ትንቢተ ሕዝቅኤል 47

AMHNIVአማርኛ23 ጥቅሶች4:51 አዳምጥ
አዳምጥ 4:51 · መደበኛ · አስደናቂ በBiblight ይክፈቱ

1ከዚያም ያ ሰው ወደ ቤተ መቅደሱ መግቢያ መልሶ አመጣኝ፤ ከቤተ መቅደሱ መድረክ ሥር ውሃ እየወጣ፣ ወደ ምሥራቅ ይፈስ ነበር፤ ቤተ መቅደሱ ለምሥራቅ ትይዩ ነበርና። ውሃው ከቤተ መቅደሱ በስተ ደቡብ በኩል፣ በመሠዊያው ደቡብ በኩል፣ ሥር ሥሩን ይወርዳል።

2ከዚያም በሰሜኑ በር በማውጣት በውጭ አዙሮ በምሥራቅ አቅጣጫ ወዳለው የውጭ በር መራኝ፤ ውሃውም በደቡብ በኩል ይፈስ ነበር።

3ያም ሰው የመለኪያውን ገመድ በእጁ ይዞ ወደ ምሥራቅ በመሄድ፣ አንድ ሺህ ክንድ ለካ፤ ከዚያም እስከ ቁርጭምጭሚት በሚደርሰው ውሃ ውስጥ መራኝ፤

4ቀጥሎም አንድ ሺህ ክንድ ለካ፤ እስከ ጒልበት ወደሚደርስም ውሃ መራኝ፤ ከዚያም ሌላ አንድ ሺህ ክንድ ለካ፤ እስከ ወገብ ወደሚደርስም ውሃ መራኝ።

5እንደ ገናም አንድ ሺህ ክንድ ለካ፤ አሁን ግን ልሻገረው የማልችል ወንዝ ሆነ፤ ምክንያቱም ውሃው ስለ ሞላና ጥልቅ ስለ ነበረ፣ በዋና ካልሆነ በስተቀር በእግር ሊሻገሩት የማይቻል ነበረ።

6እርሱም፣ “የሰው ልጅ ሆይ፤ ይህን ታየዋለህን?” ሲል ጠየቀኝ። ከዚያም መልሶ ወደ ወንዙ ዳር መራኝ፤

7እዚያም በደረስሁ ጊዜ፣ በወንዙ ግራና ቀኝ ብዙ ዛፍ አየሁ።

8እርሱም እንዲህ አለኝ፤ “ይህ ውሃ ወደ ምሥራቅ ምድር ይፈሳል፤ ወደ ባሕሩ ወደሚገባበት ወደ ዓረባ ይወርዳል፤ ወደ ባሕሩም ሲፈስ፣ በዚያ የነበረው ውሃ ንጹሕ ይሆናል።

9ወንዙ በሚፈስበት ስፍራ ሁሉ ብዙ ሕያዋን ፍጡራን ይኖራሉ። ይህ ውሃ በዚያ ስለሚፈስና ጨውማ የሆነውን ውሃ ንጹሕ ስለሚያደርገው፣ ዓሣ በብዛት ይኖራል፤ ስለዚህ ወንዙ በሚፈስበት ስፍራ ሁሉ ማንኛውም ነገር በሕይወት ይኖራል።

10ዓሣ አጥማጆች በወንዙ ዳር ይቆማሉ፤ ከዓይንጋዲ እስከ ዓይንኤግላይም ድረስ ያለው ቦታ መረብ መዘርጊያ ይሆናል፤ ዓሣውም እንደ ታላቁ ባሕር ዓሣ፣ የተለያየ ዐይነት ይሆናል።

11ነገር ግን ረግረጉና ዕቋሪው ውሃ ንጹሕ አይሆንም፤ ጨው እንደሆነ ይቀራል።

12በወንዙም ዳርና ዳር፣ ፍሬ የሚያፈሩ የዛፍ ዐይነቶች ሁሉ ይበቅላሉ፤ ቅጠላቸው አይደርቅም፤ ፍሬ አልባም አይሆኑም። ከመቅደሱ የሚወጣው ውሃ ስለሚፈስላቸው በየወሩ ያፈራሉ፤ ፍሬያቸው ለምግብ፣ ቅጠላቸውም ለፈውስ ይሆናል።

13ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ “ምድሪቱን ርስት አድርገህ ለዐሥራ ሁለቱ የእስራኤል ነገድ የምታከፋፍሉባቸው፣ ወሰኖች እነዚህ ናቸው፤ ዮሴፍ ሁለት ዕጣ ይኑረው።

14እኩል አድርጋችሁ ከፋፍሉት፤ ለቀድሞ አባቶቻችሁ እሰጣቸው ዘንድ በተዘረጋች እጅ ስለ ማልሁ፣ ምድሪቱ ርስታችሁ ትሆናለች።

15“የምድሪቱ ወሰን ይህ ነው፤ “በሰሜን በኩል ከታላቁ ባሕር አንሥቶ በሔትሎን መንገድ በሐማት መተላለፊያ አድርጎ እስከ ጽዳድ ይደርሳል፤

16ከዚያም ቤሮታን፣ በደማስቆና በሐማት ወሰን መካከል ያለውን ሲብራይምን ዐልፎ፣ በሐውራን ወሰን ላይ እስካለው እስከ ሐጸርሃቲኮን ይዘልቃል።

17ወሰኑ ከባሕሩ በመነሣት፣ በሰሜኑ የደማስቆ ድንበር አድርጎ፣ የሐማትንም ዳርቻ ወደ ሰሜን ትቶ እስከ ሐጸርዔናን ይዘልቃል።

18“በምሥራቅ በኩል ወሰኑ በሐውራንና በደማስቆ መካከል፣ በገለዓድና በእስራኤል ምድር መካከል ዮርዳኖስ ይሆናል፤ የምሥራቁ ድንበር እስከ ምሥራቁ ባሕር ይወርድና እስከ ታማር ይዘልቃል፤ ይህም የምሥራቁ ወሰን ይሆናል።

19“በደቡብ በኩል ወሰኑ ከታማር ይነሣና እስከ ሜሪባ ቃዴስ ውሃ ይደርሳል፤ ከዚያም የግብፅን ደረቅ ወንዝ ተከትሎ እስከ ታላቁ ባሕር ይዘልቃል፤ ይህ የደቡቡ ወሰን ነው።

20“በምዕራቡ በኩል ወሰኑ ከሐማት መግቢያ ፊት ለፊት እስካለው ቦታ ድረስ ታላቁ ባሕር ይሆናል፤ ይህም የምዕራቡ ወሰን ይሆናል።

21“እነሆ፤ ይህችን ምድር በእስራኤል ነገድ ቍጥር ልክ ትከፋፈላላችሁ፤

22ለራሳችሁ፣ በመካከላችሁ ለሚኖሩት ልጆች ላሏቸው መጻተኞች ርስት አድርጋችሁ መድቡ፤ እነርሱንም እንደ እስራኤል ተወላጆች ቍጠሯቸው፤ እንደ እናንተ ከእስራኤል ነገዶች ርስት ይመደብላቸው።

23መጻተኛ በማንኛውም ነገድ መካከል ቢቀመጥ፣ በዚያ ርስቱን ስጡት” ይላል ጌታ እግዚአብሔር።

ማብራሪያ

ኤዜኬል 47:1-23

እነዚህ ውኃዎች ከኢየሩሳሌም ወጥቶ በዙሪያው ባሉ አገሮች ሁሉ የተሰራጨውን የክርስቶስን ወንጌል ያመለክታሉ። እንዲሁም ከእርሱ ጋር የነበሩትን የመንፈስ ቅዱስ ስጦታዎችና ኃይላት የሚያሳዩ ሲሆን፣ በእነርሱም ኃይል ወንጌሉ ሩቅ ተሰራጭቶ የተባረኩ ውጤቶችን አፍርቷል። ክርስቶስ መቅደስ ነው፤ እርሱም በር ነው። ከእርሱም ከተወጋው ጎኑ የሕይወት ውኃ ይፈሳል። እነዚህ ውኃዎች እየጨመሩ የሚሄዱ ናቸው።

በዓለም ላይ የወንጌልን መስፋፋት እንዲሁም የጸጋ ሥራ በልብ ውስጥ የሚደረግበትን ሂደት ልብ በሉ። ከመለኮታዊ መሪነት በታች የተባረከውን የመንፈስ እንቅስቃሴም ተከተሉ።

ሙሉ ማብራሪያውን ያንብቡ ድምፅ፣ ሙሉ ማብራሪያ እና ከመስመር ውጭ ንባብ

ትርጉሞች8 · 6

AMHEVG ወደ መቅደሱም መዝጊያ መለሰኝ፤ እነሆም፥ ውኃ ከቤቱ መድረክ በታች ወደ ምሥራቅ ይወጣ ነበር፥ የቤቱ ፊት ወደ ምሥራቅ ይመለከት ነበርና፤ ውኃውም ከቤቱ ከቀኝ ወገን በታች በመሠዊያው በደቡብ … አማርኛ ENGNIV The man brought me back to the entrance of the temple, and I saw water coming out from under the threshold of the templ… English BCV ንሱ ድማ ናብ ደገ እታ ቤተ መቕደስ መለሰኒ፤ ገፅ እታ ቤት ናብ ምብራቕ ኣቢሉ እዩ ዝርኢ እሞ፥ እንሆ ማያት ካብ ትሕቲ መድረኽ እታ ቤት፥ ናብ ምብራቕ ኣቢሉ ወፀ፤ እቲ ማያት ከዓ ኻብ ታሕ… ትግርኛ GAZBIB Kana booddee namichi gara balbala mana qulqullummaatti deebisee na fide; manni qulqullummaa gara ba'a-biiftuutti gara g… Afaan Oromoo BCV GIZ ወሜጠኒ ኀበ ኆኅተ ቤት፡ ወናሁ ማያት ይወጽኡ እምታሕተ መድረክ ቤት ጽባሐዊ እስመ ገጸ ቤት ለጽባሕ ወማያት ይወርዱ እምታሕተ መትከፈ ቤት ዘየማን እምደቡበ ምሥዋዕ። giz GAZGAZ Kana booddee namichi gara balbala mana qulqullummaatti deebisee na fide; manni qulqullummaa gara ba'a-biiftuutti gara g… Afaan Oromoo BCV aksum ንሱ ድማ ናብ ደገ እታ ቤተ መቕደስ መለሰኒ፤ ገፅ እታ ቤት ናብ ምብራቕ ኣቢሉ እዩ ዝርኢ እሞ፥ እንሆ ማያት ካብ ትሕቲ መድረኽ እታ ቤት፥ ናብ ምብራቕ ኣቢሉ ወፀ፤ እቲ ማያት ከዓ ኻብ ታሕ… ትግርኛ SWAHSUV Baadaye akanileta tena mpaka lango la nyumba; na tazama, maji yalitoka chini ya kizingiti cha nyumba, kwa njia ya masha… Kiswahili