የሐዋርያት ሥራ 3

AMHEVGአማርኛ25 ጥቅሶች3:40 አዳምጥ
አዳምጥ 3:40 · መደበኛ · አስደናቂ በBiblight ይክፈቱ

1ጴጥሮስና ዮሐንስም በጸሎት ጊዜ በዘጠኝ ሰዓት ወደ መቅደስ ይወጡ ነበር።

2ወደ መቅደስም ከሚገቡት ምጽዋት ይለምን ዘንድ፥ ሰዎች ተሸክመው መልካም በሚሉአት በመቅደስ ደጅ በየቀኑ ያስቀምጡት የነበሩ ከእናቱ ማኅፀን ጀምሮ አንካሳ የሆነ አንድ ሰው ነበረ።

3እርሱም ጴጥሮስና ዮሐንስ ወደ መቅደስ ሊገቡ እንዳላቸው ባየ ጊዜ፥ ምጽዋትን ለመናቸው።

4ጴጥሮስም ከዮሐንስ ጋር ትኵር ብሎ ወደ እርሱ ተመልክቶ፦ “ወደ እኛ ተመልከት” አለው።

5እርሱም አንድ ነገር ከእነርሱ እንዲቀበል ሲጠብቅ ወደ እነርሱ ተመለከተ።

6ጴጥሮስ ግን፦ “ብርና ወርቅ የለኝም፤ ይህን ያለኝን ግን እሰጥሃለሁ፤ በናዝሬቱ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም ተነሣና ተመላለስ፡” አለው።

7በቀኝ እጁም ይዞ አስነሣው፤ በዚያን ጊዜም እግሩና ቍርጭምጭምቱ ጸና፥

8ወደ ላይ ዘሎም ቆመ፥ ይመላለስም ጀመር፤ እየተመላለሰም እየዘለለም እግዚአብሔርንም እያመሰገነ ከእነርሱ ጋር ወደ መቅደስ ገባ።

9ሕዝቡም ሁሉ እግዚአብሔርን እያመሰገነ ሲመላለስ አዩት፤

10መልካምም በሚሉአት በመቅደስ ደጅ ስለ ምጽዋት ተቀምጦ የነበረው እርሱ እንደ ሆነ አወቁት፤ በእርሱም ከሆነው የተነሣ መደነቅና መገረም ሞላባቸው።

11እርሱም ጴጥሮስንና ዮሐንስን ይዞ ሳለ፥ ሕዝቡ ሁሉ እየተደነቁ የሰሎሞን ደጅ መመላለሻ በሚባለው አብረው ወደ እነርሱ ሮጡ።

12ጴጥሮስም አይቶ ለሕዝቡ እንዲህ ሲል መለሰ፦ “የእስራኤል ሰዎች ሆይ፥ በዚህ ስለ ምን ትደነቃላችሁ? ወይስ በገዛ ኃይላችን ወይስ እግዚአብሔርን በመፍራታችን ይህ ይመላለስ ዘንድ እንዳደረግነው ስለ ምን ትኵር ብላችሁ ታዩናላችሁ?

13የአብርሀምና የይስሐቅ የያዕቆብም አምላክ፥ የአባቶቻችን አምላክ፥ እናንተ አሳልፋችሁ የሰጣችሁትንና ሊፈታው ቈርጦ ሳለ በጲላጦስ ፊት የካዳችሁትን ብላቴናውን ኢየሱስን አከበረው።

14እናንተ ግን ቅዱሱን ጻድቁንም ክዳችሁ ነፍሰ ገዳዩን ሰው ይሰጣችሁ ዘንድ ለመናችሁ፥

15የሕይወትንም ራስ ገደላችሁት፤ እርሱን ግን እግዚአብሔር ከሙታን አስነሣው፥ ለዚህም ነገር እኛ ምስክሮች ነን።

16በስሙም በማመን ይህን የምታዩትንና የምታውቁትን የእርሱ ስም አጸናው፥ በእርሱም በኩል የሆነው እምነት በሁላችሁ ፊት ይህን ፍጹም ጤና ሰጠው።

17“አሁንም፥ ወንድሞቼ ሆይ፥ እናንተ እንደ አለቆቻችሁ ደግሞ ባለማወቅ እንዳደረጋችሁት አውቄአለሁ፤

18እግዚአብሔር ግን ክርስቶስ መከራ እንዲቀበል አስቀድሞ በነቢያት ሁሉ አፍ የተናገረውን እንዲሁ ፈጸመው።

19እንግዲህ ከጌታ ፊት የመጽናናት ዘመን እንድትመጣላችሁ አስቀድሞም ለእናንተ የመረጠውን ኢየሱስ ክርስቶስን እንዲልክላችሁ፥ ኃጢአታችሁ ይደመሰስ ዘንድ ንስሐ ግቡ ተመለሱም።

21እግዚአብሔር ከጥንት ጀምሮ በቅዱሳን ነቢያቱ አፍ የተናገረው፥ ነገር ሁሉ እስከሚታደስበት ዘመን ድረስ ሰማይ ይቀበለው ዘንድ ይገባልና።

22ሙሴም ለአባቶች፦ ‘ጌታ አምላክ እኔን እንዳስነሣኝ ነቢይን ከወንድሞቻችሁ ያስነሣላችኋል፤ በሚነግራችሁ ሁሉ እርሱን ስሙት።

23ያንም ነቢይ የማትሰማው ነፍስ ሁሉ ከሕዝብ ተለይታ ትጠፋለች፡’ አለ።

24“ሁለተኛም ከሳሙኤል ጀምሮ ከእርሱም በኋላ የተናገሩት ነቢያት ሁሉ ደግሞ ስለዚህ ወራት ተናገሩ።

25እናንተ የነቢያት ልጆችና እግዚአብሔር ለአብርሃም፦ ‘በዘርህ የምድር ወገኖች ሁሉ ይባረካሉ፥’ ብሎ፥ ከአባቶቻችን ጋር ያደረገው የኪዳን ልጆች ናችሁ።

26ለእናንተ አስቀድሞ እግዚአብሔር ብላቴናውን አስነሥቶ፥ እያንዳንዳችሁን ከክፋታችሁ እየመለሰ ይባርካችሁ ዘንድ፥ ሰደደው።”

ማብራሪያ

3:1-11 ሐዋርያትና የመጀመሪያዎቹ አማኞች በጸሎት ሰዓት በቤተ መቅደስ አምልኮ ይገኙ ነበር። ጴጥሮስና ዮሐንስ ከተወለደ ጀምሮ ሽባ በሆነውና ከአርባ ዓመት በላይ በሆነው ሰው ላይ ተአምር ሊሰሩ በመለኮታዊ መመሪያ የተመሩ ይመስላል። ጴጥሮስ በናዝሬቱ ኢየሱስ ስም እንዲነሳና እንዲራመድ አዘዘው። እንደዚሁም፣ የሰዎችን ነፍሳት ፈውስ በበጎ ዓላማ ልንሞክር ከሆነ፣ አቅመ ቢስ ኃጢአተኞችን እንዲነሱና በእርሱ ባለ እምነት በቅድስና መንገድ እንዲራመዱ እየጠራን በኢየሱስ ክርስቶስ ስምና ኃይል መውጣት አለብን። የወደቀው ተፈጥሮአችን ሽባ ያደረጋቸውን ችሎታዎች ሁሉ በተመለከተ፣ የናዝሬቱ ኢየሱስ ክርስቶስ ስም ሙሉ በሙሉ ሊያድነን እንደሚችል ለነፍሳችን እንዴት ያለ ጣፋጭ ሃሳብ ነው! መንፈስ ቅዱስ በኃይሉ እዚያ እንድንገባ ሲያደርገን፣ በምን ያህል ቅዱስ ደስታና ፍንደቃ ቅዱስ አደባባዮችን እንረግጣለን!

3:12-18 በተአምራት አሰራር ውስጥ ያለውን ልዩነት አስተውሉ። ጌታችን ሁልጊዜ ሁሉን የሚችል ስልጣን እንዳለው አድርጎ ይናገር ነበር፤ በመለኮታዊ ተአምራቱ የተሰጠውን ታላቅ ክብር ለመቀበልም ፈጽሞ አላቅማማም። ነገር ግን ሐዋርያት ሁሉን ለጌታቸው አመለከቱ፤ እርሱን የማይገባቸው መሳሪያዎቹ ሆነው ከማገልገል በቀር ምንም ክብር ለመቀበል እንቢ አሉ። ይህ ደግሞ ኢየሱስ ከአብ ጋር አንድ እንደሆነና ከእርሱም ጋር እኩል መሆኑን ያሳያል። ሐዋርያት ግን እነርሱ ደካማ፣ ኃጢአተኛ ሰዎች እንደሆኑ፣ በሁሉ ነገርም የፈውሱን ስራ ሙሉ በሙሉ ባደረገው በኢየሱስ ላይ ጥገኛ እንደሆኑ ያውቁ ነበር። ጠቃሚ ሰዎች እጅግ ትሑቶች መሆን አለባቸው።

ሙሉ ማብራሪያውን ያንብቡ ድምፅ፣ ሙሉ ማብራሪያ እና ከመስመር ውጭ ንባብ

ትርጉሞች8 · 6