መጽሐፈ መክብብ 9

AMHEVGአማርኛ18 ጥቅሶች3:49 አዳምጥ
አዳምጥ 3:49 · መደበኛ · አስደናቂ በBiblight ይክፈቱ

1ጻድቃንና ጠቢባን ሥራዎቻቸውም በእግዚአብሔር እጅ እንደ ሆኑ፥ ይህን ሁሉ እመረምር ዘንድ በልቤ አኖርሁ፤ ፍቅር ወይም ጥል ቢሆን ሰው አያውቅም ሁሉ ወደ ፊታቸው ነው።

2የጻድቁና የበደለኛው፥ የመልካሙና የክፉው፥ የንጹሑና የርኩሱ፥ መሥዋዕትን የሚሠዋውና የማይሠዋው፥ የሰው ሁሉ ድርሻው አንድ ነው፤ እንደ መልካሙ ሰው እንዲሁ ኃጢአተኛው፥ እንደ መሐለኛው ሰው እንዲሁ መሐላን የሚፈራው ነው።

3አንድ ድርሻ ሁሉን እንዲያገኝ ከፀሐይ በታች በተደረገው ሁሉ ይህ ነገር ክፉ ነው፤ ደግሞም የሰው ልጆች ልብ ክፋትን ትሞላለች፥ በሕይወታቸውም ሳሉ እብደት በልባቸው ነው፥ ከዚያም በኋላ ወደ ሙታን ይወርዳሉ።

4ያልሞተ ውሻ ከሞተ አንበሳ ይሻላልና ሰው ከሕያዋን ሁሉ ጋር በአንድነት ቢኖር ተስፋ አለው።

5ሕያዋን እንዲሞቱ ያውቃሉና፤ ሙታን ግን አንዳች አያውቁም፤ መታሰቢያቸውም ተረስቶአልና ከዚያ በኋላ ዋጋ የላቸውም።

6ፍቅራቸውና ጥላቸው ቅንዓታቸውም በአንድነት ጠፍቶአል፥ ከፀሐይ በታችም በሚሠራው ነገር ለዘላለም እድል ፈንታ ከእንግዲህ ወዲህ የላቸውም።

7እግዚአብሔር ሥራህን ተቀብሎታልና ሂድ፥ እንጀራህን በደስታ ብላ፥ የወይን ጠጅህንም በተድላ ጠጣ።

8ሁልጊዜ ልብስህ ነጭ ይሁን፤ ቅባትም ከራስህ ላይ አይታጣ።

9በሕይወትህ፥ አንተም ከፀሐይ በታች በምትደክምበት ድካም ይህ እድል ፈንታህ ነውና ከንቱ በሆነ በሕይወትህ ዘመን ሁሉ፥ ከፀሐይ በታች በሰጠህ፥ በከንቱ ዘመንህ ሁሉ፥ ከምትወድዳት ሚስትህ ጋር ደስ ይበልህ።

10አንተ በምትሄድበት በሲኦል ሥራና አሳብ እውቀትና ጥበብ አይገኙምና እጅህ ለማድረግ የምታገኘውን ሁሉ እንደ ኃይልህ አድርግ።

11እኔም ተመለስሁ፥ ከፀሐይ በታችም ሩጫ ለፈጣኖች፥ ሰልፍም ለኃያላን፥ እንጀራም ለጠቢባን፥ ባለጠግነትም ለአስተዋዮች፥ ሞገስም ለአዋቂዎች እንዳልሆነ አየሁ፤ ጊዜና እድል ግን ሁሉን ይገናኛቸዋል።

12ሰውም ጊዜውን አያውቅም፤ በክፉ መረብ እንደ ተጠመዱ ዓሣዎች፥ በወጥመድም እንደ ተያዙ ወፎች፥ እንዲሁ የሰው ልጆች በክፉ ጊዜ በድንገት ሲወድቅባቸው ይጠመዳሉ።

13ከፀሐይ በታችም ይህን ጥበብ አየሁ፥ እርስዋም በእኔ ዘንድ ታላቅ መሰለችኝ።

14ታናሽ ከተማ ነበረች፥ ጥቂቶች ሰዎችም ነበሩባት፤ ታላቅ ንጉሥም መጣባት ከበባትም፥ ታላቅ ግንብም ሠራባት።

15ጠቢብ ድሀ ሰውም ተገኘባት፥ ያችንም ከተማ በጥበቡ አዳናት፤ ያን ድሀ ሰው ግን ማንም አላሰበውም።

16እኔም፦ “ከኃይል ይልቅ ጥበብ ትበልጣለች፤ የድሀው ጥበብ ግን ተናቀች ቃሉም አልተሰማችም፡” አልሁ።

17በሰነፎች መካከል ከሚጮኽ ከገዢው ጩኸት ይልቅ የጠቢባን ቃል በጸጥታ ትሰማለች።

18ከጦር መሣሪያዎች ይልቅ ጥበብ ትሻላለች፤ አንድ ኃጢአተኛ ግን ብዙ መልካምን ያጠፋል።

ማብራሪያ

9:1-3 ሁሉንም አስቸጋሪ ነገሮች ማስረዳት ስለማንችል፣ የእግዚአብሔርን ቃል ወይም ሥራዎች መመርመራችን ከንቱ ነው ብለን ማሰብ የለብንም። ለራሳችን መልካም የሆኑና ለሌሎችም ጠቃሚ የሆኑ ብዙ ነገሮችን መማር እንችላለን። ነገር ግን የእግዚአብሔር ልዩ ፍቅር ተቀባይ የሆኑት ወይም በቁጣው ሥር የሆኑት እነማን እንደሆኑ ሰው ሁልጊዜ መወሰን አይችልም። እግዚአብሔርም በከበረውና በንቁሩ መካከል በወዲያኛው ዓለም በእርግጥ ልዩነት ያደርጋል። በአሁኑ ጊዜ ስላለው ደስታ ያለው ልዩነት የሚመጣው ጻድቃን ከሚያገኙት የውስጥ ድጋፍና መጽናናት እንዲሁም ከተለያዩ ፈተናዎችና ምሕረቶች ከሚያገኙት ጥቅም ነው። የሰዎች ልጆች ለራሳቸው እስከ ተተዉ ድረስ፣ ልባቸው በክፋት የተሞላ ነው። በኃጢአት ውስጥ የሚገኘው ብልጽግናም በድፍረት ክፋት እግዚአብሔርን እንዲዘልፉ ያደርጋቸዋል። ምንም እንኳ በዚህ ምድራዊ ሕይወት ጻድቃንና ክፉዎች ብዙውን ጊዜ ተመሳሳይ ሁኔታ ውስጥ ያሉ ሊመስሉ ቢችሉም፣ በወዲያኛው ዓለም ግን በመካከላቸው እጅግ ትልቅ ልዩነት ይኖራል።

፱፥፬-፲ በሕይወት ያለው እጅግ የተናቀ ሰው ሁኔታ፣ ንስሐ ሳይገቡ ከሞቱት እጅግ የከበሩ ሰዎች ሁኔታ ይበልጣል። ሰሎሞን ጥበበኞችንና እግዚአብሔርን የሚፈሩትን ሰዎች፣ የሕይወት ሁኔታቸው ምንም ቢሆን፣ በእግዚአብሔር ላይ በደስታ እንዲተማመኑ ይመክራል። እጅግ ጥቂትም ምግብ እንኳ ከአባታቸው ፍቅር ለጸሎት መልስ ሆኖ ሲመጣ፣ ልዩ ጣዕም ይኖረዋል።

ሙሉ ማብራሪያውን ያንብቡ ድምፅ፣ ሙሉ ማብራሪያ እና ከመስመር ውጭ ንባብ

ትርጉሞች8 · 6

ENGNIV So I reflected on all this and concluded that the righteous and the wise and what they do are in God's hands, but no ma… English BCV ብዛዕባ እዙይ ኣፀቢቐ ሓሰብኩ። ፃድቃንን ጥበበኛታትን፥ ኵሉ ዝሰርሕዎን፥ ኣብ ኢድ እግዚኣብሄር ከም ዝኾነ፥ ነዝ ዅሉ ኽምርምር ብልበይ ሓሰብኩ፤ ፍቕሪ ወይ ፅልኢ ይኹን ሰብ ኣይፈልጥን፤ ኵሉ… ትግርኛ GAZBIB Ani wanta kana hundumaa garaatti qabadheera, qoreeras; namoonni qajeelonnii fi ogeeyyiin hojii isaanii wajjin harka Waa… Afaan Oromoo BCV GIZ ከመ ጻድቃን ወጠበብት ወምግባሮሙ ውስተ እደ እግዚአብሔር ፍቅረ ወጸልአ አልቦ ዘያአምር ሰብእ ኵሉ ቅድመ ገጾሙ። giz GAZGAZ Ani wanta kana hundumaa garaatti qabadheera, qoreeras; namoonni qajeelonnii fi ogeeyyiin hojii isaanii wajjin harka Waa… Afaan Oromoo BCV aksum ብዛዕባ እዙይ ኣፀቢቐ ሓሰብኩ። ፃድቃንን ጥበበኛታትን፥ ኵሉ ዝሰርሕዎን፥ ኣብ ኢድ እግዚኣብሄር ከም ዝኾነ፥ ነዝ ዅሉ ኽምርምር ብልበይ ሓሰብኩ፤ ፍቕሪ ወይ ፅልኢ ይኹን ሰብ ኣይፈልጥን፤ ኵሉ… ትግርኛ AMHNIV ስለዚህ ይህን ሁሉ በልቤ አስቤ እንዲህ አልሁ፤ ጻድቃንና ጠቢባን የሚሠሩትም ሥራ በእግዚአብሔር እጅ ነው፤ ነገር ግን ፍቅር ይሁን ወይም ጥላቻ የሚጠብቀውን ማንም አያውቅም። አማርኛ SWAHSUV Na kwa ajili ya hayo yote, nikatia moyo wangu katika kuyatafutatafuta haya; ya kuwa wenye haki, na wenye hekima, pamoja… Kiswahili