መጽሐፈ መክብብ 9

AMHNIVአማርኛ18 ጥቅሶች3:52 አዳምጥ
አዳምጥ 3:52 · መደበኛ · አስደናቂ በBiblight ይክፈቱ

1ስለዚህ ይህን ሁሉ በልቤ አስቤ እንዲህ አልሁ፤ ጻድቃንና ጠቢባን የሚሠሩትም ሥራ በእግዚአብሔር እጅ ነው፤ ነገር ግን ፍቅር ይሁን ወይም ጥላቻ የሚጠብቀውን ማንም አያውቅም።

2ጻድቃንና ኀጥአን፣ ደጎችና ክፉዎች፣ ንጹሓንና ርኩሳን፣ መሥዋዕት የሚያቀርቡና የማያቀርቡ የሁሉም የመጨረሻ ዕጣ ፈንታ አንድ ነው። ለደጉ ሰው እንደሆነው ሁሉ፣ ለኀጢአተኛውም እንዲሁ ነው፤ ለሚምሉት እንደሆነው ሁሉ፣ መሐላን ለሚፈሩትም እንዲሁ ነው።

3ከፀሓይ በታች በሁሉም ላይ የሚሆነው ክፋት ይህ ነው፤ የሁሉም የመጨረሻ ዕጣ ፈንታ አንድ ነው። በዚህም ላይ የሰዎች ልብ በክፋት የተሞላ ነው፤ በሕይወት እያሉም በልባቸው ውስጥ እብደት አለ፤ በመጨረሻም ወደ ሙታን ይወርዳሉ።

4በሕያዋን መካከል ያለ ማንኛውም ሰው ተስፋ አለው፤ በሕይወት ያለ ውሻ ከሞተ አንበሳ ይሻላልና!

5ሕያዋን እንደሚሞቱ ያውቃሉና፤ ሙታን ግን ምንም አያውቁምና፤ መታሰቢያቸው ይረሳል፤ ምንም ዋጋ የላቸውም።

6ፍቅራቸው፣ ጥላቻቸው፣ ቅናታቸውም ከጠፋ ቈይቶአል፤ ከፀሓይ በታች በሚሆነው ነገር ሁሉ፣ ፈጽሞ ዕጣ ፈንታ አይኖራቸውም።

7ሂድ፤ ምግብህን በደስታ ብላ፤ ወይንህንም ልብህ ደስ ብሎት ጠጣ፤ ባደረግኸው ነገር እግዚአብሔር ደስ ብሎታልና።

8ዘወትር ልብስህ ነጭ ይሁን፤ ራስህንም ዘወትር በዘይት ቅባ።

9እግዚአብሔር ከፀሓይ በታች በሰጠህ በዚህ ትርጒም የለሽ የሕይወት ዘመን ሁሉ፣ ከንቱ በሆኑትም ቀኖችህ ሁሉ ከምትወዳት ሚስትህ ጋር ደስ ይበልህ፤ በሕይወትህና ከፀሓይ በታች በምትደክምበት ነገር ሁሉ ይህ ዕድል ፈንታህ ነውና።

10እጅህ የሚያገኘውን ሥራ ሁሉ በሙሉ ኀይልህ ሥራው፤ ልትሄድበት ባለው መቃብር ውስጥ መሥራትም ሆነ ማቀድ፣ ዕውቀትም ሆነ ጥበብ የለምና።

11ሌላም ነገር ከፀሓይ በታች አየሁ፡ ሩጫ ለፈጣኖች፣ ውጊያም ለኀያላን አይደለም፤ እንጀራ ለጥበበኞች፣ ወይም ባለጠግነት ለብልሆች፣ ወይም ሞገስ ለዐዋቂዎች አይሆንም፤ ጊዜና ዕድል ግን ሁሉን ይገናኛቸዋል።

12ደግሞም የራሱን ጊዜ የሚያውቅ ሰው የለም፤ ዓሦች በክፉ መረብ እንደሚያዙ፣ ወይም ወፎች በወጥመድ እንደሚጠመዱ፣ ሰዎችም ሳያስቡት በሚመጣባቸው፣ በክፉ ጊዜ ይጠመዳሉ።

13እንዲሁም እጅግ ያስገረመኝን ይህን የጥበብ ምሳሌ ከፀሓይ በታች አየሁ፦

14ጥቂት ሰዎች የሚኖሩባት አንዲት ትንሽ ከተማ ነበረች፤ አንድ ኀያል ንጉሥም መጣባት፤ ከበባት፤ በላይዋም ትልቅ ምሽግ ሠራባት።

15በዚያችም ከተማ ጥበበኛ የሆነ አንድ ድኻ ሰው ይኖር ነበር፤ በጥበቡም ከተማዋን አዳናት፤ ነገር ግን ያን ድኻ ማንም አላስታወሰውም።

16ስለዚህ፣ “ጥበብ ከኀይል ይበልጣል” አልሁ፤ ሆኖም የድኻው ጥበብ ተንቋል፤ ቃሉም አልተሰማም።

17ሞኞችን ከሚያስተዳድር ገዥ ጩኸት ይልቅ፣ ጠቢብ በዝግታ የሚናገረው ቃል ይደመጣል።

18ጥበብ ከጦር መሣሪያ ይበልጣል፤ ነገር ግን አንድ ኀጢአተኛ ብዙ መልካም ነገርን ያጠፋል።

ማብራሪያ

9:1-3 ሁሉንም አስቸጋሪ ነገሮች ማስረዳት ስለማንችል፣ የእግዚአብሔርን ቃል ወይም ሥራዎች መመርመራችን ከንቱ ነው ብለን ማሰብ የለብንም። ለራሳችን መልካም የሆኑና ለሌሎችም ጠቃሚ የሆኑ ብዙ ነገሮችን መማር እንችላለን። ነገር ግን የእግዚአብሔር ልዩ ፍቅር ተቀባይ የሆኑት ወይም በቁጣው ሥር የሆኑት እነማን እንደሆኑ ሰው ሁልጊዜ መወሰን አይችልም። እግዚአብሔርም በከበረውና በንቁሩ መካከል በወዲያኛው ዓለም በእርግጥ ልዩነት ያደርጋል። በአሁኑ ጊዜ ስላለው ደስታ ያለው ልዩነት የሚመጣው ጻድቃን ከሚያገኙት የውስጥ ድጋፍና መጽናናት እንዲሁም ከተለያዩ ፈተናዎችና ምሕረቶች ከሚያገኙት ጥቅም ነው። የሰዎች ልጆች ለራሳቸው እስከ ተተዉ ድረስ፣ ልባቸው በክፋት የተሞላ ነው። በኃጢአት ውስጥ የሚገኘው ብልጽግናም በድፍረት ክፋት እግዚአብሔርን እንዲዘልፉ ያደርጋቸዋል። ምንም እንኳ በዚህ ምድራዊ ሕይወት ጻድቃንና ክፉዎች ብዙውን ጊዜ ተመሳሳይ ሁኔታ ውስጥ ያሉ ሊመስሉ ቢችሉም፣ በወዲያኛው ዓለም ግን በመካከላቸው እጅግ ትልቅ ልዩነት ይኖራል።

፱፥፬-፲ በሕይወት ያለው እጅግ የተናቀ ሰው ሁኔታ፣ ንስሐ ሳይገቡ ከሞቱት እጅግ የከበሩ ሰዎች ሁኔታ ይበልጣል። ሰሎሞን ጥበበኞችንና እግዚአብሔርን የሚፈሩትን ሰዎች፣ የሕይወት ሁኔታቸው ምንም ቢሆን፣ በእግዚአብሔር ላይ በደስታ እንዲተማመኑ ይመክራል። እጅግ ጥቂትም ምግብ እንኳ ከአባታቸው ፍቅር ለጸሎት መልስ ሆኖ ሲመጣ፣ ልዩ ጣዕም ይኖረዋል።

ሙሉ ማብራሪያውን ያንብቡ ድምፅ፣ ሙሉ ማብራሪያ እና ከመስመር ውጭ ንባብ

ትርጉሞች8 · 6

AMHEVG ጻድቃንና ጠቢባን ሥራዎቻቸውም በእግዚአብሔር እጅ እንደ ሆኑ፥ ይህን ሁሉ እመረምር ዘንድ በልቤ አኖርሁ፤ ፍቅር ወይም ጥል ቢሆን ሰው አያውቅም ሁሉ ወደ ፊታቸው ነው። አማርኛ ENGNIV So I reflected on all this and concluded that the righteous and the wise and what they do are in God's hands, but no ma… English BCV ብዛዕባ እዙይ ኣፀቢቐ ሓሰብኩ። ፃድቃንን ጥበበኛታትን፥ ኵሉ ዝሰርሕዎን፥ ኣብ ኢድ እግዚኣብሄር ከም ዝኾነ፥ ነዝ ዅሉ ኽምርምር ብልበይ ሓሰብኩ፤ ፍቕሪ ወይ ፅልኢ ይኹን ሰብ ኣይፈልጥን፤ ኵሉ… ትግርኛ GAZBIB Ani wanta kana hundumaa garaatti qabadheera, qoreeras; namoonni qajeelonnii fi ogeeyyiin hojii isaanii wajjin harka Waa… Afaan Oromoo BCV GIZ ከመ ጻድቃን ወጠበብት ወምግባሮሙ ውስተ እደ እግዚአብሔር ፍቅረ ወጸልአ አልቦ ዘያአምር ሰብእ ኵሉ ቅድመ ገጾሙ። giz GAZGAZ Ani wanta kana hundumaa garaatti qabadheera, qoreeras; namoonni qajeelonnii fi ogeeyyiin hojii isaanii wajjin harka Waa… Afaan Oromoo BCV aksum ብዛዕባ እዙይ ኣፀቢቐ ሓሰብኩ። ፃድቃንን ጥበበኛታትን፥ ኵሉ ዝሰርሕዎን፥ ኣብ ኢድ እግዚኣብሄር ከም ዝኾነ፥ ነዝ ዅሉ ኽምርምር ብልበይ ሓሰብኩ፤ ፍቕሪ ወይ ፅልኢ ይኹን ሰብ ኣይፈልጥን፤ ኵሉ… ትግርኛ SWAHSUV Na kwa ajili ya hayo yote, nikatia moyo wangu katika kuyatafutatafuta haya; ya kuwa wenye haki, na wenye hekima, pamoja… Kiswahili