ትንቢተ ኢሳይያስ 19

AMHNIVአማርኛ25 ጥቅሶች4:52 አዳምጥ
አዳምጥ 4:52 · መደበኛ · አስደናቂ በBiblight ይክፈቱ

1ስለ ግብፅ የተነገረ ንግር፤ እነሆ፤ እግዚአብሔር በፈጣን ደመና ላይ ተቀምጦ ወደ ግብፅ ይመጣል፤ የግብፅ ጣዖቶች በፊቱ ይርዳሉ፤ የግብፃውያንም ልብ በውስጣቸው ይቀልጣል።

2“ግብፃዊውን በግብፃዊው ላይ አስነሣለሁ፤ ወንድም ወንድሙን፣ ባልንጀራ ባልንጀራውን፣ ከተማም ከተማን፣ መንግሥትም መንግሥትን ይወጋል።

3የግብፃውያን ልብ ይሰለባል፤ ዕቅዳቸውንም መና አስቀራለሁ፤ እነርሱም ጣዖታትንና የሙታንን መናፍስት፤ መናፍስት ጠሪዎችንና ጠንቋዮችን ምክር ይጠይቃሉ።

4ግብፃውያንን አሳልፌ፣ ለጨካኝ ጌታ ክንድ እሰጣቸዋለሁ፤ አስፈሪ ንጉሥም ይገዛቸዋል” ይላል የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር።

5የዐባይ ወንዝ ይቀንሳል፤ ውሃውም እየጐደለ ይሄዳል።

6መስኖዎቹ ይከረፋሉ፤ የግብፅ ጅረቶች ይጐድላሉ፤ ይጠፋሉም። ደንገሉና ቄጠማውም ይጠወልጋል፤

7እንዲሁም በዐባይ ዳር፣ በወንዙ መፋሰሻ ላይ ያሉት ተክሎች ይጠወልጋሉ። በዐባይ ዳር የተዘራው ዕርሻ ሁሉ፣ በነፋስ ይወሰዳል፤ ምንም አይቀርም።

8ዓሣ አጥማጆች ያዝናሉ፤ በዐባይ ወንዝ ላይ መንጠቆአቸውን የሚወረውሩ ሁሉ ያለቅሳሉ፤ በውሃ ላይ መረባቸውን የሚጥሉ ሁሉ፣ ጒልበታቸው ይዝላል።

9የተነደፈ የተልባ እግር የሚፈትሉ፣ የተባዘተ ጥጥ የሚሠሩ ሸማኔዎችም ተስፋ ይቈርጣሉ።

10ልብስ ሠሪዎች ያዝናሉ፤ ደመወዝተኞችም ልባቸው ይሰበራል።

11የጣኔዎስ አለቆች በጣም ሞኞች ናቸው፤ የፈርዖን ጠቢባን ምክራቸው የማይረባ ነው፤ ፈርዖንን፣ “እኔ ከጥበበኞች አንዱ ነኝ፤ የጥንት ነገሥታትም ደቀ መዝሙር ነኝ” እንዴት ትሉታላችሁ?

12የእናንተ ጠቢባን አሁን የት አሉ? የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር በግብፅ ላይ ያሰበውን ነገር፣ እስቲ ያሳዩአችሁ፤ ያሳውቋችሁም።

13የጣኔዎስ አለቆች ተሞኝተዋል፤ የሜምፊስ ሹማምት ተታለዋል፤ የሕዝቧ ዋና ዋናዎች፣ ግብፅን አስተዋታል።

14እግዚአብሔር የድንዛዜን መንፈስ አፍሶባቸዋል፤ ሰካራም በትፋቱ ዙሪያ እንደሚንገዳገድ፣ ግብፅንም በምታደርገው ነገር ሁሉ እንድትንገዳገድ አደረጓት።

15ራስም ይሁን ጅራት፣ የዘንባባ ዝንጣፊም ይሁን ደንገል፣ ለግብፅ የሚያደርጉላት አንዳች ነገር የለም።

16በዚያን ቀን ግብፃውያን እንደ ሴት ይሆናሉ፤ የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር በእነርሱ ላይ ካነሣው ክንዱ የተነሣ በፍርሀት ይንቀጠቀጣሉ።

17የይሁዳ ምድር በግብፅ ላይ ሽብር ትነዛለች፤ የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር በእነርሱ ላይ ካቀደው የተነሣ፣ ስለ ይሁዳ፣ ወሬ የሰማ ሁሉ ይሸበራል።

18በዚያ ቀን አምስት የግብፅ ከተሞች በከነዓን ቋንቋ ይናገራሉ፤ የሰራዊት ጌታ የእግዚአብሔርም ወገን ለመሆን ቃል ኪዳን ይገባሉ፤ ከእነዚህም ከተሞች አንዲቱ የጥፋት ከተማ ተብላ ትጠራለች።

19በዚያ ቀን በግብፅ ምድር መካከል ለእግዚአብሔር መሠዊያ ይሠራል፤ በድንበሯም ላይ ለእግዚአብሔር ዐምድ ይቆማል።

20ይህም በግብፅ ምድር ለሰራዊት ጌታ ለእግዚአብሔር ምልክትና ምስክር ይሆናል፤ ከሚያስጨን ቋቸውም የተነሣ ወደ እግዚአብሔር ሲጮኹ፣ አዳኝና ታዳጊ ይልክላቸዋል፤ እርሱም ያድናቸዋል።

21እግዚአብሔር ራሱን ለግብፃውያን ይገልጣል፤ እነርሱም በዚያ ቀን እግዚአብሔርን ያውቁታል፤ በመሥዋዕትና በእህል ቍርባንም ያመልኩታል። ለእግዚአብሔር ስለት ይሳላሉ፤ የተሳሉትንም ይፈጽሙታል።

22እግዚአብሔር ግብፅን በመቅሠፍት ይመታታል፤ መትቶም፤ ይፈውሳቸዋል። እነርሱም ወደ እግዚአብሔር ይመለሳሉ፤ እርሱም ልመናቸውን ሰምቶ ይፈውሳቸዋል።

23በዚያ ቀን ከግብፅ ወደ አሦር አውራ መንገድ ይዘረጋል፤ አሦራውያን ወደ ግብፅ፣ ግብፃውያንም ወደ አሦር ይሄዳሉ፤ ግብፃውያንና አሦራውያን በአንድነት ያመልካሉ።

24በዚያ ቀን እስራኤል፣ ከግብፅና ከአሦር ጋር የምድር በረከት ለመሆን በሦስተኛነት ትቈጠራለች።

25የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔርም፣ “ሕዝቤ ግብፅ፣ የእጄ ሥራ አሦር፣ ርስቴም እስራኤል የተባረኩ ይሁኑ” ብሎ ይባርካቸዋል።

ማብራሪያ

19:1-17 እግዚአብሔር በፍርዶቹ ወደ ግብፅ ይወርዳል። የጥፋታቸውን መንስዔዎች ከራሳቸው መካከል ያስነሳል። ክፉ ሰዎች ከአደጋ ሲያመልጡ ራሳቸውን ደኅና እንደሆኑ አድርገው ያስባሉ፤ ነገር ግን ክፋት ኃጢአተኞችን ያሳድዳቸዋል፥ ንስሐ ካልገቡ በስተቀርም ፈጥኖ ይደርስባቸዋል። ግብፃውያን በጥቂት ጊዜ ውስጥ እንደተፈጸመው ሁሉ፣ በጭካኔ በሚገዛቸው በአንድ ገዢ እጅ ይሰጡበታል። ግብፃውያን በጥበብና በዕውቀት ይታወቁ ነበር፤ ሆኖም ጌታ ለገዛ ጠማማ ሴራዎቻቸውና እንዲጣሉ አሳልፎ ይሰጣቸዋል፥ ምድራቸውም በእርስ በእርስ ግጭታቸው የተነሳ የንቀትና የምሕረት ነገር እስክትሆን ድረስ። ኃጢአተኞችን የናቋቸውና የጨቆኗቸው ሰዎች እንዲያስፈሯቸው ያደርጋል፤ የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔርም የዓመፅን ሠሪዎች ለራሳቸውና እርስ በእርስ የሽብር ምንጭ ያደርጋቸዋል፤ በዙሪያቸው ያለውንም ነገር ሁሉ ለእነርሱ አስፈሪ ያደርገዋል።

ሙሉ ማብራሪያውን ያንብቡ ድምፅ፣ ሙሉ ማብራሪያ እና ከመስመር ውጭ ንባብ

ትርጉሞች8 · 6

AMHEVG ስለ ግብፅ የተነገረ ሸክም። እነሆ፥ እግዚአብሔር በፈጣን ደመና እይበረረ ወደ ግብፅ ይመጣል፤ የግብፅም ጣዖታት በፊቱ ይርዳሉ፥ የግብፅም ልብ በውስጥዋ ይቀልጣል። አማርኛ ENGNIV An oracle concerning Egypt: See, the Lord rides on a swift cloud and is coming to Egypt. The idols of Egypt tremble bef… English BCV ብዛዕባ ግብፂ ዝተነግረ ፆር። እንሆ እግዚኣብሄር፥ ኣብ ፈጣን ደመና ተቐሚጡ ናብ ግብፂ ኽመፅእ እዩ። ጣዖታት ግብፂ ኣብ ቅድሚኡ ራዕራዕ ክብሉ እዮም፤ ልቢ ግብፃውያን ከዓ ኽመክኽ እዩ። ትግርኛ GAZBIB Wanti biyya Gibxii irratti ta'uuf jiru in dubbatame. Kunoo! Waaqayyo duumessa ariifataadhaan gara biyya Gibxii in dhufa… Afaan Oromoo BCV GIZ ነገር በእንተ ግብፅ፤ ናሁ እግዚአብሔር ይነብር ዲበ ደመና ብሩህ ወይመጽእ ውስተ ግብፅ ወያድለቀልቅ ግብረ እደዊሆሙ ለግብፅ እምቅድመ ገጹ ወይትቀጠቀጥ ልቦሙ በላዕሌሆሙ። giz GAZGAZ Wanti biyya Gibxii irratti ta'uuf jiru in dubbatame. Kunoo! Waaqayyo duumessa ariifataadhaan gara biyya Gibxii in dhufa… Afaan Oromoo BCV aksum ብዛዕባ ግብፂ ዝተነግረ ፆር። እንሆ እግዚኣብሄር፥ ኣብ ፈጣን ደመና ተቐሚጡ ናብ ግብፂ ኽመፅእ እዩ። ጣዖታት ግብፂ ኣብ ቅድሚኡ ራዕራዕ ክብሉ እዮም፤ ልቢ ግብፃውያን ከዓ ኽመክኽ እዩ። ትግርኛ SWAHSUV Ufunuo juu ya Misri. Tazama, Bwana amepanda juu ya wingu jepesi, anafika Misri; na sanamu za Misri zinatikisika mbele z… Kiswahili