ትንቢተ ኢሳይያስ 35

AMHNIVአማርኛ10 ጥቅሶች2:07 አዳምጥ
አዳምጥ 2:07 · መደበኛ · አስደናቂ በBiblight ይክፈቱ

1ምድረ በዳውና ደረቁ ምድር ደስ ይላቸዋል፤ በረሓው ሐሤት ያደርጋል፤ ይፈካል፤ እንደ አደይም ያብባል።

2በደስታና በዝማሬ ሐሤት ያደርጋል፤ የሊባኖስ ክብር ይሰጠዋል፤ የቀርሜሎስንና የሳሮንን ግርማ ይለብሳል። የአምላካችንን ታላቅ ግርማ፣ የእግዚአብሔርን ክብር ያያሉ።

3የደከሙትን እጆች አበርቱ፤ የላሉትንም ጒልበቶች አጽኑ፤

4የሚፈራ ልብ ላላቸው እንዲህ በሉ፤ “በርቱ፤ አትፍሩ፤ አምላካችሁ ይመጣል፤ ሊበቀል ይመጣል፤ እርሱም ብድራቱን ይዞ፣ ሊያድናችሁ ይመጣል።”

5በዚያን ጊዜም የዕውር ዐይኖች ይገለጣሉ፤ የደንቈሮም ጆሮዎች ይከፈታሉ።

6አንካሳ እንደ ሚዳቋ ይዘላል፤ የድዳውም አንደበት በደስታ ይዘምራል፤ ውሃ ከበረሓ ይወጣል፤ ምንጮችም ከምድረ በዳ ይፈልቃሉ።

7ንዳዳማው ምድር ኵሬ ይሆናል፤ የተጠማው መሬት ውሃ ያመነጫል። ቀበሮዎች በተኙባቸው ጒድጓዶች፣ ሣር፣ ሸምበቆና ደንገል ይበቅልበታል።

8በዚያ አውራ ጐዳና ይሆናል፤ “የተቀደሰ መንገድ” ተብሎ ይጠራል። የረከሱ አይሄዱበትም፤ በመንገዱ ላይ ላሉት ብቻ ይሆናል። ገራገሮችም ከመንገዱ አይስቱም።

9አንበሳ አይኖርበትም፤ ነጣቂ አውሬም አይወጣበትም፤ እነዚህማ በዚያ ስፍራ አይገኙም፤ የዳኑት ብቻ በዚያ ይሄዳሉ፤

10እግዚአብሔር የዋጃቸው ይመለሳሉ። እየዘመሩ ወደ ጽዮን ይገባሉ፤ ዘላለማዊ ደስታን እንደ አክሊል ይቀዳጁታል፤ ፍሥሓና ሐሤት ያገኛሉ፤ ሐዘንና ትካዜ ከዚያ ይሸሻሉ።

ማብራሪያ

35:1-4

በሕዝቅያስ ዘመን ይሁዳ የረድኤት ሀገር ነበረች፣ ነገር ግን ዋነኛው ዓላማ የክርስቶስ መንግሥት ነው። ወደ እግዚአብሔር የመመለሻ ጸጋ ምድረ በዳ የነበረችውን ነፍስ በደስታና በዝማሬ እንድትደሰት፣ እና በብዛት እንድታብብ ታደርጋታለች። ደካሞችና ልበ ደካሞች ይበረታታሉ። ይህም የወንጌል ዓላማ ነው። ፍርሃት የሚያደክም ነውና፤ እሱን በታገልነው ቁጥር፣ ለመሥራትም ለመሰቃየትም ይበልጥ እንበረታለን፤ ‹ብርቱ ሁኑ› የሚለን ደግሞ፣ ረድኤትን በብርቱው ላይ አኖሮልናል። የመሲሑ መምጣት ተረጋግጧል፤ እርሱም በጨለማ ኃይላት ላይ ለመበቀል፣ በጽዮን ለሚያዝኑት በብዙ መጽናናት ለመክፈል ይመጣል፤ እርሱም ይመጣል ያድናል። በዘመኑ መጨረሻ ዳግመኛ ይመጣል፣ ሕዝቡን ያስጨነቁትን ለመቅጣት፤ እንዲሁም ለተጨነቁት ሁሉ፣ ለመከራቸው ሙሉ ዋጋ የሚሆን እረፍትን ለመስጠት።

35:5-10 ክርስቶስ መንግሥቱን በዓለም ሊያቆም በሚመጣበት ጊዜ፣ በሰው ልጆች ነፍሳት ላይ ድንቅ፣ እጅግም ድንቅ የሆኑ ነገሮች ይፈጸማሉ። በክርስቶስ ቃልና መንፈስ፣ በመንፈሳዊ ዕውር የነበሩ ሰዎች አይናቸው በራል፤ ለእግዚአብሔር ጥሪዎች ደንቆሮ የነበሩትም በቀላሉ እንዲሰሙ ተደረጉ።

ሙሉ ማብራሪያውን ያንብቡ ድምፅ፣ ሙሉ ማብራሪያ እና ከመስመር ውጭ ንባብ

ትርጉሞች8 · 6