ትንቢተ ዳንኤል 10

AMHEVGአማርኛ21 ጥቅሶች3:46 አዳምጥ
አዳምጥ 3:46 · መደበኛ · አስደናቂ በBiblight ይክፈቱ

1በፋርስ ንጉሥ በቂሮስ በሦስተኛው ዓመት ብልጣሶር ለተባለው ለዳንኤል ነገር ተገለጠለት፤ ነገሩም እውነት ነበረ፥ እርሱም ታላቅ ጦርነት ነው፤ ነገሩንም አስተዋለ፥ በራእዩም ውስጥ ማስተዋል ተሰጠው።

2በዚያም ወራት እኔ ዳንኤል ሦስት ሳምንት ሙሉ ሳዝን ነበርሁ።

3ማለፊያ እንጀራም አልበላሁም፥ ሥጋና ጠጅም በአፌ አልገባም፥ ሦስቱም ሳምንት እስኪፈጸም ድረስ ዘይት አልተቀባሁም።

4ከመጀመሪያውም ወር በሀያ አራተኛው ቀን ጤግሮስ በተባለው በታላቁ ወንዝ አጠገብ ሳለሁ፥ ዓይኔን አነሣሁ፥

5እነሆም፥ በፍታ የለበሰውን ጥሩም የአፌዝን ወርቅ በወገቡ ላይ የታጠቀውን ሰው አየሁ።

6አካሉም እንደ ቢረሌ ይመስል ነበር፥ ፊቱም እንደ መብረቅ ምስያ ነበረ፥ ዓይኖቹም እንደሚንበለበል ፋና፥ ክንዶቹና እግሮቹም እንደ ጋለ ናስ፥ የቃሉም ድምፅ እንደ ብዙ ሕዝብ ድምፅ ነበረ።

7እኔም ዳንኤል ብቻዬን ራእዩን አየሁ፥ ከእኔ ጋር የነበሩ ሰዎች ግን ራእዩን አላዩም፤ ነገር ግን ጽኑ መንቀጥቀጥ ወደቀባቸው፥ ሊሸሸጉም ሸሹ።

8እኔም ብቻዬን ቀረሁ ይህንም ታላቅ ራእይ አየሁ፤ ኃይልም አልቀረልኝም፥ ደም ግባቴም ወደ ማሸብሸብ ተለወጠብኝ፥ ኃይልም አጣሁ።

9የቃሉንም ድምፅ ሰማሁ፤ የቃሉንም ድምፅ በሰማሁ ጊዜ ደንግጬ በምድር ላይ በግምባሬ ተደፋሁ።

10እነሆም፥ አንዲት እጅ ዳሰሰችኝ፥ በጕልበቴና በእጄም አቆመችኝ።

11እርሱም፦ “እጅግ የተወደድህ ሰው ዳንኤል ሆይ፥ እኔ ዛሬ ወደ አንተ ተልኬአለሁና የምነግርህን ቃል አስተውል፥ ቀጥ ብለህም ቁም፡” አለኝ። ይህንም ቃል ባለኝ ጊዜ እየተንቀጠቀጥሁ ቆምሁ።

12እርሱም እንዲህ አለኝ፦ “ዳንኤል ሆይ፥ አትፍራ፤ ልብህ ያስተውል ዘንድ፥ ሰውነትህም በአምላክህ ፊት ይዋረድ ዘንድ ካደረግህበት ከመጀመሪያው ቀን ጀምሮ ቃልህ ተሰምቶአል፤ እኔም ስለ ቃልህ መጥቻለሁ።

13የፋርስ መንግሥት አለቃ ግን ሀያ አንድ ቀን ተቋቋመኝ፤ እነሆም፥ ከዋነኞቹ አለቆች አንዱ ሚካኤል ሊረዳኝ መጣ፤ እኔም ከፋርስ ነገሥታት ጋር በዚያ ተውሁት።

14ራእዩም ገና ለብዙ ዘመን ነውና በኋለኛው ዘመን ለሕዝብህ የሚሆነውን አስታውቅህ ዘንድ አሁን መጥቻለሁ።”

15ይህንም ቃል በተናገረኝ ጊዜ ፊቴን ወደ ምድር አቀረቀርሁ፥ ዲዳም ሆንሁ።

16እነሆም፥ የሰው ልጅ የሚመስል ከንፈሬን ዳሰሰኝ፤ የዚያን ጊዜም አፌን ከፍቼ ተናገርሁ በፊቴም ቆሞ የነበረውን፦ “ጌታዬ ሆይ፥ ከራእዩ የተነሣ ሕመሜ መጣብኝ፥ ኃይልም አጣሁ።

17ይህ የጌታዬ ባሪያ ከዚህ ከጌታዬ ጋር ይናገር ዘንድ እንዴት ይችላል? አሁንም ኃይል አጣሁ፥ እስትንፋስም አልቀረልኝም፡” አልሁት።

18ደግሞ ሰው የሚመስል ዳሰሰኝ፥ አበረታኝም።

19እርሱም፦ “እጅግ የተወደድህ ሰው ሆይ፥ አትፍራ፤ ሰላም ለአንተ ይሁን፤ በርታ፥ ጽና፡” አለኝ። በተናገረኝም ጊዜ በረታሁና፦ “አበርትተኸኛልና ጌታዬ ይናገር፡” አልሁ።

20እርሱም እንዲህ አለኝ፦ “ወደ አንተ የመጣሁት ስለ ምን እንደ ሆነ፥ ታውቃለህን? አሁንም ከፋርስ አለቃ ጋር እዋጋ ዘንድ እመለሳለሁ፤ እኔም ስወጣ፥ እነሆ፤ የግሪክ አለቃ ይመጣል።

21ነገር ግን በእውነት ጽሑፍ የተጻፈውን እነግርሃለሁ፤ በዚህም ነገር ከአለቃችሁ ከሚካኤል በቀር ማንም የሚያጸናኝ የለም።”

ማብራሪያ

ምዕራፍ ፲፥፩-፱።

ይህ ምዕራፍ የዳንኤልን የመጨረሻውን ራእይ መጀመሪያ ያትታል፤ ይህም እስከ መጽሐፉ መጨረሻ ድረስ ይቀጥላል። ሁሉም ነገር እስኪፈጸም ድረስ ጊዜው ረጅም ይሆናል፤ ከብዙውም ክፍል ገና ያልተፈጸመ አለ። ክርስቶስ በክብር መልክ ለዳንኤል ተገለጠ፤ ይህ ደግሞ እርሱን ከፍ አድርገንና በክብር እንድናስበው ሊያነሳሳን ይገባል። ስለ እኛና ስለ ድነታችን ያሳየውን ታላቅ ትሕትና እናድንቅ። በዳንኤል ውስጥም ኃይል አልቀረለትም። ከሁሉ የሚበልጡና ታላላቅ የሆኑ ሰዎች እንኳ የመለኮታዊውን ክብር ሙሉ ገጽታ መሸከም አይችሉም፤ ማንም ሰው አይቶት ሊኖር አይችልምና። የከበሩ ቅዱሳን ግን ክርስቶስን እንዳለ ያዩታል፣ እይታውንም መሸከም ይችላሉ። ክርስቶስ በኃጢአት ጥፋተኝነት ስሜት ውስጥ ላሉት ምን ያህል አስፈሪ ሆኖ ቢታይም፣ መንፈሳቸውን ለማረጋጋት በቃሉ ውስጥ በቂ የሆነ ነገር አለ።

10:10-21 ከእግዚአብሔር ጋር ኅብረት በምናደርግበት ጊዜ ሁሉ፣ በእኛና በቅዱሱ አምላክ መካከል ስላለው ወሰን የለሽ ርቀት ተገቢውን ግንዛቤ ሊኖረን ይገባል።

ሙሉ ማብራሪያውን ያንብቡ ድምፅ፣ ሙሉ ማብራሪያ እና ከመስመር ውጭ ንባብ

ትርጉሞች8 · 6

ENGNIV In the third year of Cyrus king of Persia, a revelation was given to Daniel (who was called Belteshazzar). Its message … English BCV ቂሮስ ኣብ ፋርስ ምስ ነገሰ ኣብታ ሳልሰይቲ ዓመቱ፥ ብልጣሶር ንዝተብሃለ ዳንኤል ራእይ ተርኣዮ። እቲ ነገር ሓቂ እዩ፤ ንሱውን ዓብዪ ውግእ ዝገልፅ ነበረ። ነቲ መልእኽቲ ምእንቲ ኽርዳእ፥ ብ… ትግርኛ GAZBIB Qiiros biyya Faaresitti mootii ta'ee waggaa sadaffaatti, dubbiin tokko Daani'el isa Belxishaazaar jedhamee moggaafamett… Afaan Oromoo BCV GIZ አመ ዐሠርቱ ዓመተ መንግሥቱ ለቂሮስ ንጉሠ ፋርስ ተከሥተ ቃለ እግዚኣብሔር ለዳንኤል ወተሰምየ ስሙ በልጣሳር ወእሙን ነገሩ ወኀይል ዓቢይ ተውህበ ሎቱ በውስተ ራእይ። giz GAZGAZ Qiiros biyya Faaresitti mootii ta'ee waggaa sadaffaatti, dubbiin tokko Daani'el isa Belxishaazaar jedhamee moggaafamett… Afaan Oromoo BCV aksum ቂሮስ ኣብ ፋርስ ምስ ነገሰ ኣብታ ሳልሰይቲ ዓመቱ፥ ብልጣሶር ንዝተብሃለ ዳንኤል ራእይ ተርኣዮ። እቲ ነገር ሓቂ እዩ፤ ንሱውን ዓብዪ ውግእ ዝገልፅ ነበረ። ነቲ መልእኽቲ ምእንቲ ኽርዳእ፥ ብ… ትግርኛ AMHNIV የፋርስ ንጉሥ ቂሮስ በነገሠ በሦስተኛው ዓመት፣ ብልጣሶር ለተባለው ዳንኤል ራእይ ታየው። መልእክቱ እውነት ነው፤ ስለ ታላቅ ጦርነትም የሚገልጽ ነበረ። መልእክቱንም ይገነዘብ ዘንድ በራእይ ማ… አማርኛ SWAHSUV Katika mwaka wa tatu wa Koreshi, mfalme wa Uajemi, Danieli, ambaye jina lake aliitwa Belteshaza, alifunuliwa neno; na n… Kiswahili