ትንቢተ ዳንኤል 10

AMHNIVአማርኛ21 ጥቅሶች4:05 አዳምጥ
አዳምጥ 4:05 · መደበኛ · አስደናቂ በBiblight ይክፈቱ

1የፋርስ ንጉሥ ቂሮስ በነገሠ በሦስተኛው ዓመት፣ ብልጣሶር ለተባለው ዳንኤል ራእይ ታየው። መልእክቱ እውነት ነው፤ ስለ ታላቅ ጦርነትም የሚገልጽ ነበረ። መልእክቱንም ይገነዘብ ዘንድ በራእይ ማስተዋል ተሰጠው።

2በዚያን ጊዜ እኔ ዳንኤል ለሦስት ሳምንት አለቀስሁ፤

3ሦስቱም ሳምንት እስኪፈጸም ድረስ ምርጥ ምግብ አልበላሁም፤ ሥጋም ሆነ የወይን ጠጅ ወደ አፌ አልገባም፤ ቅባትም አልተቀባሁም።

4በመጀመሪያው ወር በሃያ አራተኛው ቀን፣ በታላቁ በጤግሮስ ወንዝ ዳር ቆሜ፣

5ቀና ብዬ ስመለከት፣ በፊቴ በፍታ የለበሰና በወገቡም ላይ ምርጥ የወርቅ ቀበቶ የታጠቀ አንድ ሰው አየሁ።

6አካሉ እንደ ዕንቍ፣ ፊቱ እንደ መብረቅ፣ ዐይኖቹ እንደሚንበለበል ፋና፣ ክንዶቹና እግሮቹ እንደ ጋለ ናስ የሚያብረቀርቁ፣ ድምፁም እንደ ብዙ ሕዝብ ድምፅ ነበር።

7ራእዩን ያየሁት እኔ ዳንኤል ብቻ ነበርሁ፤ ከእኔ ጋር የነበሩት ሰዎች አላዩም፤ ነገር ግን ታላቅ ፍርሀት ስለወደቀባቸው ሸሽተው ተደበቁ።

8ስለዚህ ይህን ታላቅ ራእይ እያየሁ ብቻዬን ቀረሁ፤ ምንም ጒልበት አልነበረኝም፤ መልኬ እጅጉን ገረጣ፤ ኀይልም አጣሁ።

9ከዚያም የቃሉን ድምፅ ሰማሁ፤ የቃሉንም ድምፅ በሰማሁ ጊዜ፣ በግምባሬ በምድር ላይ ተደፍቼ በከባድ እንቅልፍ ተዋጥሁ።

10እነሆም፣ አንድ እጅ ዳሰሰኝ፤ እየተንቀጠቀጥሁም በእጄና በጒልበቴ አቆመኝ፤

11እርሱም፣ “እጅግ የተወደድህ ዳንኤል ሆይ፣ አሁን ወዳንተ ተልኬአለሁና፣ የምነግርህን አስተውል፤ ቀጥ ብለህም ቁም” አለኝ። ይህን ሲለኝም፣ እየተንቀጠቀጥሁ ተነሥቼ ቆምሁ።

12ደግሞም እንዲህ አለኝ፤ “ዳንኤል ሆይ፤ አትፍራ፣ ማስተዋልን ለማግኘትና በአምላክህም ፊት ራስህን ለማዋረድ ከወሰንህበት ከመጀመሪያው ቀን አንሥቶ ቃልህ ተሰምቶአል፤ እኔም የቃልህን መልስ ይዤ መጥቻለሁ።

13ነገር ግን የፋርስ መንግሥት አለቃ ሃያ አንድ ቀን ተቋቋመኝ፤ ከዋነኞቹ አለቆች አንዱ የሆነው ሚካኤል ሊረዳኝ መጣ፤ እኔም በዚያ ከፋርስ ንጉሥ ጋር ተውሁት።

14ራእዩ ሊፈጸም ገና ብዙ ዘመን ስለሚቀረው፣ ወደ ፊት በሕዝብህ ላይ የሚሆነውን ልገልጽልህ አሁን ወደ አንተ መጥቻለሁ።”

15ይህን እየተናገረኝ ሳለ፣ ፊቴን ወደ ምድር አቀረቀርሁ፤ የምናገረውንም አጣሁ።

16ከዚያም የሰው ልጅ የሚመስል ከንፈሮቼን ዳሰሰ፤ እኔም አፌን ከፈትሁ፤ መናገርም ጀመርሁ፤ በፊቴ የነበረውንም እንዲህ አልሁት፤ “ጌታዬ ሆይ፤ ከራእዩ የተነሣ ተሠቃይቻለሁ፤ ኀይልም አጣሁ፤

17ጌታዬ ሆይ፤ ጒልበቴ ከዳኝ፤ መተንፈስም አቅቶኛል፣ እኔ አገልጋይህ ከአንተ ጋር መነጋገር እንዴት እችላለሁ?”

18እንደ ገናም፣ ሰው የሚመስለው ዳሰሰኝ፤ አበረታኝም።

19እርሱም፣ “እጅግ የተወደድህ ሰው ሆይ፤ አትፍራ፤ ሰላም ለአንተ ይሁን፤ በርታ፤ ጽና” አለኝ። እየተናገረኝም ሳለ፣ በረታሁና፣ “ጌታዬ ሆይ፤ አበርትተኸኛልና ተናገር” አልሁት።

20እርሱም እንዲህ አለኝ፤ “ለምን ወደ አንተ እንደ መጣሁ ታውቃለህ? የፋርስን አለቃ ለመውጋት በቶሎ እመለሳለሁ፤ እኔም ስሄድ የግሪክ አለቃ ይመጣል።

21አስቀድሜ ግን በእውነት መጽሐፍ ውስጥ የተጻፈውን እነግርሃለሁ፤ ከእነዚህ አለቆች ጋር ለመዋጋት ከአለቃችሁ ከሚካኤል በስተቀር የሚረዳኝ የለም።

ማብራሪያ

ምዕራፍ ፲፥፩-፱።

ይህ ምዕራፍ የዳንኤልን የመጨረሻውን ራእይ መጀመሪያ ያትታል፤ ይህም እስከ መጽሐፉ መጨረሻ ድረስ ይቀጥላል። ሁሉም ነገር እስኪፈጸም ድረስ ጊዜው ረጅም ይሆናል፤ ከብዙውም ክፍል ገና ያልተፈጸመ አለ። ክርስቶስ በክብር መልክ ለዳንኤል ተገለጠ፤ ይህ ደግሞ እርሱን ከፍ አድርገንና በክብር እንድናስበው ሊያነሳሳን ይገባል። ስለ እኛና ስለ ድነታችን ያሳየውን ታላቅ ትሕትና እናድንቅ። በዳንኤል ውስጥም ኃይል አልቀረለትም። ከሁሉ የሚበልጡና ታላላቅ የሆኑ ሰዎች እንኳ የመለኮታዊውን ክብር ሙሉ ገጽታ መሸከም አይችሉም፤ ማንም ሰው አይቶት ሊኖር አይችልምና። የከበሩ ቅዱሳን ግን ክርስቶስን እንዳለ ያዩታል፣ እይታውንም መሸከም ይችላሉ። ክርስቶስ በኃጢአት ጥፋተኝነት ስሜት ውስጥ ላሉት ምን ያህል አስፈሪ ሆኖ ቢታይም፣ መንፈሳቸውን ለማረጋጋት በቃሉ ውስጥ በቂ የሆነ ነገር አለ።

10:10-21 ከእግዚአብሔር ጋር ኅብረት በምናደርግበት ጊዜ ሁሉ፣ በእኛና በቅዱሱ አምላክ መካከል ስላለው ወሰን የለሽ ርቀት ተገቢውን ግንዛቤ ሊኖረን ይገባል።

ሙሉ ማብራሪያውን ያንብቡ ድምፅ፣ ሙሉ ማብራሪያ እና ከመስመር ውጭ ንባብ

ትርጉሞች8 · 6

AMHEVG በፋርስ ንጉሥ በቂሮስ በሦስተኛው ዓመት ብልጣሶር ለተባለው ለዳንኤል ነገር ተገለጠለት፤ ነገሩም እውነት ነበረ፥ እርሱም ታላቅ ጦርነት ነው፤ ነገሩንም አስተዋለ፥ በራእዩም ውስጥ ማስተዋል ተሰ… አማርኛ ENGNIV In the third year of Cyrus king of Persia, a revelation was given to Daniel (who was called Belteshazzar). Its message … English BCV ቂሮስ ኣብ ፋርስ ምስ ነገሰ ኣብታ ሳልሰይቲ ዓመቱ፥ ብልጣሶር ንዝተብሃለ ዳንኤል ራእይ ተርኣዮ። እቲ ነገር ሓቂ እዩ፤ ንሱውን ዓብዪ ውግእ ዝገልፅ ነበረ። ነቲ መልእኽቲ ምእንቲ ኽርዳእ፥ ብ… ትግርኛ GAZBIB Qiiros biyya Faaresitti mootii ta'ee waggaa sadaffaatti, dubbiin tokko Daani'el isa Belxishaazaar jedhamee moggaafamett… Afaan Oromoo BCV GIZ አመ ዐሠርቱ ዓመተ መንግሥቱ ለቂሮስ ንጉሠ ፋርስ ተከሥተ ቃለ እግዚኣብሔር ለዳንኤል ወተሰምየ ስሙ በልጣሳር ወእሙን ነገሩ ወኀይል ዓቢይ ተውህበ ሎቱ በውስተ ራእይ። giz GAZGAZ Qiiros biyya Faaresitti mootii ta'ee waggaa sadaffaatti, dubbiin tokko Daani'el isa Belxishaazaar jedhamee moggaafamett… Afaan Oromoo BCV aksum ቂሮስ ኣብ ፋርስ ምስ ነገሰ ኣብታ ሳልሰይቲ ዓመቱ፥ ብልጣሶር ንዝተብሃለ ዳንኤል ራእይ ተርኣዮ። እቲ ነገር ሓቂ እዩ፤ ንሱውን ዓብዪ ውግእ ዝገልፅ ነበረ። ነቲ መልእኽቲ ምእንቲ ኽርዳእ፥ ብ… ትግርኛ SWAHSUV Katika mwaka wa tatu wa Koreshi, mfalme wa Uajemi, Danieli, ambaye jina lake aliitwa Belteshaza, alifunuliwa neno; na n… Kiswahili