ወደ ገላትያ 1

AMHNIVአማርኛ24 ጥቅሶች3:46 አዳምጥ
አዳምጥ 3:46 · መደበኛ · አስደናቂ በBiblight ይክፈቱ

1ከሰዎች ወይም በሰው ከተላከው ሳይሆን፣ በኢየሱስ ክርስቶስና ከሙታን ባስነሣው በእግዚአብሔር አብ ሐዋርያ ከሆነው ከጳውሎስ፤

2አብረውኝም ካሉት ወንድሞች ሁሉ፤

3ከአባታችን ከእግዚአብሔር፣ ከጌታም ከኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋና ሰላም ለእናንተ ይሁን።

4እንደ አምላካችንና እንደ አባታችን ፈቃድ፣ ከዚህ ክፉ ዓለም ያድነን ዘንድ ስለ ኀጢአታችን ራሱን ሰጠ፤

5ከዘላለም እስከ ዘላለም ለእርሱ ክብር ይሁን፤ አሜን።

6በክርስቶስ ጸጋ የጠራችሁን እርሱን ትታችሁ፣ ወደ ተለየ ወንጌል እንዲህ ፈጥናችሁ መዞራችሁ ደንቆኛል፤

7እንደ እውነቱ ከሆነ ሌላ ወንጌል የለም። የሚያደነጋግሯችሁና የክርስቶስን ወንጌል ለማጣመም ጥረት የሚያደርጉ አንዳንድ ሰዎች አሉ።

8ነገር ግን እኛም ብንሆን ወይም የሰማይ መልአክ፣ ከሰበክንላችሁ ወንጌል የተለየ ወንጌል ቢሰብክላችሁ እርሱ ለዘላለም የተረገመ ይሁን።

9ቀደም ብለን እንዳልነው፣ አሁንም ደግሜ እላለሁ፤ ማንም ከተቀበላችሁት ሌላ የተለየ ወንጌል ቢሰብክላችሁ፣ እርሱ ለዘላለም የተረገመ ይሁን።

10አሁን እኔ ጐሽ ለመባል የምሻው በሰዎች ዘንድ ነው ወይስ በእግዚአብሔር ዘንድ? ወይስ ሰዎችን ደስ ለማሰኘት እየተጣጣርሁ ነው? ሰዎችን ደስ ለማሰኘት የምጥር ብሆን ኖሮ፣ የክርስቶስ አገልጋይ ባልሆንሁ ነበር።

11ወንድሞች ሆይ፤ የሰበክሁላችሁ ወንጌል ሰው ሠራሽ አለመሆኑን እንድታውቁ እፈልጋለሁ፤

12ከማንም ሰው አልተቀበልሁትም፤ ከማንም አልተማርሁትም፤ ይልቁንስ በመገለጥ ከኢየሱስ ክርስቶስ ተቀበልሁት።

13ቀድሞ በአይሁድ ሃይማኖት እንዴት እንደኖርሁ፣ የእግዚአብሔርንም ቤተ ክርስቲያን እንዴት በእጅጉ እንዳሳደድሁ፣ ለማጥፋትም እንዴት እንደጣርሁ ሰምታችኋል፤

14በእኔ ዕድሜ ዘመን ከነበሩት ከብዙዎቹ አይሁድ ይበልጥ በአይሁድ ሃይማኖት እልቅ ነበር፤ ስለ አባቶቼም ወግ እጅግ ቀናተኛ ነበርሁ።

15ነገር ግን፣ ከእናቴ ማሕፀን ጀምሮ የለየኝና በጸጋው የጠራኝ እግዚአብሔር፣

16በአሕዛብ መካከል ስለ እርሱ እንድሰብክ ልጁን በእኔ ሊገልጥ በወደደ ጊዜ፣ ከማንም ሥጋ ለባሽ ጋር አልተማከርሁም፤

17ከእኔ በፊት ሐዋርያት ወደ ሆኑትም ወደ ኢየሩሳሌም አልወጣሁም፤ ነገር ግን ወዲያው ወደ ዐረብ አገር ሄድሁ፤ በኋላም ወደ ደማስቆ ተመለስሁ።

18ከዚያም ከሦስት ዓመት በኋላ፣ ጴጥሮስን አገኘው ዘንድ ወደ ኢየሩሳሌም ወጣሁ፤ ከእርሱም ጋር ዐሥራ አምስት ቀን ተቀመጥሁ።

19ነገር ግን ከጌታ ወንድም ከያዕቆብ በቀር፣ ከሐዋርያት ማንንም አላየሁም።

20በምጽፍላችሁ ነገር በእግዚአብሔር ፊት ሐሰት እንደማልናገር አስረግጬ እነግራችኋለሁ።

21ከዚያም በኋላ፣ ወደ ሶርያና ወደ ኪልቅያ አገር ሄድሁ።

22በክርስቶስ ያሉት የይሁዳ አብያተ ክርስቲያናትም ፊቴን አይተው አያውቁም ነበር፤

23እነርሱ ግን፣ “ቀድሞ እኛን ሲያሳድድ የነበረ ሰው፣ ከዚህ በፊት ሊያጠፋው ይፈልግ የነበረውን እምነት አሁን እየሰበከ ነው” የሚለውን ወሬ ብቻ ሰምተው ነበር፤

24በእኔም ምክንያት እግዚአብሔርን አመሰገኑ።

ማብራሪያ

1:1-5 ቅዱስ ጳውሎስ የኢየሱስ ክርስቶስ ሐዋርያ ነበር፤ እርሱ በግልጽ በራሱ በእርሱ የተሾመ ነበር፤ ስለዚህም በመለኮታዊ ማንነቱ ከእርሱ ጋር አንድ በሆነውና ክርስቶስን አስታራቂ አድርጎ በሾመው በአብ በሆነው በእግዚአብሔር ጭምር ተሾመ። ጸጋ፣ ወደ እኛ ያለውን የእግዚአብሔርን በጎ ፈቃድና በእኛ ውስጥ የሚሠራውን በጎ ሥራውን ያጠቃልላል፤ ሰላም ደግሞ ለእኛ በእርግጥ የሚያስፈልገንን ያን ሁሉ ውስጣዊ መጽናናት ወይም ውጫዊ ብልጽግና ነው። እነርሱም ከምንጩ ከአብ ከእግዚአብሔር በኢየሱስ ክርስቶስ በኩል ይመጣሉ። ነገር ግን አስተውሉ፣ በመጀመሪያ ጸጋ ከዚያም ሰላም፤ ያለ ጸጋ እውነተኛ ሰላም ሊኖር አይችልም። ክርስቶስ ስለ ኃጢአታችን ራሱን ሰጠ፣ ለእኛም ማስተስረያ ሊሆንልን ነውና፤ ይህ የእግዚአብሔር ፍትህ የጠየቀው ሲሆን እርሱም በነጻ ለዚህ ራሱን አስገዛ። እዚህ ላይ የተሰጠው የዋጋ ወሰን የለሽ ታላቅነት መታየት ይኖርበታል፤ ከዚያም የኃጢአት ኃይል እጅግ ታላቅ በመሆኑ የእግዚአብሔር ልጅ በእርሷ ምትክ ካልተሰጠ በቀር በምንም መንገድ ሊወገድ እንደማይችል በግልጽ ይታያል። እነዚህን ነገሮች በሚገባ የሚያስተውል ሁሉ፣ ኃጢአት ሊገለጽ ከሚችለው ሁሉ እጅግ አስከፊ ነገር እንደሆነ ይገነዘባል፤ ይህም በእርግጥ ሊያንቀሳቅሰንና ሊያስፈራን ይገባል። በተለይም "ስለ ኃጢአታችን" የሚሉትን ቃላት በሚገባ አስተውሉ። ምክንያቱም እዚህ ላይ ደካማ ተፈጥሮአችን ወደ ኋላ ትመለሳለችና፣ በመጀመሪያም በራሷ ሥራ ብቁ ልትሆን ትፈልጋለች። እርሷ (ደካማ ተፈጥሮ) ጤነኛውን ሰው ታመጣ ነበር እንጂ ሐኪም የሚያስፈልገውን ሰው አይደለም። እርሱ እኛን ከእግዚአብሔር ቁጣና ከሕግ እርግማን ለመቤዠት ብቻ ሳይሆን፤ በተፈጥሮአችን ከተገዛንባቸው ከክፉ ልማዶችና ባሕሎችም ሊያድነን ነው። ነገር ግን በመንፈስ ቅድሳት ከዚህ ክፉ ዓለም ያልዳኑ ሰዎች፣ በኢየሱስ ደም ከጥፋቱ ነጻ ወጥተናል ብለው መጠበቅ ከንቱ ነው።

ሙሉ ማብራሪያውን ያንብቡ ድምፅ፣ ሙሉ ማብራሪያ እና ከመስመር ውጭ ንባብ

ትርጉሞች8 · 6

AMHEVG በኢየሱስ ክርስቶስ ከሙታንም ባነሣው በእግዚአብሔር አብ ሐዋርያ የሆነ እንጂ ከሰዎች ወይም በሰው ያልሆነ ጳውሎስ ከእኔም ጋር ያሉት ወንድሞች ሁሉ፥ ወደ ገላትያ አብያተ ክርስቲያናት፤ አማርኛ ENGNIV Paul, an apostle–sent not from men nor by man, but by Jesus Christ and God the Father, who raised him from the dead– English BCV ካብቲ፥ ካብ ሰብ ወይ ብሰብ ዘይኮነስ፥ ብኢየሱስ ክርስቶስን፥ በቲ ኻብ ሙታን ዘተስኦ እግዚኣብሄር ኣብን፥ ሃዋርያ ክኸውን ዝተሓረየ ጳውሎስን፥ ትግርኛ GAZBIB Ani Phaawulos, namoota biraa yookiis karaa nama tokkoo utuu hin ta'in, Yesus Kristosiin, Waaqayyo abbaa isa Kristosin d… Afaan Oromoo BCV GIZ እምጳውሎስ ሐዋርያ ዘኢኮነ በእንተ ሰብእ ወኢኮነ እምኀበ ሰብእ፤ ዘእንበለ በእግዚእነ ኢየሱስ ክርስቶስ፤ ወእግዚአብሔር አብ ዘአንሥኦ እሙታን። giz GAZGAZ Ani Phaawulos, namoota biraa yookiis karaa nama tokkoo utuu hin ta'in, Yesus Kristosiin, Waaqayyo abbaa isa Kristosin d… Afaan Oromoo BCV aksum ካብቲ፥ ካብ ሰብ ወይ ብሰብ ዘይኮነስ፥ ብኢየሱስ ክርስቶስን፥ በቲ ኻብ ሙታን ዘተስኦ እግዚኣብሄር ኣብን፥ ሃዋርያ ክኸውን ዝተሓረየ ጳውሎስን፥ ትግርኛ SWAHSUV Paulo, mtume, (si mtume wa wanadamu, wala kutumwa na mwanadamu, bali na Yesu Kristo, na Mungu Baba aliyemfufua kutoka k… Kiswahili