ትንቢተ ሕዝቅኤል 47

AMHEVGአማርኛ23 ጥቅሶች4:53 አዳምጥ
አዳምጥ 4:53 · መደበኛ · አስደናቂ በBiblight ይክፈቱ

1ወደ መቅደሱም መዝጊያ መለሰኝ፤ እነሆም፥ ውኃ ከቤቱ መድረክ በታች ወደ ምሥራቅ ይወጣ ነበር፥ የቤቱ ፊት ወደ ምሥራቅ ይመለከት ነበርና፤ ውኃውም ከቤቱ ከቀኝ ወገን በታች በመሠዊያው በደቡብ በኩል ይወርድ ነበር።

2በሰሜኑም በር በኩል አወጣኝ፤ በስተ ውጭ ባለው መንገድ፥ ወደ ምሥራቅ ወደሚመለከት በስተ ውጭ ወዳለው በር አዞረኝ፤ እነሆም፥ ውኃው በቀኙ ወገን ይፈስስ ነበር።

3ሰውዬውም ገመዱን በእጁ ይዞ ወደ ምሥራቅ ወጣ አንድ ሺህም ክንድ ለካ፥ በውኃውም ውስጥ አሻገረኝ፥ ውኃም እስከ ቍርጭምጭሚት ደረሰ።

4ደግሞ አንድ ሺህ ለካ በውኃውም ውስጥ አሻገረኝ፥ ውኃውም እስከ ጕልበት ደረሰ። ደግሞም አንድ ሺህ ለካ በውኃውም ውስጥ አሻገረኝ፥ ውኃውም እስከ ወገብ ደረሰ።

5ደግሞ አንድ ሺህ ለካ ልሻገረውም የማልችለው ወንዝ ሆነ፤ ውኃውም ጥልቅ ነበረ፥ የሚዋኝበትም ውኃ ነበረ፤ ሰው ሊሻገረው የማይችለው ወንዝ ነበረ።

6እርሱም፦ የሰው ልጅ ሆይ፥ አይተሃልን? አለኝ። አመጣኝም፥ ወደ ወንዙም ዳር መለሰኝ።

7በተመለስሁም ጊዜ፥ እነሆ፥ በወንዙ ዳር በዚህና በዚያ እጅግ ብዙ ዛፎች ነበሩ።

8እርሱም እንዲህ አለኝ፦ ይህ ውኃ ወደ ምሥራቅ ምድር ይወጣል፥ ወደ ዓረባም ይወርዳል፥ ወደ ባሕሩም ይገባል፤ ወደ ባሕሩም ወደ ረከሰው ውኃ በገባ ጊዜ ውኃው ይፈወሳል።

9ሕያው ነፍስ ያለው ተንቀሳቃሽ ሁሉ ወንዙ በመጣበት ስፍራ ሁሉ በሕይወት ይኖራል፤ ይህም ውኃ በዚያ ስለ ደረሰ ዓሣዎች እጅግ ይበዛሉ፤ የባሕሩም ውኃ ይፈወሳል፥ ወንዙም በሚመጣበት ያለው ሁሉ በሕይወት ይኖራል።

10አጥማጆችም በዚያ ይቆማሉ፤ ከዓይንጋዲ ጀምሮ እስከ ዓይንኤግላይም ድረስ መረብ መዘርጊያ ይሆናል፤ ዓሣዎችም እንደ ታላቁ ባሕር ዓሣዎች በየወገናቸው እጅግ ይበዛሉ።

11እረግረጉና እቋሪው ውኃ ግን ጨው እንደ ሆነ ይኖራል እንጂ አይፈወስም።

12በወንዙም አጠገብ በዳሩ ላይ በዚህና በዚያ ፍሬው የሚበላ ዛፍ ሁሉ ይበቅላል፥ ቅጠሉም አይረግፍም ፍሬውም አይጐድልም፤ ውኃውም ከመቅደስ ይወጣልና በየወሩ ሁሉ የፍሬ በኵር ያገኛል፤ ፍሬውም ለመብል ቅጠሉም ለመድኃኒት ይሆናል።

13ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ርስት አድርጋችሁ ለአሥራ ሁለቱ የእስራኤል ነገዶች ምድሪቱን የምትከፍሉበት ድንበር ይህ ነው። ለዮሴፍ ሁለት እድል ፈንታ ይሆናል።

14ለአባቶቻችሁ እሰጣቸው ዘንድ ምዬ ነበርና እናንተ እኩል አድርጋችሁ ተካፈሉት ይህችም ምድር ርስት ትሆናችኋለች።

15የምድሪቱም ድንበር ይህ ነው። በሰሜኑ ወገን ከታላቁ ባሕር ጀምሮ በሔትሎን መንገድ ወደ ጽዳድ መግቢያ፤

16ሐማት፥ ቤሮታ፥ በደማስቆ ድንበርና በሐማት ድንበር መካከል ያለው ሲብራይም፥ በሐውራን ድንበር አጠገብ ያለው ሐጸርሃቲኮን።

17ድንበሩ ከባሕሩ በደማስቆ ድንበር ላይ ያለው ሐጸርዔናን ይሆናል፥ በሰሜንም በኩል የሐማት ድንበር አለ። የሰሜኑ ድንበር ይህ ነው።

18የምሥራቁም ድንበር በሐውራን በደማስቆና በገለዓድ በእስራኤልም ምድር መካከል ዮርዳኖስ ይሆናል። ከሰሜኑ ድንበር ጀምሮ እስከ ምሥራቁ ባሕር እስከ ታማር ድረስ የምሥራቁ ድንበር ይህ ነው።

19የደቡቡም ድንበር ከታማር ጀምሮ እስከ ሜርባ ቃዴስ ውኃ እስከ ግብፅ ወንዝ እስከ ታላቁ ባሕር ድረስ ይሆናል። የደቡቡ ድንበር ይህ ነው።

20የምዕራቡም ድንበር ከደቡቡ ድንበር ጀምሮ እስከ ሐማት መግቢያ አንጻር ድረስ ታላቁ ባሕር ይሆናል። የምዕራቡ ድንበር ይህ ነው።

21እንዲሁ ይህችን ምድር እንደ እስራኤል ነገዶች መጠን ለእናንተ ትካፈላላችሁ።

22ለእናንተና በእናንተ መካከል ለሚቀመጡ በእናንተም መካከል ልጆችን ለሚወልዱ መጻተኞች ርስት አድርጋችሁ በዕጣ ትካፈሉአታላችሁ፤ እነርሱም በእስራኤል ልጆች መካከል እንዳሉ የአገር ልጆች ይሆኑላችኋል፥ በእስራኤልም ነገዶች መካከል ከእናንተ ጋር ርስትን ይወርሳሉ።

23መጻተኛውም በማናቸውም ነገድ መካከል ቢቀመጥ በዚያ ርስቱን ትሰጡታላችሁ፥ ይላል ጌታ እግዚአብሔር።

ማብራሪያ

ኤዜኬል 47:1-23

እነዚህ ውኃዎች ከኢየሩሳሌም ወጥቶ በዙሪያው ባሉ አገሮች ሁሉ የተሰራጨውን የክርስቶስን ወንጌል ያመለክታሉ። እንዲሁም ከእርሱ ጋር የነበሩትን የመንፈስ ቅዱስ ስጦታዎችና ኃይላት የሚያሳዩ ሲሆን፣ በእነርሱም ኃይል ወንጌሉ ሩቅ ተሰራጭቶ የተባረኩ ውጤቶችን አፍርቷል። ክርስቶስ መቅደስ ነው፤ እርሱም በር ነው። ከእርሱም ከተወጋው ጎኑ የሕይወት ውኃ ይፈሳል። እነዚህ ውኃዎች እየጨመሩ የሚሄዱ ናቸው።

በዓለም ላይ የወንጌልን መስፋፋት እንዲሁም የጸጋ ሥራ በልብ ውስጥ የሚደረግበትን ሂደት ልብ በሉ። ከመለኮታዊ መሪነት በታች የተባረከውን የመንፈስ እንቅስቃሴም ተከተሉ።

ሙሉ ማብራሪያውን ያንብቡ ድምፅ፣ ሙሉ ማብራሪያ እና ከመስመር ውጭ ንባብ

ትርጉሞች8 · 6

ENGNIV The man brought me back to the entrance of the temple, and I saw water coming out from under the threshold of the templ… English BCV ንሱ ድማ ናብ ደገ እታ ቤተ መቕደስ መለሰኒ፤ ገፅ እታ ቤት ናብ ምብራቕ ኣቢሉ እዩ ዝርኢ እሞ፥ እንሆ ማያት ካብ ትሕቲ መድረኽ እታ ቤት፥ ናብ ምብራቕ ኣቢሉ ወፀ፤ እቲ ማያት ከዓ ኻብ ታሕ… ትግርኛ GAZBIB Kana booddee namichi gara balbala mana qulqullummaatti deebisee na fide; manni qulqullummaa gara ba'a-biiftuutti gara g… Afaan Oromoo BCV GIZ ወሜጠኒ ኀበ ኆኅተ ቤት፡ ወናሁ ማያት ይወጽኡ እምታሕተ መድረክ ቤት ጽባሐዊ እስመ ገጸ ቤት ለጽባሕ ወማያት ይወርዱ እምታሕተ መትከፈ ቤት ዘየማን እምደቡበ ምሥዋዕ። giz GAZGAZ Kana booddee namichi gara balbala mana qulqullummaatti deebisee na fide; manni qulqullummaa gara ba'a-biiftuutti gara g… Afaan Oromoo BCV aksum ንሱ ድማ ናብ ደገ እታ ቤተ መቕደስ መለሰኒ፤ ገፅ እታ ቤት ናብ ምብራቕ ኣቢሉ እዩ ዝርኢ እሞ፥ እንሆ ማያት ካብ ትሕቲ መድረኽ እታ ቤት፥ ናብ ምብራቕ ኣቢሉ ወፀ፤ እቲ ማያት ከዓ ኻብ ታሕ… ትግርኛ AMHNIV ከዚያም ያ ሰው ወደ ቤተ መቅደሱ መግቢያ መልሶ አመጣኝ፤ ከቤተ መቅደሱ መድረክ ሥር ውሃ እየወጣ፣ ወደ ምሥራቅ ይፈስ ነበር፤ ቤተ መቅደሱ ለምሥራቅ ትይዩ ነበርና። ውሃው ከቤተ መቅደሱ በስተ… አማርኛ SWAHSUV Baadaye akanileta tena mpaka lango la nyumba; na tazama, maji yalitoka chini ya kizingiti cha nyumba, kwa njia ya masha… Kiswahili