ትንቢተ ኢሳይያስ 14

AMHEVGአማርኛ31 ጥቅሶች4:59 አዳምጥ
አዳምጥ 4:59 · መደበኛ · አስደናቂ በBiblight ይክፈቱ

1እግዚአብሔርም ያዕቆብን ይምረዋል፥ እስራኤልንም ደግሞ ይመርጠዋል፥ በአገራቸውም ያኖራቸዋል፤ መጻተኛም ከእርሱ ጋር ይተባበራል፥ ከያዕቆብም ቤት ጋር ይጣበቃል።

2አሕዛብም ይዘው ወደ ስፍራቸው ያመጡአቸዋል፥ የእስራኤልም ቤት በእግዚአብሔር ምድር እንደ ሎሌዎችና እንደ ገረዶች አድርገው ይገዙአቸዋል፤ የማረኩአቸውን ይማርካሉ፥ አስጨናቂዎችንም ይገዛሉ።

3በዚያም ቀን እንዲህ ይሆናል፤ እግዚአብሔር ከኀዘንህና ከመከራህ ከተገዛህለትም ከጽኑ ባርነት ያሳርፍሃል።

4ይህንም ምሳሌ በባቢሎን ንጉሥ ላይ ታነሣለህ እንዲህም ትላለህ፦ አስጨናቂ እንዴት ዐረፈ! አስገባሪም እንዴት ጸጥ አለ!

5አሕዛብንም በመዓትና በማያቋርጥ መምታት የመታውን፥ አሕዛብንም ባልተከለከለ መከራ በቍጣው የገዛውን የኀጥኣንን በትር የአለቆችንም ዘንግ እግዚአብሔር ሰብሮአል።

7ምድርም ሁሉ ዐርፋ በጸጥታ ተቀምጣለች እልልም ብላለች።

8ጥድና የሊባኖስ ዝግባ፦ አንተ ከተዋረድህ ጀምሮ ማንም ይቈርጠን ዘንድ አልወጣብንም፡ ብለው በአንተ ደስ አላቸው።

9ሲኦል በመምጣትህ ልትገናኝህ በታች ታወከች፤ የሞቱትንም፥ የምድርን ታላላቆች ሁሉ፥ ለአንተ አንቀሳቀሰች፥ የአሕዛብንም ነገሥታት ሁሉ ከዙፋኖቻቸው አስነሣች።

10እነዚህ ሁሉ፦ አንተ ደግሞ እንደ እኛ ደክመሃልን? እኛንስ መስለሃልን?

11ጌጥህና የበገናህ ድምፅ ወደ ሲኦል ወረደ፤ በበታችህም ብል ተነጥፎአል፥ ትልም መደረቢያህ ሆኖአል፡ ብለው ይመልሱልሃል።

12አንተ የንጋት ልጅ አጥቢያ ኮከብ ሆይ፥ እንዴት ከሰማይ ወደቅህ! አሕዛብንም ያዋረድህ አንተ ሆይ፥ እንዴት እስከ ምድር ድረስ ተቈረጥህ!

13አንተን በልብህ፦ ወደ ሰምይ ዐርጋለሁ፥ ዙፋኔንም ከእግዚአብሔር ከዋክብት በላይ ከፍ ከፍ አደርጋለሁ፥ በሰሜንም ዳርቻ በመሰብሰቢያ ተራራ ላይ እቀመጣለሁ፤

14ከዳመናዎች ከፍታ በላይ ዐርጋለሁ፥ በልዑልም እመሰላለሁ፡ አልህ።

15ነገር ግን ወደ ሲኦል ወደ ጕድጓዱም ጥልቅ ትወርዳለህ።

16የሚያዩህ ይመለከቱሃልና፦ በውኑ ምድርን ያንቀጠቀጠ፥ መንግሥታትንም ያናወጠ፥

17ዓለሙን ሁሉ ባድማ ያደረገ፥ ከተሞችንም ያፈረሰ ምርከኞቹንም ወደ ቤታቸው ያልሰደደ ሰው ይህ ነውን? ብለው ያስተውሉሃል።

18የአሕዛብ ነገሥታት ሁሉ በየቤታቸው በክብር አንቀላፍተዋል።

19አንተ ግን እንደ ተጠላ ቅርንጫፍ ከመቃብርህ ተጥለሃል፤ በሰይፍም የተወጉት፥ ተገድለውም ወደ ጕድጓዱ ድንጋዮች የወረዱት ከድነውሃል፤ እንደ ተረገጠም ሬሳ ሆነሃል።

20ምድርህን አጥፍተሃልና፥ ሕዝብህንም ገድለሃልና ከእነርሱ ጋር በመቃብር በአንድነት አትሆንም፤ የክፉዎች ዘር ለዘላለም የተጠራ አይሆንም።

21እንዳይነሡም፥ ምድርንም እንዳይወርሱ፥ የዓለሙንም ፊት በከተሞች እንዳይሞሉ ስለ አባቶቻቸው በደል ለልጆቹ ሞትን አዘጋጁላቸው።

22በእነርሱ ላይ እነሣለሁ ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር፤ ከባቢሎን ስምንና ቅሬታን፥ ዘርንና ትውልድንም እቈርጣለሁ ይላል እግዚአብሔር።

23የጃርት መኖርያ የውኃም መቋሚያ አደርጋታለሁ፤ በጥፋትም መጥረጊያ እጠርጋታለሁ ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር።

24የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ብሎ ምሎአል፦ እንደ ተናገርሁ በእርግጥ ይሆናል፥ እንደ አሰብሁም እንዲሁ ይቆማል።

25አሦርን በምድሬ ላይ እሰብረዋለሁ፥ በተራራዬም ላይ እረግጠዋለሁ፤ ቀንበሩም ከእነርሱ ላይ ይነሣል፥ ሸክሙም ከጫንቃቸው ላይ ይወገዳል።

26በምድር ሁሉ ላይ እግዚአብሔር ያሰበው አሳብ ይህ ነው፥ በአሕዛብም ሁሉ ላይ የተዘረጋች እጅ ይህች ናት።

27የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር ይህን አስቦአል፤ የሚያስጥለውስ ማን ነው? እጁም ተዘርግታለች፤ የሚመልሳትስ ማን ነው?

28ንጉሡ አካዝ በሞተበት ዓመት ይህ ሸክም ሆነ።

29ፍልስጥኤም ሆይ፥ ከእባቡ ሥር እፉኝት ይወጣልና፥ ፍሬውም የሚበርርና እሳት የሚመስል እባብ ይሆናልና የመታሽ በትር ስለ ተሰበረ ሁላችሁም ደስ አይበላችሁ።

30የድሆችም የበኵር ልጆች ይሰማራሉ፥ ችግረኞችም ተዘልለው ይተኛሉ፤ ሥርህንም በራብ እገድላለሁ፥ ቅሬታህም ይገደላል።

31አንተ በር ሆይ፥ ወዮ በል አንቺም ከተማ ሆይ፥ ጩኺ፤ ፍልስጥኤም ሆይ፥ ሁላችሁም ቀልጣችኋል፤ ጢስ ከሰሜን ይመጣል ከጭፍራውም ተለይቶ የሚቀር የለም።

32ለሕዝቡም መልእክተኞች ምን ብሎ መመለስ ይገባል? እግዚአብሔር ጽዮንን እንደ መሠረተ፥ የሕዝቡም ችግረኞች በእርስዋ ውስጥ እንደሚጠጉ ነው።

ማብራሪያ

14:1-23 የእግዚአብሔር መለኮታዊ አሳብ ሁሉ ለእግዚአብሔር ሕዝብ መልካምነት ታስቦ የተዘጋጀ ነው። በተስፋይቱ ምድር መሰፈር የእግዚአብሔር ምሕረት ውጤት ነው። ቤተ ክርስቲያን እግዚአብሔር የሚቀበላቸውን ሁሉ ትቀበል። የእግዚአብሔር ሕዝብ፣ ዕጣ ፈንታቸው በወደቀበት ሁሉ፣ በትክክለኛና በሚያማልል አኗኗራቸው ሃይማኖትን ማስተዋወቅ (ወይም እንዲወደድ ማድረግ) ይገባቸዋል። ከእነርሱ ጋር ለመታረቅ ያልፈቀዱት በእነርሱ ሊዋረዱ ይገባል። ይህ፣ ወንጌልን ይቃወሙ የነበሩ ሰዎች እንዲታዘዙት ሲደረጉ፣ የወንጌል ስኬት ጋር ሊያያዝ ይችላል። እግዚአብሔር ራሱ የተባረከ ለውጥ ለማምጣት ይነሳል። ከሐዘናቸውና ከፍርሃታቸው፣ ከአሁኑ ሸክማቸው ስሜት፣ እና ከባሰ ነገር ፍርሃት ዕረፍት ያገኛሉ። ባቢሎን በሀብት የደለበች ነበረች። የባቢሎን ንጉሥ የዚህን ያህል ታላቅ ሀብት ፍጹም ቁጥጥር ስለነበረው፣ በእርሱም እርዳታ አሕዛብን ይገዛ ነበር። ይህ በተለይ የአይሁድን ሕዝብ ያመለክታል፤ እርሱም የባቢሎን ንጉሥ ኃጢአት መለኪያውን ሞላው። ጨካኝ ገዥዎች እውነተኛ ጥቅማቸውን ለፍትወታቸውና ለስሜታቸው ይሠዋሉ። እንደ እጅግ ቅዱሱ ለመሆን መመኘት ጸጋ የሞላበት ምኞት ነው፤ እርሱም፦ እኔ ቅዱስ ነኝና እናንተም ቅዱሳን ሁኑ ብሏልና፤ ነገር ግን እንደ ልዑል እግዚአብሔር ለመሆን ማሰብ ኃጢአተኛ ምኞት ነው፤ እርሱም፦ ራሱን ከፍ የሚያደርግ ሁሉ ይዋረዳል ብሏልና። ዲያብሎስ በዚህ መንገድ የመጀመሪያዎቹን ወላጆቻችንን ወደ ኃጢአት ሳበ። ፍጹም ጥፋት በእርሱ ላይ ይመጣበታል። ኃጢአት መሥራትን የማያቆሙትን እግዚአብሔር ያጠፋቸዋል።

ሙሉ ማብራሪያውን ያንብቡ ድምፅ፣ ሙሉ ማብራሪያ እና ከመስመር ውጭ ንባብ

ትርጉሞች8 · 6

ENGNIV The Lord will have compassion on Jacob; once again he will choose Israel and will settle them in their own land. Aliens… English BCV እግዚኣብሄር ንያእቆብ ክምሕሮ እዩ፤ ንእስራኤል ድማ ኽሓርዮ እዩ። ኣብ ሃገሮም ከዓ ኸንብሮም እዩ፤ ጓኖት ከዓ ምስኡ ኽሕወሱ እዮም፤ ኣብ ቤት ያእቆብውን ክለግቡ እዮም። ትግርኛ GAZBIB Waaqayyo sanyii Yaaqoobiif in oo'a, ammas Israa'eloota fo'ee biyya isaanii keessa in teessisa; sabni ormaa isaanitti in… Afaan Oromoo BCV GIZ ወይሣሀሎ እግዚአብሔር ለያዕቆብ ወየኀርዮ ካዕበ ለእስራኤል ወያዐርፋ ውስተ ብሔሮሙ ወይትዌሰኩ ውስቴቶሙ ፈላሲያን ወይትዌሰኩ ውስተ ቤተ ያዕቆብ። giz GAZGAZ Waaqayyo sanyii Yaaqoobiif in oo'a, ammas Israa'eloota fo'ee biyya isaanii keessa in teessisa; sabni ormaa isaanitti in… Afaan Oromoo BCV aksum እግዚኣብሄር ንያእቆብ ክምሕሮ እዩ፤ ንእስራኤል ድማ ኽሓርዮ እዩ። ኣብ ሃገሮም ከዓ ኸንብሮም እዩ፤ ጓኖት ከዓ ምስኡ ኽሕወሱ እዮም፤ ኣብ ቤት ያእቆብውን ክለግቡ እዮም። ትግርኛ AMHNIV እግዚአብሔር ለያዕቆብ ይራራለታል፤ እስራኤልን እንደ ገና ይመርጠዋል፤ በራሳቸውም አገር ያኖራቸዋል። መጻተኞች አብረዋቸው ይኖራሉ፤ ከያዕቆብም ቤት ጋር ይተባበራሉ። አማርኛ SWAHSUV Maana Bwana atamhurumia Yakobo, atamchagua Israeli tena, naye atawaweka katika nchi yao wenyewe; na mgeni atajiunga nao… Kiswahili