ትንቢተ ኢሳይያስ 33

AMHNIVአማርኛ24 ጥቅሶች4:46 አዳምጥ
አዳምጥ 4:46 · መደበኛ · አስደናቂ በBiblight ይክፈቱ

1አንተ ሳትጠፋ የምታጠፋ፣ አንት አጥፊ፣ ወዮልህ! አንተ ሳትካድ የምትክድ፣ አንት ከዳተኛ፣ ወዮልህ! ማጥፋትን በተውህ ጊዜ፣ ትጠፋለህ፤ ክሕደትህንም በተውህ ጊዜ ትከዳለህ።

2እግዚአብሔር ሆይ፤ ማረን፤ አንተን ተስፋ አድርገናል። በየማለዳው ብርታት፣ በጭንቅ ጊዜም ድነት ሁነን።

3ሕዝቦች በድምፅህ ነጐድጓድ ይሸሻሉ፣ መንግሥታት ስትነሣ ይበተናሉ።

4ሕዝቦች ሆይ፤ አንበጣ እንደሚሰበስብ ብዝበዛችሁም ይሰበሰባል፤ ሰዎችም እንደ ኩብኩባ ይጨፍሩበታል።

5እግዚአብሔር በአርያም ተቀምጦአልና ከፍ ከፍ አለ፤ ጽዮንን በጽድቅና በፍትሕ ይሞላታል።

6እርሱ ለዘመንህ የሚያስተማምን መሠረት፣ የድነት፣ የዕውቀትና የጥበብ መዝገብ ይሆናል፤ እግዚአብሔርንም መፍራት የዚህ ሀብት ቍልፍ ነው።

7እነሆ፤ ጐበዞቻቸው በየመንገዱ ይጮኻሉ፤ የሰላም መልእክተኞችም አምርረው ያለቅሳሉ።

8አውራ ጐዳናዎች ባዶ ናቸው፤ በመንገድ ላይ ሰው የለም፤ ስምምነቱ ፈርሶአል፤ መካሪዎቹ ተንቀዋል፤ የሚከበርም የለም።

9ምድሪቱ አለቀሰች፤ መነመነች፤ ሊባኖስ ዐፈረች፤ ጠወለገች፤ ሳሮን እንደ ዐረባ ምድረ በዳ ሆነች፤ ባሳንና ቀርሜሎስ ቅጠላቸውን አረገፉ።

10እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ “አሁን እነሣለሁ፤ አሁን ከፍ ከፍ እላለሁ፤ አሁን እከብራለሁ።

11ገለባን ፀነሳችሁ፤ እብቅንም ወለዳችሁ፤ እስትንፋሳችሁም የሚበላችሁ እሳት ነው።

12ሕዝቦች ኖራ እንደሚወጣው ድንጋይ ይቃጠላሉ፤ እንደ እሾኽ ቍጥቋጦ በእሳት ይጋያሉ።”

13እናንት በሩቅ ያላችሁ ያደረግሁትን ስሙ፤ እናንት በቅርብ ያላችሁ ኀይሌን ዕወቁ!

14በጽዮን ያሉ ኀጢአተኞች ደነገጡ፤ አምላክ የሌላቸውም ፍርሀት ይዞአቸው፣ “ከእኛ መካከል ከሚባላ እሳት ጋር ማን መኖር ይችላል፣ ከዘላለም እሳትስ ጋር ማን መኖር ይችላል?” አሉ።

15በጽድቅ የሚራመድ፣ ቅን ነገር የሚናገር፣ በሽንገላ የሚገኝ ትርፍ የሚንቅ፣ መማለጃን ላለመቀበል እጁን የሚሰበሰብ፣ የግድያን ሤራ ላለመስማት ጆሮውን የሚደፍን፣ ክፋትን ላለማየት ዐይኑን የሚጨፍን፣

16ይህ ሰው በከፍታ ላይ ይኖራል፤ የተራራም ምሽግ መጠጊያው ይሆናል፤ እንጀራ ይሰጠዋል፣ ውሃውም አይቋረጥበትም።

17ዐይኖችህ ንጉሡን በውበቱ ያዩታል፤ በሩቅ የተዘረጋችውንም ምድር ይመለከታሉ።

18የቀደመው መከራ ትዝ እያለህ፣ “ያ ዋና አለቃ የት አለ? ግብር ተቀባዩስ ወዴት ሄደ? የመጠበቂያ ማማ ኀላፊውስ የት አለ?” ትላለህ።

19እነዚያ ንግግራቸው የማይገባ፣ የሚሉትም የማይታወቅ፣ ሊረዱት የማይቻል ቋንቋ የሚናገሩትን ጋጠወጥ ሕዝብ ከእንግዲህ አታያቸውም።

20በዓላታችንን የምናከብርባትን ከተማ ጽዮንን ተመልከት፤ ሰላማዊ መኖሪያ፣ የማትነቃነቅ ድንኳን የሆነችውን፣ ካስማዋ የማይነቀል፣ ከገመዷ አንዱ እንኳ የማይበጠሰውን፣ ኢየሩሳሌምን ዐይኖችህ ያያሉ።

21እግዚአብሔር በዚያ ኀይላችን ይሆናል፤ ባለ መቅዘፊያ ጀልባዎች እንደማያልፉባቸው፣ ታላላቅ መርከቦችም እንደማይሻገሯቸው፣ ሰፋፊ ወንዞችና ጅረቶች ይሆንልናል።

22እግዚአብሔር ዳኛችን ነው፤ እግዚአብሔር ሕግ ሰጪያችን ነው፤ እግዚአብሔር ንጉሣችን ነው፤ የሚያድነንም እርሱ ነውና።

23መወጠሪያ ገመድህ ላልቶአል፤ ምሰሶው ጠብቆ አልተተከለም፤ ሸራው አልተወጠረም፤ በዚያ ጊዜ ታላቅ ምርኮ ይከፋፈላል፤ አንካሳ እንኳ ሳይቀር ምርኮ ይወስዳል።

24በጽዮን ተቀምጦ፣ “ታምሜአለሁ” የሚል አይኖርም፤ በዚያ የሚኖሩ ሰዎች ኀጢአትም ይቅር ይባላል።

ማብራሪያ

33:1-14 እዚህ ጋር ትዕቢተኛውና ሐሰተኛው አጥፊ ለፈጸመው ማታለልና ግፍ ሁሉ በጽድቅ ፍርድ የተጠየቀበትን እናያለን። ጻድቁ አምላክ ብዙ ጊዜ ኃጢአተኞችን በሠራውት ሥራ ልክ ይመልስላቸዋል። በእምነት በትሕትና እግዚአብሔርን የሚጠብቁት እርሱም ጸጋ የሞላበት ሆኖ ያገኙታል። ቀኑ እንደ ሆነ እንዲሁ ኃይሉ ይሁንላቸው። እግዚአብሔር በማንኛውም ማለዳ ለራሳችን ቢተወን እንጠፋለን። በየማለዳው ራሳችንን ለእርሱ አሳልፈን መስጠት አለብን፤ እንዲሁም የቀኑን ሥራ ለመሥራት በእርሱ ኃይል መውጣት አለብን። እግዚአብሔር ሲነሳ ጠላቶቹም ይበተናሉ። እውነተኛ ጥበብና እውቀት ወደ ድነት ኃይል ይመራሉ፤ ይህም በእግዚአብሔር መንገዶች ጸንተን እንድንቆም ያደርገናል። እውነተኛ እግዚአብሔርን መምሰልም በፍጹም የማይዘረፍ ወይም የማይባክን ብቸኛው ሀብት ነው። ኢየሩሳሌም የገባችበት ጭንቀት ተገልጿል። እግዚአብሔር ለሕዝቡ የሚገለጥበት ጊዜ ሌሎች ረዳቶች ሁሉ ሲጠፉ ነው። እግዚአብሔር ያደረገውን የሚሰሙ ሁሉ ሁሉን ነገር ማድረግ እንደሚችል ይገንዘቡ። በጽዮን ያሉ ኃጢአተኞች ከሌሎች ኃጢአተኞች የበለጠ የሚመልሱት ብዙ ነገር ይኖራቸዋል።

ሙሉ ማብራሪያውን ያንብቡ ድምፅ፣ ሙሉ ማብራሪያ እና ከመስመር ውጭ ንባብ

ትርጉሞች8 · 6

AMHEVG አንተ ሳትጠፋ የምታጠፋ፥ በአንተም ላይ ወንጀል ሳይደረግ ወንጀል የምታደርግ ወዮልህ! ማጥፋትን በተውህ ጊዜ ትጠፋለህ፤ መወንጀልንም በተውህ ጊዜ ይወነጅሉሃል። አማርኛ ENGNIV Woe to you, O destroyer, you who have not been destroyed! Woe to you, O traitor, you who have not been betrayed! When y… English BCV ኣታ እንተይጠፋእኻ እተጥፍእ፥ ኣታ እንተይተጠለምካ እትጠልም ወይለኻ! ምጥፋእ ምስ ሓደግካ ኽትጠፍእ ኢኻ፤ ወንጀል ምስ ሓደግካ ኽትውንጀል ኢኻ። ትግርኛ GAZBIB Yaa isa warra kaan balleessituu, ati ofii keetii amma iyyuu hin badne'o siif wayyoo! Utuu namni dabarsee si hin kennin,… Afaan Oromoo BCV GIZ አሌ ሎሙ ለእለ ያኀስሩክሙ ወለክሙሰ አልቦ ዘያኀስረክሙ፤ ዘሂ ዐለወ አኮ ኪያክሙ ዘዐለወ፤ ወይሠገሩ ዐላዊያን ወይእኅዝዎሙ ወከመ ቍንቍኔ ልብስ ከማሁ ይትበልዑ። giz GAZGAZ Yaa isa warra kaan balleessituu, ati ofii keetii amma iyyuu hin badne'o siif wayyoo! Utuu namni dabarsee si hin kennin,… Afaan Oromoo BCV aksum ኣታ እንተይጠፋእኻ እተጥፍእ፥ ኣታ እንተይተጠለምካ እትጠልም ወይለኻ! ምጥፋእ ምስ ሓደግካ ኽትጠፍእ ኢኻ፤ ወንጀል ምስ ሓደግካ ኽትውንጀል ኢኻ። ትግርኛ SWAHSUV Ole wako uharibuye ila hukuharibiwa, utendaye hila wala hukutendwa hila! Utakapokwisha kuharibu, utaharibiwa wewe; na u… Kiswahili