ትንቢተ ኢሳይያስ 20

AMHNIVአማርኛ6 ጥቅሶች1:24 አዳምጥ
አዳምጥ 1:24 · መደበኛ · አስደናቂ በBiblight ይክፈቱ

1ዋናው የጦር አዛዥ በአሦር ንጉሥ በሳርጎን ተልኮ፣ የአዛጦንን ከተማ ወሮ በያዘበት ዓመት፣

2በዚያ ጊዜ እግዚአብሔር የአሞጽን ልጅ ኢሳይያስን፣ “ማቁን ከሰውነትህ፣ ጫማህን ከእግርህ አውልቅ” ሲል ተናገረው። እርሱም እንዲሁ አደረገ፤ ዕርቃኑንና ባዶ እግሩን ተመላለሰ።

3ከዚያም እግዚአብሔር እንዲህ አለ፤ “ባሪያዬ ኢሳይያስ ሦስት ዓመት በግብፅና በኢትዮጵያ ለምልክትና ለማስጠንቀቂያ ዕርቃኑንና ባዶ እግሩን እንደሄደ፣

4እንዲሁ የአሦር ንጉሥ ወጣትና ሽማግሌ የሆኑትን የተማረኩ ግብፃውያንንና የተሰደዱ ኢትዮጵያውያንን ዕርቃናቸውንና ባዶ እግራቸውን ይወስዳቸዋል፤ መቀመጫቸውን ገልቦ በመስደድም ግብፅን ያዋርዳል።

5በኢትዮጵያ ተስፋ ያደረጉ፣ በግብፅ የተመኩ ይፈራሉ፤ ይዋረዳሉም።

6በዚያ ቀን በዚህ ባሕር ዳርቻ የሚኖረው ሕዝብ፣ ‘የተመካንባቸው፣ ከአሦር ንጉሥ ለማምለጥና ነጻ ለመውጣት የተሸሸግንባቸው ምን እንደ ደረሰባቸው ተመልከቱ እንግዲህ እኛስ እንዴት እናመልጣለን?’ ይላል።”

ማብራሪያ

20:1-6 የግብፅና የኢትዮጵያ ወረራና ድል መንሳት። ኢሳይያስ በውጭ ሲመላለስ ባልተለመደው ልብሱ ለሕዝቡ ምልክት ነበር። እርሱ እንደ ነቢይ ለዓለም እንደሞተ ለማሳየት በተለምዶ ማቅ ይለብስ ነበር። ይህንንም ከወገቡ መፍታት፣ የላይኛውን ልብስ አለመልበስ፣ ባዶ እግሩንም መሄድ ነበረበት። ይህ ምልክት የሚያመለክተውም ግብፃውያንና ኢትዮጵያውያን እንዲህ ተራቁተው በአሦር ንጉሥ ተማርከው እንደሚወሰዱ ነበር። ዓለም ለእግዚአብሔር በመታዘዝ ልዩ ሲሆኑ ብዙውን ጊዜ አማኞችን ሞኞች አድርጋ ትመለከታለች።

ሙሉ ማብራሪያውን ያንብቡ ድምፅ፣ ሙሉ ማብራሪያ እና ከመስመር ውጭ ንባብ

ትርጉሞች8 · 6