ትንቢተ ሕዝቅኤል 42

AMHNIVአማርኛ20 ጥቅሶች4:04 አዳምጥ
አዳምጥ 4:04 · መደበኛ · አስደናቂ በBiblight ይክፈቱ

1ከዚያም ያ ሰው በሰሜን በኩል ወዳለው ወደ ውጩ አደባባይ በማምጣት፣ በቤተ መቅደሱ አደባባይ ትይዩና በሰሜን በኩል ባለው ግንብ ትይዩ ወደ አሉት ክፍሎች አመጣኝ።

2በሩ በሰሜን ትይዩ የሆነው ሕንጻ ርዝመቱ አንድ መቶ ክንድ ወርዱም አምሳ ክንድ ነበር።

3ከውስጠኛው አደባባይ ሃያ ክንድ ርቀት ላይና በአንጻሩም ከውጩ አደባባይ የንጣፍ ድንጋይ ፊት ለፊት ርቀት ላይ በሦስት ደርቦች ትይዩ የሆኑ ሰገነቶች ነበሩ።

4ከክፍሎቹ ፊት ለፊት ወርዱ ዐሥር ክንድ፣ ርዝመቱ አንድ መቶ ክንድ የሆነ መተላለፊያ በውስጥ በኩል ነበር። የክፍሎቹም በሮች በሰሜን በኩል ነበሩ።

5የላይኞቹ ክፍሎች ጠበብ ያሉ ናቸው፤ ምክንያቱም ሰገነቶቹ ታችና መካከል ላይ ካሉት ከሕንጻው ክፍሎች ይልቅ ሰፋ ያሉ ቦታዎች ይዘውባቸዋልና።

6አደባባዮቹ ዐምዶች ሲኖሯቸው፣ በሦስተኛው ደርብ ላይ ያሉት ክፍሎች ግን ዐምድ የላቸውም። ስለዚህ የወለላቸው ስፋት በታችኛውና በመካከለኛው ደርብ ካሉት ክፍሎች ይልቅ ጠበብ ያለ ነው።

7ከክፍሎቹና፣ ከውጩ አደባባይ ትይዩ የሆነ የውጪ ግንብ አለ፤ ይህም በክፍሎቹ ፊት ለፊት ሆኖ አምሳ ክንድ ይረዝማል።

8ከውጩ አደባባይ ቀጥሎ ያሉት መደዳ ክፍሎች ርዝመት አምሳ ክንድ ሲሆን፣ ከቤተ መቅደሱ አጠገብ ያሉት መደዳ ክፍሎች ርዝመት ደግሞ አንድ መቶ ክንድ ነበር።

9ከውጩ አደባባይ ወደ ውስጥ ሲገባ፣ በስተ ምሥራቅ የታችኞቹ ክፍሎች መግቢያ ይገኛል።

10በደቡብ በኩል የውጩን አደባባይ ግንብ ተከትሎ፣ ከቤተ መቅደሱ አደባባይ ጋር የተያያዙና ከውጩ ግንብ ጋር ትይዩ የሆኑ ክፍሎች አሉ፤

11ከፊት ለፊታቸውም መተላለፊያ መንገድ አለ። እነዚህ በሰሜን በኩል ካሉት ክፍሎች ጋር ተመሳሳይ ሲሆኑ፣ ርዝመትና ወርዳቸው፣ መውጫና መጠናቸው አንድ ዐይነት ነበር፤ በሰሜን በኩል እንዳሉት በሮች፣

12በደቡብ በኩል ያሉት ክፍሎች በሮች መጠናቸው ተመሳሳይ ነበር። ከመመላለሻው መነሻ ላይ መግቢያ በር አለ፤ መመለሻውም ፊት ለፊት ካለው ወደ ምሥራቅ ከሚያመራው ግንብ ጋር ተጓዳኝ ነው።

13ከዚያም እንዲህ አለኝ፤ “ከቤተ መቅደሱ አደባባይ ፊት ለፊት ያሉት የሰሜኑና የደቡቡ ክፍሎች የካህናቱ ሲሆኑ፣ እነዚህም በእግዚአብሔር ፊት የሚቀርቡት ካህናት እጅግ የተቀደሱትን ቍርባኖች የሚበሉባቸው ናቸው። በዚያም እጅግ የተቀደሱትን ቍርባኖች ማለት የእህሉን ቍርባን፣ የኀጢአቱን ቍርባን፣ የበደሉን ቍርባን ያስቀምጣሉ፤ ቦታው ቅዱስ ነውና።

14ካህናቱ አንድ ጊዜ ወደ ተቀደሰው ቦታ ከገቡ በኋላ፣ ያገለገሉበትን ልብስ ሳያወልቁ ወደ ውጩ አደባባይ መውጣት አይችሉም፤ የተቀደሰ ነውና፤ ወደ ሕዝቡ ቦታ ከመምጣታቸው በፊት ሌላውን ልብሳቸውን መልበስ አለባቸው።”

15በቤተ መቅደሱ ውስጥ ያለውን ስፍራ ለክቶ ከጨረሰ በኋላ፣ በምሥራቅ በር በኩል ወደ ውጩ አወጣኝ፤ በዙሪያው ያለውንም ስፍራ ሁሉ ለካ፤

16በምሥራቅ ያለውንም በመለኪያው ዘንግ ለካ፤ አምስት መቶ ክንድ ሆነ።

17ሰሜኑንም ለካ፤ በመለኪያው ዘንግ አምስት መቶ ክንድ ሆነ።

18ደቡቡንም ለካ፤ በመለኪያው ዘንግ አምስት መቶ ክንድ ሆነ።

19ከዚያም ወደ ምዕራብ ጐን ዞሮ ለካ፤ በመለኪያው ዘንግ አምስት መቶ ክንድ ሆነ።

20ስለዚህ በአራቱም ማእዘን ለካው፤ የተቀደሰውን ስፍራ ከሌላው የሚለይ በዙሪያው ግንብ ነበረ፤ የግንቡም ርዝመት አምስት መቶ ክንድ ሲሆን፣ ወርዱ አምስት መቶ ክንድ ነበር።

ማብራሪያ

ምዕራፍ ፵፪፥፩-፳ በዚህ ምዕራፍ የካህናት ክፍሎች፣ አጠቃቀማቸው እንዲሁም ቤተ መቅደሱ የቆመበት የቅዱሱ ተራራ ልኬት ተብራርተዋል። እነዚህ ክፍሎች ብዙ ነበሩ። ኢየሱስ፣ «በአባቴ ቤት ብዙ ማደሪያዎች አሉ» ብሏል። በምድር ላይ ባለው ቤቱም ብዙዎች አሉ፤ ብዙ ሕዝብ በእምነት በመቅደሱ ውስጥ ያድራሉ፣ እናም ገና ቦታ አለ። እነዚህ ክፍሎች፣ የግል ቢሆኑም እንኳ፣ ከቤተ መቅደሱ አጠገብ ነበሩ።

ሙሉ ማብራሪያውን ያንብቡ ድምፅ፣ ሙሉ ማብራሪያ እና ከመስመር ውጭ ንባብ

ትርጉሞች8 · 6

AMHEVG በውጭም አደባባይ በሰሜኑ መንገድ አወጣኝ፥ በልዩውም ስፍራ አንጻርና በሰሜን በኩል ባለው ግቢ ፊት ለፊት ወዳለው ዕቃ ቤት አገባኝ። አማርኛ ENGNIV Then the man led me northward into the outer court and brought me to the rooms opposite the temple courtyard and opposi… English BCV ድሕሪዙይ ንሱ ናብቲ ናብ ሰሜን ዘብል መንገዲ ናብ ወፃኢ ዓፀድ ኣውፅአኒ፤ ናብቲ ኣብ ቅድሚ እቲ ጥራሑ ዘሎ ቦታን፥ ኣብ ግምባር እቲ ናብ ሰሜን ዝርኢ ህንፃን፥ ዘሎ ኽፍሊ ቤት ከዓ ኣእተወኒ። ትግርኛ GAZBIB Kana booddee namichi gara bitaatti gad na baasee oobdii isa gara duubaatti na fidee, kutaa manaa isa fuullee oobdii man… Afaan Oromoo BCV GIZ ወአውጽአኒ ውስተ ዓፀድ ጸናፊ፡ ወወሰደኒ ፍኖተ ሰሜን፡ ወአብአኒ ውስተ ኤስኬዴሬ ዘቅድመ ኦጶሊጱ ወዘቅድመ ደሪዞን ኀበ ሰሜን። giz GAZGAZ Kana booddee namichi gara bitaatti gad na baasee oobdii isa gara duubaatti na fidee, kutaa manaa isa fuullee oobdii man… Afaan Oromoo BCV aksum ድሕሪዙይ ንሱ ናብቲ ናብ ሰሜን ዘብል መንገዲ ናብ ወፃኢ ዓፀድ ኣውፅአኒ፤ ናብቲ ኣብ ቅድሚ እቲ ጥራሑ ዘሎ ቦታን፥ ኣብ ግምባር እቲ ናብ ሰሜን ዝርኢ ህንፃን፥ ዘሎ ኽፍሊ ቤት ከዓ ኣእተወኒ። ትግርኛ SWAHSUV Ndipo akanileta mpaka ua wa nje, njia ya kuelekea upande wa kaskazini; akaniingiza katika chumba kilichopakabili mahali… Kiswahili