ትንቢተ አሞጽ 3

AMHNIVአማርኛ15 ጥቅሶች2:55 አዳምጥ
አዳምጥ 2:55 · መደበኛ · አስደናቂ በBiblight ይክፈቱ

1የእስራኤል ልጆች ሆይ፤ እግዚአብሔር በእናንተ ከግብፅ ባወጣሁት ሕዝብ ሁሉ ላይ የተናገረውን ይህን ቃል ስሙ፤

2“ከምድር ወገን ሁሉ፣ እናንተን ብቻ መረጥሁ፤ ስለዚህ ስለ ሠራችሁት ኀጢአት ሁሉ፣ እኔ እቀጣችኋለሁ።”

3በውኑ ሁለት ሰዎች ሳይስማሙ፣ አብረው መጓዝ ይችላሉን?

4አንበሳ የሚበላውን ሳያገኝ፣ በጫካ ውስጥ ይጮኻልን? ምንም ነገርስ ሳይዝ፣ በዋሻው ውስጥ ያገሣልን?

5ወጥመድ ሳይዘረጋ፣ ወፍ በምድር ላይ ይጠመዳልን? የሚይዘው ነገር ሳይኖርስ፣ ወጥመዱ ከምድር ይፈነጠራልን?

6የመለከት ድምፅ በከተማ ውስጥ ሲሰማ፣ ሰዎች አይደነግጡምን? ጥፋትስ በከተማ ላይ ቢደርስ፣ ያደረገው እግዚአብሔር አይደለምን?

7በእውነት ጌታ እግዚአብሔር ምስጢሩን ለአገልጋዮቹ ለነቢያት ሳይገልጥ፣ ምንም ነገር አያደርግም።

8አንበሳ አገሣ፤ የማይፈራ ማን ነው? ጌታ እግዚአብሔር ተናገረ፤ ትንቢት የማይናገር ማን ነው?

9ለአዛጦን ምሽግ፣ ለግብፅም ምሽግ እንዲህ ብላችሁ ዐውጁ፤ “በሰማርያ ተራሮች ላይ ተሰብሰቡ፤ በውስጧ ያለውን ታላቅ ሁከት፣ በሕዝቧም መካከል ያለውን ግፍ እዩ።”

10“ቅሚያንና ዝርፊያን በምሽጋቸው ውስጥ የሚያከማቹ፣ በጎ ነገር ማድረግን አያውቁም፤” ይላል እግዚአብሔር።

11ስለዚህ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ “ጠላት ምድሪቱን ይወራል፤ ምሽጎቻችሁን ያፈርሳል፤ ድንኳኖቻችሁን ይዘርፋል።”

12እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ “እረኛ ከአንበሳ መንጋጋ፣ ሁለት የእግር ዐጥንት ወይም የጆሮ ቍራጭ እንደሚያድን፣ እንዲሁም በሰማርያ በዐልጋቸው ጫፍ ላይ፣ በደማስቆም በምንጣፋቸው ላይ የተቀመጡ፣ እስራኤላውያን ይድናሉ።”

13“ይህን ስሙ፤ በያዕቆብም ቤት ላይ መስክሩ” ይላል ጌታ፣ ሁሉን የሚገዛ አምላክ እግዚአብሔር።

14“እስራኤልን ስለ ኀጢአቷ በምቀጣበት ቀን፣ የቤቴልን መሠዊያዎች አፈርሳለሁ፤ የመሠዊያው ቀንዶች ይቈረጣሉ፤ ወደ ምድርም ይወድቃሉ።

15የክረምቱን ቤት፣ ከበጋው ቤት ጋር እመታለሁ፤ በዝሆን ጥርስ ያጌጡ ቤቶችም ይደመሰሳሉ፤ ታላላቅ አዳራሾችም ይፈርሳሉ፤” ይላል እግዚአብሔር።

ማብራሪያ

3:1-8 የእግዚአብሔር ለእኛ ያደረገው ልዩ ሞገስ ከኃጢአት ካላቀበን፣ ከቅጣት አያድንም። ከእርሱ ጋር ሰላምን አስቀድመው ካልፈለጉ በቀር ከእግዚአብሔር ጋር ህብረት ሊጠብቁ አይችሉም ነበር። ወዳጅነት በሌለበት ህብረት ሊኖር አይችልም። እግዚአብሔርና ሰው ካልተስማሙ በቀር አብረው ሊመላለሱ አይችሉም። ክብሩን ካልፈለግን በቀር ከእርሱ ጋር ልንመላለስ አንችልም። ልዩ በሆነችውና ቅድሳት በሚያደርገው ጸጋ ካልሆነ በውጫዊ መብቶች ላይ አንመካ። በሰው ኃጢአት ላይ የእግዚአብሔር ቃልና መለኮታዊ አሠራር የሚያቀርቧቸው ማስፈራሪያዎች እውነተኛዎች ናቸው፤ እንዲሁም የእግዚአብሔር ፍርዶች ቅርብ መሆናቸውን በርግጥ ያሳያሉ። የላከውን መከራ እግዚአብሔር ስራውን እስኪሰራ ድረስ አያስወግደውም። የኃጢአት ክፋት ከራሳችን የመጣ ነው፤ የእኛም የራሳችን ሥራ ነው።

ሙሉ ማብራሪያውን ያንብቡ ድምፅ፣ ሙሉ ማብራሪያ እና ከመስመር ውጭ ንባብ

ትርጉሞች8 · 6

AMHEVG የእስራኤል ልጆች ሆይ፥ እግዚአብሔር በእናንተ፥ ከግብፅ ምድር ባወጣሁት ወገን ሁሉ ላይ የተናገረውን ይህን ቃል ስሙ፤ አማርኛ ENGNIV Hear this word the Lord has spoken against you, O people of Israel–against the whole family I brought up out of Egypt: English BCV ኣቱም ደቂ እስራኤል፥ ኣነ እግዚኣብሄር ኣብ ልዕሌኹም፥ ኣብ ልዕሊ ዅሉ እቲ ኻብ ምድሪ ግብፂ ዘውፃእኽዎ ወገን ዝተናገርክዎ እዝ ቃል ስምዑ፤ ከምዙይውን በለ፦ ትግርኛ GAZBIB Yommus raajichi, “Yaa namoota Israa'el, dubbii Waaqayyoo isa inni isin irratti, guutummaa saba inni ofii isaatii biyya … Afaan Oromoo BCV GIZ ስምዑ ዘንተ ነገረ ዘይቤለክሙ እግዚአብሔር ቤተ እስራኤል ወኵሉ ሕዝብ ዘአውፃእክዎሙ እምድረ ግብፅ እንዘ ይብል፦ giz GAZGAZ Yommus raajichi, “Yaa namoota Israa'el, dubbii Waaqayyoo isa inni isin irratti, guutummaa saba inni ofii isaatii biyya … Afaan Oromoo BCV aksum ኣቱም ደቂ እስራኤል፥ ኣነ እግዚኣብሄር ኣብ ልዕሌኹም፥ ኣብ ልዕሊ ዅሉ እቲ ኻብ ምድሪ ግብፂ ዘውፃእኽዎ ወገን ዝተናገርክዎ እዝ ቃል ስምዑ፤ ከምዙይውን በለ፦ ትግርኛ SWAHSUV Lisikieni neno hili alilolisema Bwana juu yenu, enyi wana wa Israeli, juu ya jamaa yote niliowapandisha kutoka nchi ya … Kiswahili