ትንቢተ አሞጽ 1

AMHNIVአማርኛ15 ጥቅሶች3:23 አዳምጥ
አዳምጥ 3:23 · መደበኛ · አስደናቂ በBiblight ይክፈቱ

1በቴቁሔ ከነበሩት እረኞች መካከል አንዱ የሆነው አሞጽ፣ ዖዝያን የይሁዳ ንጉሥ በነበረ ጊዜ እንዲሁም የዮአስ ልጅ ኢዮርብዓም የእስራኤል ንጉሥ በነበረ ጊዜ፣ ይኸውም የምድር መናወጥ ከመሆኑ ከሁለት ዓመት በፊት ስለ እስራኤል ያየውና የተናገረው ቃል ይህ ነው፤

2እርሱም እንዲህ አለ፤ “እግዚአብሔር ከጽዮን ድምፁን ከፍ አድርጎ ያሰማል፤ ከኢየሩሳሌምም ያንጐደጒዳል፤ የእረኞች ማሰማሪያዎች ደርቀዋል፤ የቀርሜሎስም ዐናት ጠውልጎአል።”

3እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ “ስለ ሦስቱ የደማስቆ ኀጢአት፣ ይልቁንም ስለ አራቱ፣ ቊጣዬን አልመልስም፤ የብረት ጥርስ ባለው ማሄጃ፣ ገለዓድን አሂዳለችና፤

4የወልደ አዴርን ምሽጎች እንዲበላ፣ በአዛሄል ቤት ላይ እሳት እሰዳለሁ።

5የደማስቆን በሮች እሰባብራለሁ፤ በቤት ዔደን በትር የያዘውን፣ በአዌን ሸለቆ ያለውን ንጉሥ እደመስሳለሁ፤ የሶርያም ሕዝብ ተማርኮ ወደ ቂር ይሄዳል” ይላል እግዚአብሔር።

6እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ “ስለ ሦስቱ የጋዛ ኀጢአት፣ ይልቁንም ስለ አራቱ፣ ቊጣዬን አልመልስም፤ ሕዝቡን ሁሉ ማርካ በመውሰድ፣ ለኤዶም ሸጣለችና።

7ምሽጎቿን እንዲበላ፣ በጋዛ ቅጥሮች ላይ እሳት እሰዳለሁ።

8በአስቀሎና በትር የያዘውን፣ የአሸዶድንም ንጉሥ እደመስሳለሁ፤ በፍልስጥኤም ካሉት የመጨረሻው ሰው እስኪሞት ድረስ፣ እጄን በአቃሮን ላይ እዘረጋለሁ፤” ይላል ጌታ እግዚአብሔር።

9እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ “ስለ ሦስቱ የጢሮስ ኀጢአት፣ ይልቁንም ስለ አራቱ፣ ቊጣዬን አልመልስም። የወንድማማችነትን ቃል ኪዳን በማፍረስ፣ ሕዝቡን ሁሉ ማርካ ለኤዶም ሸጣለችና።

10ምሽጎችዋን እንዲበላ፣ በጢሮስ ቅጥሮች ላይ እሳት እሰዳለሁ።”

11እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ “ስለ ሦስቱ የኤዶም ኀጢአት፣ ይልቁንም ስለ አራቱ፣ ቊጣዬን አልመልስም፤ ርኅራኄን በመንፈግ፣ ወንድሙን በሰይፍ አሳዶታልና፤ የቊጣውንም ነበልባል ሳይገድብ፣ መዓቱን ሳያቋርጥ አውርዶበታልና፤

12የባሶራን ምሽጎች እንዲበላ፣ በቴማን ቅጥሮች ላይ እሳት እሰዳለሁ።”

13እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ “ስለ ሦስቱ የአሞን ኀጢአት፣ ይልቁንም ስለ አራቱ፣ ቊጣዬን አልመልስም፤ ድንበሩን ለማስፋት፣ የገለዓድን ነፍሰ ጡር ሴቶች ሆድ ቀዶአልና።

14በጦርነት ቀን በጩኸት ውስጥ፣ በማዕበል ቀን በዐውሎ ነፋስ ውስጥ፣ ምሽጎቿን እንዲበላ፣ በረባት ቅጥሮች ላይ እሳት እሰዳለሁ።

15ንጉሥዋ ከሹማምንቱ ጋር፣ በአንድነት ተማርኮ ይሄዳል፣” ይላል እግዚአብሔር።

ማብራሪያ

፩፥፲፰-፳፩ ብዙ መለኮታዊ ተጽዕኖዎች ይኖራሉ፤ ወንጌልም በፍጥነት እስከ ምድር ዳርቻዎች ድረስ ይሰራጫል። እነዚህ ክስተቶች በጠቃሚ ምልክቶች ስር ተተንብየዋል፤ ሁሉ የተሳሳተ ነገር የሚስተካከልበት ቀን ይመጣል። የዚህ ብዛት ምንጭ በእግዚአብሔር ቤት ውስጥ ነው፣ ዥረቶቹም ከዚያ ይፈስሳሉ። ክርስቶስ ይህ ምንጭ ነው፤ መከራው፣ ጽድቁ፣ እና ጸጋው ያጠራሉ፣ ያድሳሉ፣ እና ፍሬያማ ያደርጋሉ።

ሙሉ ማብራሪያውን ያንብቡ ድምፅ፣ ሙሉ ማብራሪያ እና ከመስመር ውጭ ንባብ

ትርጉሞች8 · 6

AMHEVG በቴቁሔ ከላም ጠባቂዎች መካከል የነበረ አሞጽ በይሁዳ ንጉሥ በዖዝያን ዘመን፥ በእስራኤልም ንጉሥ በዮአስ ልጅ በኢዮርብዓም ዘመን፥ የምድር መናወጥ ከሆነበቱ ከሁለት ዓመት በፊት ስለ እስራኤል… አማርኛ ENGNIV The words of Amos, one of the shepherds of Tekoa–what he saw concerning Israel two years before the earthquake, when Uz… English BCV እዝ ቓል እዙይ፥ ኣሞፅ፥ ሓደ ኻብቶም ጓሶት ቴቁሔ ዝነበረ፥ ብዘመን ኣዛርያስ ንጉስ ይሁዳን፥ ብዘመን ኢዮርብዓም ወዲ ኢዮኣስ ንጉስ እስራኤልን፥ ክልተ ዓመት ቅድሚ ምንቅጥቃጥ ምድርን፥ ብዛዕ… ትግርኛ GAZBIB Kun dubbii Amos, inni warra mandara Teqo'aa keessatti hoolota horsiisan keessaa tokko ture dubbatee dha; inni bara biyy… Afaan Oromoo BCV GIZ ቃለ እግዚአብሔር ኀበ አሞጽ ዘኮነ በአቃሬም ዘቴቁሔ ዘርእየ በእንተ ኢየሩሳሌም በመዋዕለ ዖዝያን ንጉሠ ይሁዳ ወበመዋዕለ ኢያሮብዓም ወልደ ዮአስ ንጉሠ እስራኤል እምቅድመ ክልኤቱ ዓመት ዘድል… giz GAZGAZ Kun dubbii Amos, inni warra mandara Teqo'aa keessatti hoolota horsiisan keessaa tokko ture dubbatee dha; inni bara biyy… Afaan Oromoo BCV aksum እዝ ቓል እዙይ፥ ኣሞፅ፥ ሓደ ኻብቶም ጓሶት ቴቁሔ ዝነበረ፥ ብዘመን ኣዛርያስ ንጉስ ይሁዳን፥ ብዘመን ኢዮርብዓም ወዲ ኢዮኣስ ንጉስ እስራኤልን፥ ክልተ ዓመት ቅድሚ ምንቅጥቃጥ ምድርን፥ ብዛዕ… ትግርኛ SWAHSUV Maneno ya Amosi, aliyekuwa mmoja wa wachungaji wa Tekoa; maono aliyoyaona katika habari za Israeli, siku za Uzia, mfalm… Kiswahili