ትንቢተ ኢሳይያስ 39

AMHEVGአማርኛ8 ጥቅሶች1:29 አዳምጥ
አዳምጥ 1:29 · መደበኛ · አስደናቂ በBiblight ይክፈቱ

1በዚያም ወራት የባቢሎን ንጉሥ የባልዳን ልጅ መሮዳክ ባልዳን ሕዝቅያስ ታምሞ እንደ ተፈወሰ ሰምቶ ነበርና ደብዳቤና እጅ መንሻ ላከለት።

2ሕዝቅያስም ደስ አለው፥ ግምጃ ቤቱንም፥ ብሩንና ወርቁንም፥ ቅመሙንና የከበረውንም ዘይት፥ መሣርያም ያለበትን ቤት ሁሉ፥ በቤተ መዛግብቱም የተገኘውን ሁሉ አሳያቸው፤ በቤቱና በግዛቱ ሁሉ ካለው ሕዝቅያስ ያላሳያቸው የለም።

3ነቢዩም ኢሳይያስ ወደ ንጉሡ ወደ ሕዝቅያስ መጥቶ፦ እነዚህ ሰዎች ምን አሉ? ከወዴትስ መጡልህ? አለው። ሕዝቅያስም፦ ከሩቅ አገር ከባቢሎን መጡልኝ፡ አለው።

4እርሱም፦ በቤትህ ያዩት ምንድር ነው? አለው፤ ሕዝቅያስም፦ በቤቴ ያለውን ሁሉ አይተዋል፤ በቤተ መዛግብቴ ካለው ያላሳየኋቸው የለም፡ አለው።

5ኢሳይያስም ሕዝቅያስን፦ የሠራዊትን ጌታ የእግዚአብሔርን ቃል ስማ።

6እነሆ፥ በቤትህ ያለው ሁሉ፥ አባቶችህም እስከ ዛሬ ድረስ ያከማቹት ሁሉ ወደ ባቢሎን የሚፈልስበት ወራት ይመጣል፤ ምንም አይቀርም፡ ይላል እግዚአብሔር።

7ከአንተም ከሚወጡት ከምትወልዳቸው ልጆችህ ማርከው ይወስዳሉ፤ በባቢሎንም ንጉሥ ቤት ውስጥ ጃንደረቦች ይሆናሉ፡ አለው።

8ሕዝቅያስም ኢሳይያስን፦ የተናገርኸው የእግዚአብሔር ቃል መልካም ነው፡ አለው። ደግሞም፦ በዘመኔ ሰላምና እውነት ይሁን፡ አለ።

ትርጉሞች8 · 6

ENGNIV At that time Merodach-Baladan son of Baladan king of Babylon sent Hezekiah letters and a gift, because he had heard of … English BCV በታ ጊዜ እቲኣ መሮዳክ፥ ወዲ ባልዳን ንጉስ ባቢሎን፥ ሕዝቅያስ ሓሚሙ ኸም ዝሓወየ ሰሚዑ ነበረ እሞ፥ መልእኽትን ገፅ በረኸትን ሰደደሉ። ትግርኛ GAZBIB Merodaak-Baladaan ilmi Baladaan mootiin Baabilon, Hisqiyaas dhukkubsatee akka fayye yommuu dhaga'e, caaffataa fi kennaa… Afaan Oromoo BCV GIZ ወውእተ አሚረ ለአከ መሮዳክ በልዳንሃ ወልደ በልዳን ንጉሠ ባቢሎን መጻሕፍተ ወተናብልተ ወአምኃ ኀበ ሕዝቂያስ፤ እስመ ሰምዐ ከመ ደወየ ወበጽሐ ለመዊት ወሐይወ። giz GAZGAZ Merodaak-Baladaan ilmi Baladaan mootiin Baabilon, Hisqiyaas dhukkubsatee akka fayye yommuu dhaga'e, caaffataa fi kennaa… Afaan Oromoo BCV aksum በታ ጊዜ እቲኣ መሮዳክ፥ ወዲ ባልዳን ንጉስ ባቢሎን፥ ሕዝቅያስ ሓሚሙ ኸም ዝሓወየ ሰሚዑ ነበረ እሞ፥ መልእኽትን ገፅ በረኸትን ሰደደሉ። ትግርኛ AMHNIV በዚያን ጊዜ የባቢሎን ንጉሥ፣ የባልዳን ልጅ፣ መሮዳክ ባልዳን የሕዝቅያስን መታመምና መፈወስ ሰምቶ ስለ ነበር፣ ደብዳቤና ስጦታ ላከለት። አማርኛ SWAHSUV Wakati huo Merodakibaladani, mwana wa Baladani, mfalme wa Babeli, alipeleka barua na zawadi kwa Hezekia; kwa maana amep… Kiswahili