ትንቢተ ሕዝቅኤል 42

AMHEVGአማርኛ20 ጥቅሶች3:30 አዳምጥ
አዳምጥ 3:30 · መደበኛ · አስደናቂ በBiblight ይክፈቱ

1በውጭም አደባባይ በሰሜኑ መንገድ አወጣኝ፥ በልዩውም ስፍራ አንጻርና በሰሜን በኩል ባለው ግቢ ፊት ለፊት ወዳለው ዕቃ ቤት አገባኝ።

2መቶ ክንድ በሆነው ርዝመት ፊት በሰሜን በኩል መዝጊያ ነበረ ወርዱም አምሳ ክንድ ነበረ።

3በውስጠኛውም አደባባይ በሀያው ክንድ አንጻር በውጭውም አደባባይ በወለሉ አንጻር በሦስት ደርብ በትይዩ የተሠራ መተላለፊያ ነበረ።

4በዕቃ ቤቶቹም ፊት በስተ ውስጥ ወርዱ አሥር ክንድ ርዝመቱ መቶ ክንድ የሆነ መንገድ ነበረ፤ መዝጊያዎቻቸውም ወደ ሰሜን ይመለከቱ ነበር።

5መተላለፊያውም አሳጥሮአቸዋልና ላይኞቹ ዕቃ ቤቶች ከመካከለኞቹና ከታችኞቹ ይልቅ አጫጭር ነበሩ።

6በሦስትም ደርብ ተሠርተው ነበርና፥ በአደባባዩም እንዳሉት አዕማድ፥ አዕማድ አልነበሩላቸውምና ስለዚህ ላይኞቹ ከመካከለኞቹና ከታችኞቹ ይልቅ ጠባብ ነበሩ።

7በውጭ በዕቃ ቤቶቹ አጠገብ ያለው፥ ወደ ውጭው አደባባይ የሚመለከተው ቅጥር፥ በዕቃ ቤቶች ትይዩ የሆነ፥ ርዝመቱ አምሳ ክንድ ነበረ።

8በመቅደሱ ፊት የነበሩት ዕቃ ቤቶች ርዝመታቸው መቶ ክንድ ሲሆን በውጭው አደባባይ በኩል የነበሩት ዕቃ ቤቶች ርዝመታቸው አምሳ ክንድ ነበረና።

9ከእነዚህም ዕቃ ቤቶች በታች በስተ ምሥራቅ በኩል፥ ሰው ከውጭው አደባባይ የሚገባበት መግቢያ ነበረ። ይህም በቅጥሩ ራስ አጠገብ ነበረ።

10በደቡብም በኩል በልዩው ስፍራና በግቢው አንጻር ዕቃ ቤቶች ነበሩ።

11በስተ ፊታቸውም የነበረ መንገድ በሰሜን በኩል እንደ ነበረው እንደ ዕቃ ቤቶቹ መንገድ ምስያ ነበረ። ርዝመታቸውም ወርዳቸውም መውጫቸውም ሥርዓታቸውም መዝጊያዎቻቸውም በዚያው ልክ ነበረ።

12በደቡብም በኩል ካሉት ዕቃ ቤቶች በታች በምሥራቅ በኩል በቅጥሩ ራስ አጠገብ መግቢያ ነበረ።

13እንዲህም አለኝ፦ በልዩ ስፍራ አንጻር በሰሜንና በደቡብ በኩል ያሉ ዕቃ ቤቶች፥ እነርሱ ወደ እግዚአብሔር የሚቀርቡ ካህናት ከሁሉ ይልቅ የተቀደሰውን ምግብ የሚበሉባቸው ቤቶች ናቸው። ስፍራው ቅዱስ ነውና በዚያ የተቀደሰውን ነገር የእህሉን ቍርባን የኃጢአቱንና የበደሉን መሥዋዕት ያኖራሉ።

14ካህናቱም በገቡ ጊዜ ከመቅደሱ በውጭው አደባባይ አይወጡም፤ የሚያገለግሉበትን ልብሳቸውን ግን ቅዱስ ነውና በዚያ ያኖሩታል፥ ሌላም ልብስ ለብሰው ወደ ሕዝብ ይወጣሉ።

15ውስጠኛውንም ቤት ለክቶ በፈጸመ ጊዜ ወደ ምሥራቅ በሚመለከት በር መንገድ አወጣኝ እርሱንም በዙሪያው ለካው።

16የምሥራቁን ወገን በመለኪያ ዘንግ አምስት መቶ ክንድ አድርጎ ለካ።

17ዞረም፥ የሰሜኑንም ወገን በመለኪያ ዘንግ አምስት መቶ ክንድ አድርጎ ለካ።

18ዞረም፥ የደቡቡንም ወገን በመለኪያ ዘንግ አምስት መቶ ክንድ አድርጎ ለካ።

19ዞረም፥ የምዕራቡንም ወገን በመለኪያ ዘንግ አምስት መቶ ክንድ አድርጎ ለካ።

20በአራቱ ወገን ለካው። የተቀደሰውንና ያልተቀደሰውን ይለይ ዘንድ ርዝመቱ አምስት መቶ ክንድ ወርዱም አምስት መቶ ክንድ የሆነ ቅጥር በዙሪያው ነበረ።

ማብራሪያ

ምዕራፍ ፵፪፥፩-፳ በዚህ ምዕራፍ የካህናት ክፍሎች፣ አጠቃቀማቸው እንዲሁም ቤተ መቅደሱ የቆመበት የቅዱሱ ተራራ ልኬት ተብራርተዋል። እነዚህ ክፍሎች ብዙ ነበሩ። ኢየሱስ፣ «በአባቴ ቤት ብዙ ማደሪያዎች አሉ» ብሏል። በምድር ላይ ባለው ቤቱም ብዙዎች አሉ፤ ብዙ ሕዝብ በእምነት በመቅደሱ ውስጥ ያድራሉ፣ እናም ገና ቦታ አለ። እነዚህ ክፍሎች፣ የግል ቢሆኑም እንኳ፣ ከቤተ መቅደሱ አጠገብ ነበሩ።

ሙሉ ማብራሪያውን ያንብቡ ድምፅ፣ ሙሉ ማብራሪያ እና ከመስመር ውጭ ንባብ

ትርጉሞች8 · 6

ENGNIV Then the man led me northward into the outer court and brought me to the rooms opposite the temple courtyard and opposi… English BCV ድሕሪዙይ ንሱ ናብቲ ናብ ሰሜን ዘብል መንገዲ ናብ ወፃኢ ዓፀድ ኣውፅአኒ፤ ናብቲ ኣብ ቅድሚ እቲ ጥራሑ ዘሎ ቦታን፥ ኣብ ግምባር እቲ ናብ ሰሜን ዝርኢ ህንፃን፥ ዘሎ ኽፍሊ ቤት ከዓ ኣእተወኒ። ትግርኛ GAZBIB Kana booddee namichi gara bitaatti gad na baasee oobdii isa gara duubaatti na fidee, kutaa manaa isa fuullee oobdii man… Afaan Oromoo BCV GIZ ወአውጽአኒ ውስተ ዓፀድ ጸናፊ፡ ወወሰደኒ ፍኖተ ሰሜን፡ ወአብአኒ ውስተ ኤስኬዴሬ ዘቅድመ ኦጶሊጱ ወዘቅድመ ደሪዞን ኀበ ሰሜን። giz GAZGAZ Kana booddee namichi gara bitaatti gad na baasee oobdii isa gara duubaatti na fidee, kutaa manaa isa fuullee oobdii man… Afaan Oromoo BCV aksum ድሕሪዙይ ንሱ ናብቲ ናብ ሰሜን ዘብል መንገዲ ናብ ወፃኢ ዓፀድ ኣውፅአኒ፤ ናብቲ ኣብ ቅድሚ እቲ ጥራሑ ዘሎ ቦታን፥ ኣብ ግምባር እቲ ናብ ሰሜን ዝርኢ ህንፃን፥ ዘሎ ኽፍሊ ቤት ከዓ ኣእተወኒ። ትግርኛ AMHNIV ከዚያም ያ ሰው በሰሜን በኩል ወዳለው ወደ ውጩ አደባባይ በማምጣት፣ በቤተ መቅደሱ አደባባይ ትይዩና በሰሜን በኩል ባለው ግንብ ትይዩ ወደ አሉት ክፍሎች አመጣኝ። አማርኛ SWAHSUV Ndipo akanileta mpaka ua wa nje, njia ya kuelekea upande wa kaskazini; akaniingiza katika chumba kilichopakabili mahali… Kiswahili