃል ስማ፤

6እነሆ፤ በቤተ መንግሥትህ ያለው ሁሉ፣ አባቶችህ እስከዚህች ቀን ድረስ ያከማቹትም ሁሉ ወደ ባቢሎን ተማርኮ የሚወሰድበት ቀን ይመጣል፤ አንዳች የሚተርፍ ነገር የለም፤ ይላል እግዚአብሔር።

7ከአብራክህ ከሚከፈሉት፣ ከዘርህ፣ ከአንተ ከሚወለዱት ልጆች ተወስደው፣ በባቢሎን ንጉሥ ቤተ መንግሥት ጃንደረባዎች ይሆናሉ።”

8ሕዝቅያስም፣ “የተናገርኸው የእግዚአብሔር ቃል መልካም ነው” አለው፤ “በዘመኔ ሰላምና ጸጥታ ከኖረ ዘንድ” ብሎ ዐስቦ ነበርና።

ትርጉሞች8 · 6

AMHEVG በዚያም ወራት የባቢሎን ንጉሥ የባልዳን ልጅ መሮዳክ ባልዳን ሕዝቅያስ ታምሞ እንደ ተፈወሰ ሰምቶ ነበርና ደብዳቤና እጅ መንሻ ላከለት። አማርኛ ENGNIV At that time Merodach-Baladan son of Baladan king of Babylon sent Hezekiah letters and a gift, because he had heard of … English BCV በታ ጊዜ እቲኣ መሮዳክ፥ ወዲ ባልዳን ንጉስ ባቢሎን፥ ሕዝቅያስ ሓሚሙ ኸም ዝሓወየ ሰሚዑ ነበረ እሞ፥ መልእኽትን ገፅ በረኸትን ሰደደሉ። ትግርኛ GAZBIB Merodaak-Baladaan ilmi Baladaan mootiin Baabilon, Hisqiyaas dhukkubsatee akka fayye yommuu dhaga'e, caaffataa fi kennaa… Afaan Oromoo BCV GIZ ወውእተ አሚረ ለአከ መሮዳክ በልዳንሃ ወልደ በልዳን ንጉሠ ባቢሎን መጻሕፍተ ወተናብልተ ወአምኃ ኀበ ሕዝቂያስ፤ እስመ ሰምዐ ከመ ደወየ ወበጽሐ ለመዊት ወሐይወ። giz GAZGAZ Merodaak-Baladaan ilmi Baladaan mootiin Baabilon, Hisqiyaas dhukkubsatee akka fayye yommuu dhaga'e, caaffataa fi kennaa… Afaan Oromoo BCV aksum በታ ጊዜ እቲኣ መሮዳክ፥ ወዲ ባልዳን ንጉስ ባቢሎን፥ ሕዝቅያስ ሓሚሙ ኸም ዝሓወየ ሰሚዑ ነበረ እሞ፥ መልእኽትን ገፅ በረኸትን ሰደደሉ። ትግርኛ SWAHSUV Wakati huo Merodakibaladani, mwana wa Baladani, mfalme wa Babeli, alipeleka barua na zawadi kwa Hezekia; kwa maana amep… Kiswahili