ትንቢተ አሞጽ 3

AMHEVGአማርኛ15 ጥቅሶች2:26 አዳምጥ
አዳምጥ 2:26 · መደበኛ · አስደናቂ በBiblight ይክፈቱ

1የእስራኤል ልጆች ሆይ፥ እግዚአብሔር በእናንተ፥ ከግብፅ ምድር ባወጣሁት ወገን ሁሉ ላይ የተናገረውን ይህን ቃል ስሙ፤

2እንዲህም ብሎአል፦ “እኔ ከምድር ወገን ሁሉ እናንተን ብቻችሁን አውቄአችኋለሁ፤ ስለዚህ ስለ ኃጢአታችሁ ሁሉ እበቀላችኋለሁ።

3በውኑ ሁለት ሰዎች ሳይስማሙ በአንድነት ይሄዳሉን?

4ወይስ አንበሳ የሚነጥቀው ነገር ሳያገኝ በጫካ ውስጥ ያገሣልን? ወይስ የአንበሳ ደቦል አንዳች ሳይዝ በመደቡ ሆኖ ይጮኻልን?

5ወይስ ወፍ፥ አጥማጅ ከሌለው፥ በምድር ላይ በወጥመድ ይያዛልን? ወይስ ወስፈንጠር አንዳች ሳይዝ ከምድር ይፈነጠራልን?

6ወይስ በከተማ ውስጥ መለከት ሲነፋ ሕዝቡ አይፈራምን? ወይስ ክፉ ነገር በከተማ ላይ የመጣ እንደ ሆነ ያደረገው እግዚአብሔር አይደለምን?

7በእውነት ጌታ እግዚአብሔር ምሥጢሩን ለባሪያዎቹ ለነቢያት ካልነገረ በቀር ምንም አያደርግም።

8አንበሳው አገሣ፤ የማይፈራ ማን ነው? ጌታ እግዚአብሔር ተናገረ፤ ትንቢት የማይናገር ማን ነው?

9በአዛጦን አዳራሾችና በግብፅ ምድር አዳራሾች አውሩና፦ ‘በሰማርያ ተራሮች ላይ ተሰብሰቡ፥ በውስጥዋም የሆነውን ታላቁን ውካታ፥ በመካከልዋም ያለውን ግፍ ተመልከቱ፡’ በሉ።

10ግፍንና ቅሚያን በአዳራሾቻቸው የሚያከማቹት ቅን ነገርን ያደርጉ ዘንድ አያውቁም፥” ይላል እግዚአብሔር።

11ስለዚህ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “በምድሪቱ ዙሪያ ጠላት ይመጣል፤ ብርታትሽንም ከአንቺ ያወርዳል፥ አዳራሾችሽም ይበዘበዛሉ።”

12እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “እረኛ ከአንበሳ አፍ ሁለት እግርን ወይም የጆሮን ጫፍ እንደሚያድን፥ እንዲሁ በሰማርያ በአልጋ ማዕዘን፥ በደማስቆም በምንጣፍ ላይ የተቀመጡት የእስራኤል ልጆች ይድናሉ።

13ስሙ፥ በያዕቆብም ቤት ላይ መስክሩ፥ ይላል የሠራዊት አምላክ ጌታ እግዚአብሔር።

14እስራኤልን ስለ ኃጢአቱ በምበቀልበት ቀን የቤቴልን መሠዊያዎች ደግሞ እበቀላለሁ፤ የመሠዊያው ቀንዶች ይሰበራሉ፥ ወደ ምድርም ይወድቃሉ።

15የክረምቱንና የበጋውን ቤት እመታለሁ፤ በዝሆንም ጥርስ የተለበጡት ቤቶች ይጠፋሉ፥ ታላላቆችም ቤቶች ይፈርሳሉ፥” ይላል እግዚአብሔር።

ማብራሪያ

3:1-8 የእግዚአብሔር ለእኛ ያደረገው ልዩ ሞገስ ከኃጢአት ካላቀበን፣ ከቅጣት አያድንም። ከእርሱ ጋር ሰላምን አስቀድመው ካልፈለጉ በቀር ከእግዚአብሔር ጋር ህብረት ሊጠብቁ አይችሉም ነበር። ወዳጅነት በሌለበት ህብረት ሊኖር አይችልም። እግዚአብሔርና ሰው ካልተስማሙ በቀር አብረው ሊመላለሱ አይችሉም። ክብሩን ካልፈለግን በቀር ከእርሱ ጋር ልንመላለስ አንችልም። ልዩ በሆነችውና ቅድሳት በሚያደርገው ጸጋ ካልሆነ በውጫዊ መብቶች ላይ አንመካ። በሰው ኃጢአት ላይ የእግዚአብሔር ቃልና መለኮታዊ አሠራር የሚያቀርቧቸው ማስፈራሪያዎች እውነተኛዎች ናቸው፤ እንዲሁም የእግዚአብሔር ፍርዶች ቅርብ መሆናቸውን በርግጥ ያሳያሉ። የላከውን መከራ እግዚአብሔር ስራውን እስኪሰራ ድረስ አያስወግደውም። የኃጢአት ክፋት ከራሳችን የመጣ ነው፤ የእኛም የራሳችን ሥራ ነው።

ሙሉ ማብራሪያውን ያንብቡ ድምፅ፣ ሙሉ ማብራሪያ እና ከመስመር ውጭ ንባብ

ትርጉሞች8 · 6

ENGNIV Hear this word the Lord has spoken against you, O people of Israel–against the whole family I brought up out of Egypt: English BCV ኣቱም ደቂ እስራኤል፥ ኣነ እግዚኣብሄር ኣብ ልዕሌኹም፥ ኣብ ልዕሊ ዅሉ እቲ ኻብ ምድሪ ግብፂ ዘውፃእኽዎ ወገን ዝተናገርክዎ እዝ ቃል ስምዑ፤ ከምዙይውን በለ፦ ትግርኛ GAZBIB Yommus raajichi, “Yaa namoota Israa'el, dubbii Waaqayyoo isa inni isin irratti, guutummaa saba inni ofii isaatii biyya … Afaan Oromoo BCV GIZ ስምዑ ዘንተ ነገረ ዘይቤለክሙ እግዚአብሔር ቤተ እስራኤል ወኵሉ ሕዝብ ዘአውፃእክዎሙ እምድረ ግብፅ እንዘ ይብል፦ giz GAZGAZ Yommus raajichi, “Yaa namoota Israa'el, dubbii Waaqayyoo isa inni isin irratti, guutummaa saba inni ofii isaatii biyya … Afaan Oromoo BCV aksum ኣቱም ደቂ እስራኤል፥ ኣነ እግዚኣብሄር ኣብ ልዕሌኹም፥ ኣብ ልዕሊ ዅሉ እቲ ኻብ ምድሪ ግብፂ ዘውፃእኽዎ ወገን ዝተናገርክዎ እዝ ቃል ስምዑ፤ ከምዙይውን በለ፦ ትግርኛ AMHNIV የእስራኤል ልጆች ሆይ፤ እግዚአብሔር በእናንተ ከግብፅ ባወጣሁት ሕዝብ ሁሉ ላይ የተናገረውን ይህን ቃል ስሙ፤ አማርኛ SWAHSUV Lisikieni neno hili alilolisema Bwana juu yenu, enyi wana wa Israeli, juu ya jamaa yote niliowapandisha kutoka nchi ya … Kiswahili