የሐዋርያት ሥራ 8

AMHNIVአማርኛ40 ጥቅሶች6:56 አዳምጥ
አዳምጥ 6:56 · መደበኛ · አስደናቂ በBiblight ይክፈቱ

1ሳውልም በእስጢፋኖስ መገደል ተስማምቶ ነበር። በዚያ ቀን በኢየሩሳሌም በነበረችው ቤተ ክርስቲያን ላይ ታላቅ ስደት ተነሣ፤ ከሐዋርያትም በስተቀር አማኞች በሙሉ በይሁዳና በሰማርያ አውራጃዎች ሁሉ ተበተኑ፤

2በመንፈሳዊ ነገር የተጉ ሰዎችም እስጢፋኖስን ቀበሩት፤ ደግሞም እጅግ አለቀሱለት።

3ሳውል ግን ቤተ ክርስቲያንን ለማጥፋት ታጥቆ ተነሣ፤ ከቤት ወደ ቤት በመግባትም ወንዶችንና ሴቶችን ጐትቶ እያወጣ ወህኒ ቤት ያስገባቸው ነበር።

4የተበተኑትም በሄዱበት ሁሉ ቃሉን ሰበኩ፤

5ፊልጶስም ወደ አንዲት የሰማርያ ከተማ ወርዶ ክርስቶስን ሰበከላቸው።

6ብዙ ሕዝብም ፊልጶስ የተናገረውን ሲሰሙና ያደረገውንም ታምራዊ ምልክቶች ሲያዩ፣ አንድ ልብ ሆነው ያዳምጡት ነበር።

7ርኵሳን መናፍስትም እየጮኹ ከብዙ ሰዎች ወጡ፤ ብዙ ሽባዎችና አንካሶችም ተፈወሱ፤

8ከዚህ የተነሣም በከተማዪቱ ታላቅ ደስታ ሆነ።

9ነገር ግን ከዚህ ቀደም ሲል በከተማዪቱ ውስጥ እየጠነቈለ የሰማርያን ሰዎች ሁሉ ያስገረመ፣ ሲሞን የሚሉት አንድ ሰው ነበር፤ እርሱም ራሱን እንደ ታላቅ ሰው ይቈጥር ነበር።

10ከታናሽ እስከ ታላቅ ያለው ሰው ሁሉ፣ “ይህ ሰው ‘ታላቁ ኀይል’ በመባል የሚታወቀው መለኮታዊ ኀይል ነው” በማለት ከልብ ያዳምጡት ነበር፤

11ከብዙ ጊዜ ጀምሮ በጥንቈላ ሥራው ስላስገረማቸውም ትኵረት ሰጥተው ይከተሉት ነበር።

12ነገር ግን ፊልጶስ ስለ እግዚአብሔር መንግሥትና ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ ስም የሰበከላቸውን አምነው በመቀበላቸው ወንዶችም ሴቶችም ተጠመቁ፤

13ራሱ ሲሞን እንኳ ሳይቀር አምኖ ተጠመቀ፤ ፊልጶስንም ተከትሎ ሄደ፤ የሚደረገውን ምልክትና ታላቅ ታምራት አይቶም ተገረመ።

14በኢየሩሳሌም የነበሩት ሐዋርያት የሰማርያ ሰዎች የእግዚአብሔርን ቃል መቀበላቸውን በሰሙ ጊዜ፣ ጴጥሮስንና ዮሐንስን ወደ እነርሱ ላኳቸው።

15እነርሱም ሰማርያ በደረሱ ጊዜ መንፈስ ቅዱስን እንዲቀበሉ ለሰማርያ ሰዎች ጸለዩላቸው፤

16ምክንያቱም በዚያን ጊዜ በጌታ ኢየሱስ ስም ተጠምቀው ነበር እንጂ ገና መንፈስ ቅዱስ በአንዳቸውም ላይ አልወረደም ነበር።

17ስለዚህ ጴጥሮስና ዮሐንስ እጃቸውን ጫኑባቸው፤ እነርሱም መንፈስ ቅዱስን ተቀበሉ።

18ሲሞንም ሐዋርያት እጃቸውን በሚጭኑበት ጊዜ መንፈስ ቅዱስ እንደሚሰጥ አይቶ፣ ገንዘብ አመጣላቸውና እንዲህ አላቸው፤

19“እጄን የምጭንበት ሰው ሁሉ መንፈስ ቅዱስን እንዲቀበል ይህን ሥልጣን ለእኔም ስጡኝ።”

20ጴጥሮስ ግን እንዲህ አለው፤ “የእግዚአብሔርን ስጦታ በገንዘብ ለመግዛት አስበሃልና፣ አንተም ገንዘብህም አብራችሁ ጥፉ!

21ልብህ በእግዚአብሔር ፊት ቅን ስላልሆነ፣ አንተ በዚህ አገልግሎት ድርሻ ወይም ዕድል ፈንታ የለህም።

22አሁንም ስለዚህ ክፋትህ ንስሓ ግባ፤ ወደ ጌታም ጸልይ፤ ምናልባት ይህን የልብህን ሐሳብ ይቅር ይልህ ይሆናል፤

23ምክንያቱም በመራራነት ተሞልተህ፣ በዐመፅ ሰንሰለት ተይዘህ አይሃለሁና።”

24ሲሞንም መልሶ፣ “ከተናገራችሁት ምንም ነገር እንዳይደርስብኝ ጌታን ለምኑልኝ” አላቸው።

25ጴጥሮስና ዮሐንስም የጌታን ቃል ከመሰከሩና ገልጠው ከተናገሩ በኋላ፣ በብዙ የሰማርያ መንደሮች ወንጌልን እየሰበኩ፣ ወደ ኢየሩሳሌም ተመለሱ።

26የጌታም መልአክ ፊልጶስን፣ “ተነሥተህ በደቡብ በኩል ከኢየሩሳሌም ወደ ጋዛ በሚያወርደው በምድረ በዳው መንገድ ሂድ” አለው፤

27እርሱም ተነሥቶ ሄደ። እነሆ የኢትዮጵያ ንግሥት የህንደኬ ባለሟልና የሀብት ንብረቷ ሁሉ አዛዥ የሆነ አንድ ኢትዮጵያዊ ጃንደረባ አገኘ። ይህም ሰው ሊሰግድ ወደ ኢየሩሳሌም መጥቶ ነበር።

28ሲመለስም በሠረገላ ተቀምጦ የነቢዩን የኢሳይያስን መጽሐፍ ያነብ ነበር።

29መንፈስም ፊልጶስን፣ “ሂድ፤ ወደዚህ ሠረገላ ቅረብ” አለው።

30ፊልጶስም ፈጥኖ ወደ ሠረገላው ሄደ፤ ጃንደረባውም የነቢዩን የኢሳይያስን መጽሐፍ ሲያነብ ሰምቶ፣ “ለመሆኑ፣ የምታነበውን ታስተውለዋለህን?” አለው።

31ጃንደረባውም፣ “የሚያስረዳኝ ሰው ሳይኖር እንዴት አድርጌ አስተውላለሁ” አለው፤ እርሱም ወደ ሠረገላው ወጥቶ አብሮት እንዲቀመጥ ፊልጶስን ለመነው።

32ጃንደረባው ያነብ የነበረው የመጽሐፍ ክፍል ይህ ነበር፤ “እንደ በግ ወደ መታረድ ተነዳ፤ የበግ ጠቦት በሸላቹ ፊት ዝም እንደሚል፣ እንዲሁ አፉን አልከፈተም።

33ራሱን በማዋረዱም ፍትሕን ተነፈገ፤ ሕይወቱ ከምድር ተወግዳለችና፣ ስለ ትውልዱ ማን ሊናገር ይችላል?”

34ጃንደረባውም መልሶ ፊልጶስን፣ “ነቢዩ ይህን የሚናገረው ስለ ማን ነው? ስለ ራሱ ነው፣ ወይስ ስለ ሌላ ሰው? እባክህ ንገረኝ” አለው።

35ፊልጶስም አፉን ከፈተ፤ ከዚሁም መጽሐፍ ክፍል ጀምሮ ስለ ኢየሱስ ወንጌል ሰበከለት።

36በመጓዝ ላይ ሳሉም ውሃ ካለበት ስፍራ ደረሱ፤ ጃንደረባውም፣ “እነሆ፤ ውሃ እዚህ አለ፤ ታዲያ እንዳልጠመቅ የሚከለክለኝ ምን ነገር አለ?” አለው።

37ፊልጶስም፣ “በፍጹም ልብህ ካመንህ መጠመቅ ትችላለህ” አለው። ጃንደረባውም፣ “ኢየሱስ ክርስቶስ የእግዚአብሔር ልጅ እንደሆነ አምናለሁ” ሲል መለሰለት፤

38ሠረገላውም እንዲቆም አዘዘ። ከዚያም ሁለቱ አብረው ወደ ውሃው ወረዱ፤ ፊልጶስም ጃንደረባውን አጠመቀው።

39ከውሃውም በወጡ ጊዜ፣ የጌታ መንፈስ ፊልጶስን ነጥቆ ወሰደው፤ ጃንደረባውም ከዚህ በኋላ አላየውም፤ ሆኖም ደስ እያለውም ጒዞውን ቀጠለ።

40ከዚያ በኋላ ግን ፊልጶስ በአዛጦን ታየ፤ ቂሳሪያም እስኪደርስ ድረስ፣ በሚያልፍባቸው ከተሞች ሁሉ ወንጌልን ይሰብክ ነበር።

ማብራሪያ

8:1-4 ስደት ከሥራችን ሊያስቆመን ባይገባም፣ ወደ ሌላ ስፍራ እንድንሠራ ሊመራን ይችላል። ጸንቶ የቆመው ምእመን ወደ የትም ቢባረር፣ የወንጌልን እውቀት ይዞ ይሄዳል፤ በየቦታውም የክርስቶስን ውድነት ያስታውቃል። መልካም የማድረግ ቅን ፍላጎት ልብን በሚገዛበት ጊዜ፣ አንድን ሰው ከጠቃሚ አገልግሎት ከሁሉም አጋጣሚዎች ማግለል የማይቻል ሆኖ ይገኛል።

8:5-13

ወንጌል በሰፈነበት መጠን ክፉ መናፍስት፣ በተለይም ርኩሳን መናፍስት ይባረራሉ። ነፍስን የሚዋጉ ሥጋዊ ምኞቶችም ሁሉ እንዲህ ዓይነቶች (ክፉ መንፈሶች) ናቸው። እዚህ ላይ የተጠቀሱት በሽታዎች በተፈጥሮአዊ መንገድ ለመዳን በጣም የሚያስቸግሩ ከመሆናቸውም በላይ የኃጢአትን በሽታ በእጅጉ የሚያሳዩ ናቸው። ትዕቢት፣ ምኞትና ለታላቅነት መሻት ሁልጊዜ ለዓለምም ለቤተ ክርስቲያንም ብዙ ጉዳት አስከትለዋል። ሰዎች ስለ ስምዖን፦ "ይህ ሰው የእግዚአብሔር ታላቅ ኃይል ነው" አሉ። በድንቁርናና በግዴለሽነት የተሞሉ ሰዎች እንዴት እንደሚሳሳቱ ተመልከቱ። ነገር ግን የመለኮታዊ ጸጋ ኃይል እንዴት ብርቱ ነው! በእርሱም (በጸጋው) ወደ ክርስቶስ መጡ፤ እርሱም ራሱ እውነት ነውና! ሰዎች የፊልጶስን ቃል የሰሙ ብቻ ሳይሆኑ፣ የእግዚአብሔር እንጂ የሰዎች አለመሆኑን ሙሉ በሙሉ አመኑ፤ በዚያም እንዲመሩ ራሳቸውን ሰጡ። ክፉ ሰዎችም እንኳን፣ ልባቸው አሁንም ስግብግብነትን የሚከተል ሰዎችም፣ እንደ ሕዝቡ ወደ እግዚአብሔር ሊቀርቡ ይችላሉ፤ ለተወሰነ ጊዜም ከእነርሱ ጋር ሊቀጥሉ ይችላሉ። ብዙዎች የመለኮታዊ እውነቶችን ማረጋገጫዎች ያደንቃሉ፤ የእነርሱን ኃይል ግን ፈጽሞ አይለማመዱም። የተሰበከው ወንጌል በነፍስ ላይ የተለመደ ተግባር ሊኖረው ይችላል፤ የውስጥ ቅድስናን ግን ፈጽሞ ባላመጣበት ቦታ። ወንጌልን እናምናለን የሚሉ ሁሉ በመዳን የተቀየሩ አይደሉም።

8:14-25 መንፈስ ቅዱስ በጰንጠቆስጤ ዕለት በመውረዱ ያመጣቸውን ያልተለመዱ ኃይላት ገና ከእነዚህ አዲስ አማኞች በአንዳቸውም ላይ አልወረደም ነበር። ስለ መንፈሳዊ ደህንነታቸው ለምንጨነቅላቸው ሰዎች ሁሉ የመንፈስ ቅዱስን አድሳሽ ጸጋዎች እንዲሰጣቸው እግዚአብሔርን ስንጸልይ ከዚህ ምሳሌ መበረታታት እንችላለን፤ ይህም ሁሉንም በረከቶች ያካትታልና። ማንም ሰው እጁን በመጫን መንፈስ ቅዱስን ሊሰጥ አይችልም፤ ነገር ግን የምንጸልይላቸውን ለማስተማር የተቻለንን ሁሉ ጥረት ማድረግ ይገባናል።

ሙሉ ማብራሪያውን ያንብቡ ድምፅ፣ ሙሉ ማብራሪያ እና ከመስመር ውጭ ንባብ

ትርጉሞች8 · 6

AMHEVG ሳውልም በእርሱ መገደል ተስማምቶ ነበር። በዚያን ቀንም በኢየሩሳሌም ባለች ቤተ ክርስቲያን ላይ ታላቅ ስደት ሆነ፤ ሁሉም ከሐዋርያትም በቀር ወደ ይሁዳና ወደ ሰማርያ አገሮች ተበተኑ። አማርኛ ENGNIV And Saul was there, giving approval to his death. On that day a great persecution broke out against the church at Jerus… English BCV ሳውል ድማ ኣብ ቅትለት እስጢፋኖስ ተሓባቢሩ ነበረ። በታ መዓልቲ እቲኣ ኸዓ፥ ኣብ ልዕሊ እታ ኣብ ኢየሩሳሌም ዝነበረት ቤተ ክርስቲያን ብርቱዕ ስደት ኮነ። እንትርፊ ሃዋርያት፥ ኵሎም ናብ ሃ… ትግርኛ GAZBIB Saa'ol ajjeefamuu Isxifaanositti walii galee ture. Kana irratti immoo guyyuma sana waldaa amantoota Yerusaalem keessa j… Afaan Oromoo BCV GIZ ወሳውልኒ ኮነ ኅቡረ ውስተ ቀቲለ ዚኣሁ። ወውእተ አሚረ ኮነ ዐቢይ ምንዳቤ ወሁከት በቤተ ክርስቲያን ዘኢየሩሳሌም፣ ወተዘርዉ ኵሎሙ ውስተ ኵሉ በሐውርተ ይሁዳ፡ ወሰማርያ፡ ወገሊላ፣ ዘእንበለ … giz GAZGAZ Saa'ol ajjeefamuu Isxifaanositti walii galee ture. Kana irratti immoo guyyuma sana waldaa amantoota Yerusaalem keessa j… Afaan Oromoo BCV aksum ሳውል ድማ ኣብ ቅትለት እስጢፋኖስ ተሓባቢሩ ነበረ። በታ መዓልቲ እቲኣ ኸዓ፥ ኣብ ልዕሊ እታ ኣብ ኢየሩሳሌም ዝነበረት ቤተ ክርስቲያን ብርቱዕ ስደት ኮነ። እንትርፊ ሃዋርያት፥ ኵሎም ናብ ሃ… ትግርኛ SWAHSUV Siku ile kukatukia adha kuu ya kanisa lililokuwa katika Yerusalemu; wote wakatawanyika katika nchi ya Uyahudi na Samari… Kiswahili