ትንቢተ ኢሳይያስ 14

AMHNIVአማርኛ32 ጥቅሶች5:46 አዳምጥ
አዳምጥ 5:46 · መደበኛ · አስደናቂ በBiblight ይክፈቱ

1እግዚአብሔር ለያዕቆብ ይራራለታል፤ እስራኤልን እንደ ገና ይመርጠዋል፤ በራሳቸውም አገር ያኖራቸዋል። መጻተኞች አብረዋቸው ይኖራሉ፤ ከያዕቆብም ቤት ጋር ይተባበራሉ።

2አሕዛብም ይወስዷቸዋል፤ ወደ ገዛ ስፍራቸውም ይመልሷቸዋል። የእስራኤል ቤት አሕዛብን ርስት ያደርጓቸዋል፤ በእግዚአብሔርም ምድር ወንዶችና ሴቶች ባሪያዎች አድርገው ይገዟቸዋል፤ የማረኳቸውን ይማርኳቸዋል፤ የጨቈኗቸውንም ይገዟቸዋል።

3እግዚአብሔር ከሥቃይህ፣ ከመከራህና ከጽኑ ባርነትህ ባሳረፈህ ቀን፣

4በባቢሎን ንጉሥ ላይ ትሣለቃለህ፤ እንዲህም ትላለህ፤ ጨቋኙ እንዴት አበቃለት! አስገባሪነቱስ እንዴት አከተመ!

5እግዚአብሔር የክፉዎችን ዘንግ፣ የገዦችንም በትረ መንግሥት ሰብሮአል፤

6ሕዝቦችን በማያቋርጥ ቍጣ የመታውን፣ ያለ ርኅራኄ እያሳደደ የቀጠቀጠውን ሰብሮአል።

7ምድር ሁሉ ሰላምና ዕረፍት አግኝታለች፤ የደስታም ዝማሬ ታስተጋባለች።

8ጥድና የሊባኖስ ዝግባ እንኳ ደስ ብሎአቸው፣ “አንተም ወደቅህ፤ ዕንጨት ቈራጭም መጥረቢያ አላነሣብንምቃ አሉ።

9በመጣህ ጊዜ ሲኦል ልትቀበልህ ተነሣሥታለች፤ ይቀበሉህም ዘንድ የሙታንን መናፍስት፣ በዓለም ገዥ የነበሩትን ሁሉ ቀስቅሳለች፤ በአሕዛብ ላይ የነገሡትን ነገሥታት ከዙፋናቸው አውርዳለች።

10እነርሱ ሁሉ ይመልሱልሃል፤ እንዲህም ይሉሃል፤ “አንተም እንደ እኛ ደከምህ፤ እንደ እኛም ሆንህ።”

11ክብርህ፣ ከነበገና ድምፁ ወደ ሲኦል ወረደ፤ ብሎች ከበታችህ ተነጥፈዋል፤ ትሎችም መደረቢያህ ይሆናሉ።

12አንተ የንጋት ልጅ፣ አጥቢያ ኮከብ ሆይ፤ እንዴት ከሰማይ ወደቅ አንተ ቀድሞ መንግሥታትን ያዋረድህ፤ እንዴት ወደ ምድር ተጣልህ!

13በልብህም እንዲህ አልህ፤ “ወደ ሰማይ ዐርጋለሁ፤ ዙፋኔንም ከእግዚአብሔር ከዋክብት በላይ ከፍ አደርጋለሁ፤ በተራራው መሰብሰቢያ፣ በተቀደሰውም ተራራ ከፍታ ላይ በዙፋኔ እቀመጣለሁ፤

14ከደመናዎችም ከፍታ በላይ ዐርጋለሁ፤ ራሴንም እንደ ልዑል አደርጋለሁ።”

15ነገር ግን ወደ ሲኦል፣ ወደ ጥልቁም ጕድጓድ ወርደሃል።

16የሚያዩህም አትኵረው እየተመለክቱህ፣ በመገረም ስለ አንተ እንዲህ ይላሉ፤ “ያ ምድርን ያናወጠ፣ መንግሥታትን ያንቀጠቀጠ፣ ይህ ሰው ነውን?

17ዓለምን ምድረ በዳ ያደረገ፤ ከተሞችን ያፈራረሰ፣ ምርኮኞቹንም ወደ አገራቸው እንዳይሄዱ የከለከለ ይህ ነውን?”

18የአሕዛብ ነገሥታት ሁሉ በክብር አንቀላፍተዋል፤ በየመቃብራቸው ዐርፈዋል።

19አንተ ግን እንደማይፈለግ ቅርንጫፍ፣ ከመቃብር ወጥተህ ተጥለሃል፤ በሰይፍ በተወጉት፣ ወደ ጥልቁ ድንጋዮች በወረዱት፣ በተገደሉትም ተሸፍነሃል። እንደ ተረገጠም ሬሳ ሆነሃል።

20ከእነርሱ ጋር በመቃብር አትሆንም፤ ምድርህን አጥፍተሃልና፤ ሕዝብህንም ፈጅተሃልና። የክፉ አድራጊዎች ዘር ፈጽሞ አይታወስም።

21ተነሥተው ምድርን እንዳይወርሱ፣ ዓለምንም በከተሞቻቸው እንዳይሞሉ፣ ስለ አባቶቻቸው ኀጢአት፣ ወንድ ልጆቹ የሚታረዱበትን ስፍራ አዘጋጁ።

22“በእነርሱ ላይ እነሣለሁ” ይላል የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር። “ስሟንና ትሩፋኖቿን፣ ዘሯንና ትውልዷን ከባቢሎን እቈርጣለሁ” ይላል እግዚአብሔር።

23“የጃርት መኖሪያ፣ ረግረጋማ ቦታ አደርጋታለሁ፤ በጥፋትም መጥረጊያ እጠርጋታለሁ” ይላል የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር።

24የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ብሎ ምሎአል፤ “እንደ ዐቀድሁት በርግጥ ይከናወናል፤ እንደ አሰብሁትም ይሆናል።

25አሦርን በምድሬ ላይ አደቃለሁ፤ በተራራዬም ላይ እረግጠዋለሁ፤ ቀንበሩ ከሕዝቤ ላይ ይነሣል፤ ሸክሙም ከትከሻቸው ላይ ይወርዳል።”

26ለምድር ሁሉ የታሰበው ዕቅድ ይህ ነው፤ በአሕዛብም ሁሉ ላይ የተዘረጋው እጅ ይኸው ነው።

27የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ አስቦአል፤ ማንስ ያግደዋል? እጁም ተዘርግቶአል? ማንስ ይመልሰዋል?

28ንጉሡ አካዝ በሞተበት ዓመት እንዲህ የሚል ንግር መጣ፤

29“እናንት ፍልስጥኤማውያን ሆይ፤ የመታችሁ በትር ስለ ተሰበረ ሁላችሁ ደስ አይበላችሁ፤ ከእባቡ ሥር እፉኝት ይወጣልና፤ ፍሬውም ተወርዋሪ መርዘኛ እባብ ይሆናል።

30ከድኻም ድኻ የሆኑት መሰማሪያ ያገኛሉ፤ ችግረኞችም ተዝናንተው ይተኛሉ፤ ሥርህን ግን በራብ እገድላለሁ፤ ትሩፋንህንም እፈጃለሁ።

31በር ሆይ፣ ዋይ በል፤ ከተማ ሆይ ጩኽ፣ ፍልስጥኤማውያን ሆይ፤ ሁላችሁም በፍርሀት ቅለጡ ጢስ ከሰሜን መጥቶብሃል፤ ከሰልፉ ተነጥሎ የሚቀር የለምና።

32ከዚያ ሕዝብ ለሚመጡ መልእክተኞች ምን መልስ ይሰጣል? መልሱ፣ “እግዚአብሔር ጽዮንን መሥርቶአል፤ መከራን የተቀበለው ሕዝብም፣ በእርሷ ውስጥ መጠጊያን አግኝቶአል” የሚል ነው።

ማብራሪያ

14:1-23 የእግዚአብሔር መለኮታዊ አሳብ ሁሉ ለእግዚአብሔር ሕዝብ መልካምነት ታስቦ የተዘጋጀ ነው። በተስፋይቱ ምድር መሰፈር የእግዚአብሔር ምሕረት ውጤት ነው። ቤተ ክርስቲያን እግዚአብሔር የሚቀበላቸውን ሁሉ ትቀበል። የእግዚአብሔር ሕዝብ፣ ዕጣ ፈንታቸው በወደቀበት ሁሉ፣ በትክክለኛና በሚያማልል አኗኗራቸው ሃይማኖትን ማስተዋወቅ (ወይም እንዲወደድ ማድረግ) ይገባቸዋል። ከእነርሱ ጋር ለመታረቅ ያልፈቀዱት በእነርሱ ሊዋረዱ ይገባል። ይህ፣ ወንጌልን ይቃወሙ የነበሩ ሰዎች እንዲታዘዙት ሲደረጉ፣ የወንጌል ስኬት ጋር ሊያያዝ ይችላል። እግዚአብሔር ራሱ የተባረከ ለውጥ ለማምጣት ይነሳል። ከሐዘናቸውና ከፍርሃታቸው፣ ከአሁኑ ሸክማቸው ስሜት፣ እና ከባሰ ነገር ፍርሃት ዕረፍት ያገኛሉ። ባቢሎን በሀብት የደለበች ነበረች። የባቢሎን ንጉሥ የዚህን ያህል ታላቅ ሀብት ፍጹም ቁጥጥር ስለነበረው፣ በእርሱም እርዳታ አሕዛብን ይገዛ ነበር። ይህ በተለይ የአይሁድን ሕዝብ ያመለክታል፤ እርሱም የባቢሎን ንጉሥ ኃጢአት መለኪያውን ሞላው። ጨካኝ ገዥዎች እውነተኛ ጥቅማቸውን ለፍትወታቸውና ለስሜታቸው ይሠዋሉ። እንደ እጅግ ቅዱሱ ለመሆን መመኘት ጸጋ የሞላበት ምኞት ነው፤ እርሱም፦ እኔ ቅዱስ ነኝና እናንተም ቅዱሳን ሁኑ ብሏልና፤ ነገር ግን እንደ ልዑል እግዚአብሔር ለመሆን ማሰብ ኃጢአተኛ ምኞት ነው፤ እርሱም፦ ራሱን ከፍ የሚያደርግ ሁሉ ይዋረዳል ብሏልና። ዲያብሎስ በዚህ መንገድ የመጀመሪያዎቹን ወላጆቻችንን ወደ ኃጢአት ሳበ። ፍጹም ጥፋት በእርሱ ላይ ይመጣበታል። ኃጢአት መሥራትን የማያቆሙትን እግዚአብሔር ያጠፋቸዋል።

ሙሉ ማብራሪያውን ያንብቡ ድምፅ፣ ሙሉ ማብራሪያ እና ከመስመር ውጭ ንባብ

ትርጉሞች8 · 6

AMHEVG እግዚአብሔርም ያዕቆብን ይምረዋል፥ እስራኤልንም ደግሞ ይመርጠዋል፥ በአገራቸውም ያኖራቸዋል፤ መጻተኛም ከእርሱ ጋር ይተባበራል፥ ከያዕቆብም ቤት ጋር ይጣበቃል። አማርኛ ENGNIV The Lord will have compassion on Jacob; once again he will choose Israel and will settle them in their own land. Aliens… English BCV እግዚኣብሄር ንያእቆብ ክምሕሮ እዩ፤ ንእስራኤል ድማ ኽሓርዮ እዩ። ኣብ ሃገሮም ከዓ ኸንብሮም እዩ፤ ጓኖት ከዓ ምስኡ ኽሕወሱ እዮም፤ ኣብ ቤት ያእቆብውን ክለግቡ እዮም። ትግርኛ GAZBIB Waaqayyo sanyii Yaaqoobiif in oo'a, ammas Israa'eloota fo'ee biyya isaanii keessa in teessisa; sabni ormaa isaanitti in… Afaan Oromoo BCV GIZ ወይሣሀሎ እግዚአብሔር ለያዕቆብ ወየኀርዮ ካዕበ ለእስራኤል ወያዐርፋ ውስተ ብሔሮሙ ወይትዌሰኩ ውስቴቶሙ ፈላሲያን ወይትዌሰኩ ውስተ ቤተ ያዕቆብ። giz GAZGAZ Waaqayyo sanyii Yaaqoobiif in oo'a, ammas Israa'eloota fo'ee biyya isaanii keessa in teessisa; sabni ormaa isaanitti in… Afaan Oromoo BCV aksum እግዚኣብሄር ንያእቆብ ክምሕሮ እዩ፤ ንእስራኤል ድማ ኽሓርዮ እዩ። ኣብ ሃገሮም ከዓ ኸንብሮም እዩ፤ ጓኖት ከዓ ምስኡ ኽሕወሱ እዮም፤ ኣብ ቤት ያእቆብውን ክለግቡ እዮም። ትግርኛ SWAHSUV Maana Bwana atamhurumia Yakobo, atamchagua Israeli tena, naye atawaweka katika nchi yao wenyewe; na mgeni atajiunga nao… Kiswahili