ኦሪት ዘጸአት 27

AMHNIVአማርኛ21 ጥቅሶች4:07 አዳምጥ
አዳምጥ 4:07 · መደበኛ · አስደናቂ በBiblight ይክፈቱ

1“ከፍታው ሦስት ክንድ የሆነ መሠዊያ ከግራር ዕንጨት ሥራ፤ ርዝመቱ አምስት፣ ስፋቱም አምስት ክንድ ሆኖ ባለ አራት ማእዘን ይሁን።

2ቀንዶቹና መሠዊያው አንድ ወጥ ይሆኑ ዘንድ በአራቱም ማእዘኖች ላይ ቀንድ አድርግለት፤ መሠዊያውንም በነሐስ ለብጠው።

3ዕቃዎቹን ሁሉ ይኸውም የዐመድ ማስወገጃ ምንቸቶችን፣ መጫሪያዎችን፣ ጐድጓዳ ሳሕኖችን፣ ሜንጦዎችንና የፍም መያዣዎችን ከነሐስ አብጃቸው።

4ዐመድ ማውረጃ የሚሆን እንደ መረብ የሆነ የነሐስ ፍርግርግ አድርግለት በአራቱም የመረብ ማእዘኖች ላይ የነሐስ ቀለበቶች አብጅ።

5እስከ መሠዊያው ወገብ እንዲደርስ በመሠዊያው ዙሪያ ባለው እርከን ሥር አድርገው።

6የግራር ዕንጨት መሎጊያዎችን ለመሠዊያው ሠርተህ በነሐስ ለብጣቸው።

7በሸክም ጊዜ በመሠዊያው ሁለቱም ጎኖች እንዲሆኑ፣ መሎጊያዎቹ በቀለበቶቹ ውስጥ ይግቡ።

8መሠዊያውን ውስጡን ባዶ ከሆኑ ሳንቃዎች አብጀው፤ ልክ በተራራው ላይ ባየኸው መሠረት ይበጅ።

9“ለመገናኛው ድንኳን አደባባይ አብጅለት፤ በደቡብ በኩል ርዝመቱ አንድ መቶ ክንድ ይሁን፣ ከቀጭን በፍታ የተፈተሉ መጋረጃዎች፣

10ሃያ ምሰሶዎች፣ ሃያ የነሐስ መቆሚያዎች፣ የብር ኵላቦችና በምሰሶዎቹም ላይ ዘንጎች ይኑሩት።

11በሰሜኑም በኩል አንድ መቶ ክንድ ርዝመት ያላቸው መጋረጃዎች ይሁኑ፤ ሃያ ምሰሶዎቹ፣ ሃያ የነሐስ መቆሚያዎች፣ የብር ኵላቦችና በምሰሶዎችም ላይ ዘንጎች ይኑሩ።

12“የአደባባዩ ምዕራብ ጫፍ ስፋቱ አምሳ ክንድ ሆኖ ዐሥር ምሰሶዎችና ዐሥር መቆሚያዎች ያሉት መጋረጃዎች ይኑሩት።

13በምሥራቅ ጫፍ በፀሓይ መውጫ በኩል ያለው አደባባይ አሁንም አምስት ክንድ ስፋት ይኑረው።

14ሦስት ምሰሶዎችና ሦስት መቆሚያዎች ያሏቸው ርዝመታቸው ዐሥራ አምስት ክንድ የሆነ መጋረጃዎች በአንድ በኩል ባለው ደጃፍ ይሁኑ።

15ሦስት ምሰሶዎች ሦስት መቆሚያዎች ያሏቸው ርዝመታቸው ዐሥራ አምስት ክንድ የሆነ መጋረጃዎች በሌላው በኩል ይሁኑ።

16“ለአደባባዩ መግቢያ አራት ምሰሶዎችና አራት መቆሚያዎች ያሉት ከሰማያዊ፣ ከሐምራዊ፣ ከቀይ ማግና ከቀጭን በፍታ የተፈተለ፣ ጥልፍ ጠላፊ የጠለፈበት ሃያ ክንድ ርዝመት ያለው መጋረጃ ይሁን።

17በአደባባዩ ዙሪያ ያሉት ምሰሶዎች ሁሉ የብር ዘንጎች፣ ኵላቦችና የነሐስ መቆሚያዎች ይኑሯቸው።

18አደባባዩ ርዝመቱ አንድ መቶ ክንድ፣ ስፋቱ አምሳ ክንድ ሆኖ፣ በቀጭኑ ከተፈተለ ማግ ቁመታቸው አምስት ክንድ የሆነ መጋረጃዎችና የነሐስም መቆሚያዎች ያሉት ይሁን።

19ጥቅማቸው ምንም ዐይነት ይሁን፣ ለመገናኛው ድንኳን አገልግሎት የሚውሉ ዕቃዎች በሙሉ የድንኳኑና የአደባባዩ ካስማዎችም ሁሉ ሳይቀሩ ከነሐስ የተሠሩ ይሁኑ።

20“መብራቶቹ ባለማቋረጥ እንዲበሩ ለመብራቱ የሚሆን ተወቅጦ የተጠለለ ንጹሕ ዘይት እንዲያመጡልህ እስራኤላውያንን እዘዛቸው።

21በመገናኛው ድንኳን ውስጥ ከመጋረጃው በስተውጭ ይኸውም ከምስክሩ ታቦት ፊት ለፊት፣ አሮንና ወንድ ልጆቹ መብራቶቹን ከምሽት እስከ ንጋት በእግዚአብሔር (ያህዌ) ፊት እንዲበሩ ያድርጉ፤ ይህም በእስራኤላውያን ዘንድ ከትውልድ እስከ ትውልድ የዘላለም ሥርዐት ይሆናል።

ማብራሪያ

፳፯፥፩-፰ ከማደሪያው ድንኳን ፊት ለፊት ባለው አደባባይ፣ ሕዝቡ በሚሰበሰብበት ስፍራ፣ መሥዋዕቶቻቸውን ሊያመጡበት የሚገባቸውና ካህናቶቻቸውም ለእግዚብሔር የሚያቀርቡበት መሠዊያ ነበረ። ከነሐስ በተለበጠ እንጨት የተሠራ ነበር። የነሐስ ፍርግርግ በመሠዊያው ክፍት ክፍል ውስጥ የተቀመጠ ሲሆን፣ እሳት የሚቀመጥበትና መሥዋዕቱ የሚቃጠልበትም በመሀሉ አካባቢ ነበር። እንደ ወንፊት መረብ በሚመስል መልኩ የተሠራ ሲሆን፣ አመዱ ወደ ታች እንዲወድቅ ባዶ ሆኖ ተንጠልጥሎ ነበር። ይህ የነሐስ መሠዊያ ስለ ኃጢአታችን ማስተሰረያ የሞተው የክርስቶስ ምሳሌ ነበር። እንጨቱ በነሐስ ባይጠበቅ ኖሮ በሰማያዊው እሳት ተበልቶ በጠፋ ነበር፤ እንዲሁ የክርስቶስም የሰውነት ባህርይ በመለኮታዊ ኃይል ባልተደገፈ ኖሮ የእግዚአብሔርን ቁጣ መሸከም ባልቻለም ነበር።

ምዕራፍ 27 በዚህ ምዕራፍ ውስጥ መመሪያዎች ተሰጥተዋል፤

I. ስለ መሥዋዕቱ የሚሆን የናስ መሠዊያ (ቁጥር 1-8)።

II. ስለ ማደሪያው አደባባይና መጋረጃዎቹ (ቁጥር 9-19)።

III. ስለ መብራቱ ዘይት (ቁጥር 20, 21)።

ቁጥር 1-8 እግዚአብሔር በማደሪያው ድንኳን ውስጥ በመካከላቸው መገኘቱን ሊገልጥ አስቦ እንደነበር ሁሉ፣ እነርሱም አምልኳቸውን ለእርሱ የሚያቀርቡት በዚያ ነበር፤ በማደሪያው ድንኳን ውስጥ ራሱ ሳይሆን (ወደዚያ የሚገቡት ካህናት ብቻ ነበሩ፤ እንደ እግዚአብሔር የቤት አገልጋዮች)፣ ነገር ግን በማደሪያው ድንኳን ፊት ባለው አደባባይ ውስጥ ነበር፤ በዚያም እንደ ተራ ተገዢዎች ያገለግሉ ነበር። በዚያም መሠዊያ እንዲቆም ታዘዘ፤ ወደዚያም መሥዋዕቶቻቸውን ማምጣት ነበረባቸው፤ ካህናቶቻቸውም ለእግዚአብሔር ማቅረብ ነበረባቸው፤ ይህ መሠዊያም ስጦታዎቻቸውን ይቀድስ ነበር። እግዚአብሔር ከምሕረት መቀመጫው ትእዛዛቱን እንደሰጣቸው ሁሉ፣ እነርሱም አገልግሎቶቻቸውን ለእግዚአብሔር የሚያቀርቡት በዚያ ነበር፤ በዚህም በእግዚአብሔርና በእስራኤል መካከል ኅብረት ተመሠረተ። ሙሴ እዚህ ላይ መመሪያ ተሰጥቶታል፤

1. የመሠዊያው ስፋት፤ አራት ማዕዘን ነበር፣ ቁጥር 1።

2. ቀንዶቹ (ቁጥር 2)፣ ለጌጥና ለአገልግሎት የሚውሉ ነበሩ፤ መሥዋዕቶቹ በመሠዊያው ቀንዶች ላይ በገመድ ይታሰሩ ነበር፤ ወንጀለኞችም ለመጠጊያነት ወደ እነርሱ ይሸሹ ነበር።

3. ቁሳቁሱ፤ በናስ የተለበጠ ከእንጨት የተሠራ ነበር፣ ቁጥር 1, 2።

4. መገልገያዎቹ (ቁጥር 3)፣ ሁሉም ከናስ የተሠሩ ነበሩ።

5. ፍርግርጉ፣ በመሠዊያው ክፍት ክፍል ውስጥ፣ በመካከለኛው አካባቢ የሚገባ ነበር፤ እሳት የሚቀመጥበትና መሥዋዕቱ የሚቃጠልበት ነበር፤ እንደ ወንፊት የተሠራ መረብ ነበር፤ እሳቱ በተሻለ ሁኔታ እንዲነድድና አመዱም ወደ መሠዊያው ክፍት ክፍል እንዲወድቅ ክፍት ሆኖ ይንጠለጠል ነበር፣ ቁጥር 4, 5።

6.

ሙሉ ማብራሪያውን ያንብቡ ድምፅ፣ ሙሉ ማብራሪያ እና ከመስመር ውጭ ንባብ

ትርጉሞች8 · 6

AMHEVG “ርዝመቱ አምስት ክንድ፥ ወርዱም አምስት ክንድ መሠዊያ ከግራር እንጨት አድርግ፤ አራት ማዕዘንም ይሁን፤ ከፍታውም ሦስት ክንድ ይሁን። አማርኛ ENGNIV “Build an altar of acacia wood, three cubits high; it is to be square, five cubits long and five cubits wide. English BCV “ብዕንፀይቲ ሰራው ጌርካ ሓሙሽተ እመት ዝምንዋሑ፥ ሓሙሽተ እመት ዝምግፋሑ መሰውኢ ግበር። እቲ መሰውኢ ኣርባዕተ መኣዝን ይኹን፤ ምብራኹ ድማ ሰለስተ እመት ይኹን። ትግርኛ GAZBIB “Iddoo aarsaa dheerinni isaa dhundhuma shan, bal'inni isaa dhundhuma shan, irraan-oleen isaa dhundhuma sadii, gara arfa… Afaan Oromoo BCV GIZ ወአግብር ቤተ ምሥዋዕ እምዕፅ ዘኢይነቀዝ ዘኅምስ በእመት ኑኁ ወኅምስ በእመት ፅፍኁ ርቡዐ ይኩን ምሥዋዑ ወሥልስ በእመት ይኩን ቆሙ። giz GAZGAZ “Iddoo aarsaa dheerinni isaa dhundhuma shan, bal'inni isaa dhundhuma shan, irraan-oleen isaa dhundhuma sadii, gara arfa… Afaan Oromoo BCV aksum “ብዕንፀይቲ ሰራው ጌርካ ሓሙሽተ እመት ዝምንዋሑ፥ ሓሙሽተ እመት ዝምግፋሑ መሰውኢ ግበር። እቲ መሰውኢ ኣርባዕተ መኣዝን ይኹን፤ ምብራኹ ድማ ሰለስተ እመት ይኹን። ትግርኛ SWAHSUV Nawe fanya madhabahu ya mti wa mshita; urefu wake utakuwa ni dhiraa tano, na upana wake dhiraa tano; hiyo madhabahu ita… Kiswahili