ትንቢተ ኢሳይያስ 36

AMHEVGአማርኛ22 ጥቅሶች4:18 አዳምጥ
አዳምጥ 4:18 · መደበኛ · አስደናቂ በBiblight ይክፈቱ

1እንዲህም ሆነ፤ በንጉሡ በሕዝቅያስ በአሥራ አራተኛው ዓመት የአሦር ንጉሥ ሰናክሬም ወደ ይሁዳ ወደ ተመሸጉት ከተሞች ሁሉ ወጥቶ ወሰዳቸው።

2የአሦርም ንጉሥ ራፋስቂስን ከብዙ ሠራዊት ጋር ከለኪሶ ወደ ንጉሡ ወደ ሕዝቅያስ ወደ ኢየሩሳሌም ላከ፥ እርሱም በአጣቢው እርሻ መንገድ ባለችው በላይኛይቱ ኵሬ መስኖ አጠገብ ቆመ።

3የቤቱም አዛዥ የኬልቅያስ ልጅ ኤልያቄም ጸሐፊውም ሳምናስ ታሪክ ጸሐፊም የአሳፍ ልጅ ዮአስ ወደ እርሱ ወጡ።

4ራፋስቂስም አላቸው፦ ለሕዝቅያስ እንዲህ ብላችሁ ንገሩት፦ ታላቁ የአሦር ንጉሥ እንዲህ ይላል፦ ይህ የምትታመንበት መተማመኛ ምንድር ነው?

5እኔ፦ ለሰልፍ የሆነው ምክርህና ኃያልህ ከንቱ ነገር ነው፡ አልሁ፤ አሁንም በእኔ ላይ ያመፅኸው በማን ተማምነህ ነው?

6እነሆ፥ በዚህ በተቀጠቀጠ በሸምበቆ በትር በግብፅ ትታመናለህ፤ ሰው ቢመረኰዘው ተሰብሮ በእጁ ይገባል ያቈስለውማል የግብፅ ንጉሥ ፈርዖን ለሚታመኑበት ሁሉ አንዲሁ ነው።

7አንተም፦ በአምላካችን በእግዚአብሔር እንታመናለን፡ ብትለኝ፥ ሕዝቅያስ ይሁዳንና ኢየሩሳሌምን፦ በዚህ መሠዊያ ፊት ስገዱ፡ ብሎ የኮረብታ መስገጃዎቹንና መሠዊያዎቹን ይስፈረሰ ይህ አይደለምን?

8አሁን እንግዲህ ከጌታዬ ከአሦር ንጉሥ ጋር ተወራረድ፥ የሚቀመጡባቸውንም ሰዎች ማግኘት ቢቻልህ እኔ ሁለት ሺህ ፈረሶች እሰጥሃለሁ።

9ስለ ሰረገሎችና ስለ ፈረሶኞች በግብፅ ስትታመን፥ ከጌታዬ ባሪያዎች የሚያንሰውን የአንዱን አለቃ ፊት ትቃወም ዘንድ እንዴት ይቻልሃል?

10አሁንም በውኑ ያለ እግዚአብሔር ትእዛዝ ይህን አገር አጠፋ ዘንድ ወጥቻለሁን? እግዚአብሔር፦ ወደዚህ አገር ወጥተህ አጥፋው፡ አለኝ።

11ኤልያቄምና ሳምናስ ዮአስም ራፋስቂስን፦ እኛ እንሰማለንና እባክህ፥ በሶርያ ቋንቋ ለባሪያዎችህ ተናገር፤ በቅጥርም ላይ ባለው ሕዝብ ጆሮ በአይሁድ ቋንቋ አትናገረን፡ አሉት።

12ራፋስቂስ ግን፦ ጌታዬ ይህን ቃል እናገር ዘንድ ወደ አንተና ወደ ጌታህ ልኮኛልን? ከእናንተ ጋር ኵሳቸውን ይበሉ ዘንድ ሽንታቸውንም ይጠጡ ዘንድ በቅጥር ላይ ወደ ተቀመጡት ሰዎች አይደለምን? አላቸው።

13ራፋስቂስም ቆሞ በታላቅ ድምፅ በአይሁድ ቋንቋ እንዲህ ብሎ ጮኸ፦ የታላቁን የአሦርን ንጉሥ ቃል ስሙ።

14ንጉሡ እንዲህ ይላል፦ ያድናችሁ ዘንድ አይችልምና ሕዝቅያስ አያታልላችሁ፤

15ሕዝቅያስም፦ እግዚአብሔር በእርግጥ ያድነናል ይህችም ከተማ በአሦር ንጉሥ እጅ አትሰጥም፡ ብሎ በእግዚአብሔር እንድትታመኑ አያድርጋችሁ።

16ሕዝቅያስንም አትስሙ፤ የአሦር ንጉሥ እንዲህ ይላል፦ ከእኔ ጋር ታረቁ ወደ እኔም ውጡ፤ እያንዳንዳችሁም ከወይናችሁና ከበለሳችሁ ብሉ፥ ከጕድጓዳችሁም ውኃ ጠጡ፤

17ይህም መጥቼ ምድራችሁን ወደምትመስለው ምድር፥ እህልና የወይን ጠጅ፥ እንጀራና ወይን ወዳለበት ምድር እስካፈልሳችሁ ድረስ ነው።

18ሕዝቅያስም፦ እግዚአብሔር ያድነናል፡ ብሎ እንዳያታልላችሁ ተጠንቀቁ። በውኑ የአሕዛብ አማልክት አገሮቻቸውን ከአሦር ንጉሥ እጅ አድነዋቸዋልን?

19የሐማትና የአርፋድ አማልክት ወዴት አሉ? የሴፈርዋይም አማልክት ወዴት አሉ? ሰማርያን ከእጄ አድነዋታልን?

20እግዚአብሔር ኢየሩሳሌምን ከእጄ ያድን ዘንድ ከእነዚህ አገሮች አማልክት ሁሉ አገሩን ከእጄ ያዳነ ማን ነው?

21እነርሱም ዝም አሉ፥ አንዳችም አልመለሱለትም፤ ንጉሡ አንዳይመልሱለት አዝዞ ነበርና።

22የቤቱ አዛዥ የኬልቅያስ ልጅ ኤልያቄም ጸሐፊውም ሳምናስ ታሪክ ጸሐፊም የአሳፍ ልጅ ዮአስ ልብሳቸውን ቀድደው ወደ ሕዝቅያስ መጡ፥ የራፋስቂስንም ቃል ነገሩት።

ትርጉሞች8 · 6

ENGNIV In the fourteenth year of King Hezekiah's reign, Sennacherib king of Assyria attacked all the fortified cities of Judah… English BCV ከምዙይ ከዓ ኾነ፦ ሕዝቅያስ ምስ ነገሰ፥ ኣብ መበል ዓሰርተ ኣርባዕተ ዓመቱ፥ ሰናክሬም ንጉስ ኣሶር ነተን ዕሩዳት ከተማታት ይሁዳ ዅላተን ደዪቡ ሓዘን። ትግርኛ GAZBIB Bara Hisqiyaas mootichaa waggaa kudha afuraffaa keessa Shenaaheriib mootiin Asor biyya Yihudaatti duulee, mandara biyyi… Afaan Oromoo BCV GIZ አመ ዓሠርቱ ወአርባዕቱ ዓመተ መንግሥቱ ለሕዝቂያስ ዓርገ ሰናክሬም ንጉሠ ፋርስ ላዕለ አህጉረ ይሁዳ እለ ቦን ጥቅመ ወነሥኦን ወአስተጋብኦን። giz GAZGAZ Bara Hisqiyaas mootichaa waggaa kudha afuraffaa keessa Shenaaheriib mootiin Asor biyya Yihudaatti duulee, mandara biyyi… Afaan Oromoo BCV aksum ከምዙይ ከዓ ኾነ፦ ሕዝቅያስ ምስ ነገሰ፥ ኣብ መበል ዓሰርተ ኣርባዕተ ዓመቱ፥ ሰናክሬም ንጉስ ኣሶር ነተን ዕሩዳት ከተማታት ይሁዳ ዅላተን ደዪቡ ሓዘን። ትግርኛ AMHNIV ንጉሥ ሕዝቅያስ በነገሠ በዐሥራ አራተኛው ዓመት፣ የአሦር ንጉሥ ሰናክሬም የተመሸጉትን የይሁዳ ከተሞች ሁሉ አጥቅቶ ያዛቸው። አማርኛ SWAHSUV Ikawa, katika mwaka wa kumi na nne wa kumiliki kwake mfalme Hezekia, Senakeribu, mfalme wa Ashuru, akapanda ili kupigan… Kiswahili