የሐዋርያት ሥራ 27

AMHNIVአማርኛ44 ጥቅሶች7:54 አዳምጥ
አዳምጥ 7:54 · መደበኛ · አስደናቂ በBiblight ይክፈቱ

1ወደ ኢጣሊያ እንድንሄድ በተወሰነ ጊዜ፣ ጳውሎስንና ሌሎቹን እስረኞች የንጉሠ ነገሥቱ ክፍለ ጦር አባል ለሆነው፣ ዩልዮስ ለተባለ የመቶ አለቃ አስረከቧቸው።

2ከአድራሚጢስ ተነሥቶ በእስያ አውራጃ ባሕር ዳርቻ ላይ ወዳሉት ወደቦች በሚሄደው መርከብ ተሳፍረን የባሕር ጒዞ ጀመርን፤ በተሰሎንቄ ይኖር የነበረው የመቄዶንያ ሰው፣ አርስጥሮኮስም ከእኛ ጋር ነበረ።

3በሚቀጥለው ቀን ሲዶና ደረስን፤ ዩልዮስም ለጳውሎስ ደግነት በማሳየት ወደ ወዳጆቹ ሄዶ ርዳታ እንዲቀበል ፈቀደለት።

4ከዚያም ተነሥተን በባሕር ተጓዝን፤ ነፋስ ከፊት ለፊት ስለገጠመን፣ የቆጵሮስን ደሴት ተገን አድርገን ዐለፍን።

5በኪልቅያና በጵንፍልያ ዳርቻ ያለውን ባሕር ከተሻገርን በኋላ በሉቅያ አገር ሙራ የተባለ ቦታ ደረስን።

6ከዚያም የመቶ አለቃው ወደ ኢጣሊያ የሚሄድ የእስክንድርያ መርከብ አግኝቶ አሳፈረን።

7ብዙ ቀን በዝግታ እየተጓዝን ቀኒዶስ አካባቢ በጭንቅ ደረስን፤ ነፋሱም ወደ ፊት እንዳንሄድ በከለከለን ጊዜ፣ በሰልሙና አጠገብ አድርገን በቀርጤስ ተተግነን ሄድን፤

8ጥግ ጥጉንም ይዘን፣ በላሲያ ከተማ አጠገብ ወዳለው፣ ‘መልካም ወደብ’ ወደተባለ ስፍራ በጭንቅ ደረስን።

9ብዙ ጊዜ ባክኖ፤ የጾሙ ጊዜ ስላለፈ በመርከብ መጓዙ አደገኛ ሆኖ ነበርና ጳውሎስ፣

10“እናንት ሰዎች፤ ጒዞው አደገኛ እንደሚሆን፣ በመርከቡና በጭነቱ እንዲሁም በእኛ በራሳችን ላይ እንኳ ትልቅ ጒዳት እንደሚደርስ ይታየኛል” ብሎ አስጠነቀቃቸው።

11የመቶ አለቃው ግን ከጳውሎስ ምክር ይልቅ የመርከቡ መሪና የመርከቡ ባለቤት ያሉትን ይሰማ ነበር።

12ክረምቱንም በዚያ ለማሳለፍ ወደቡ አመቺ ስላልነበረ፣ አብዛኛዎቹ ፍንቄ ወደተባለው ወደብ ደርሰው በዚያ ለመክረም ተስፋ በማድረግ ጒዞአችንን እንድንቀጥል ውሳኔ አስተላለፉ፤ ወደቡም በቀርጤስ ደቡብ ምዕራብና ሰሜን ምዕራብ ትይዩ የሚገኝ ነበር።

13መጠነኛ የደቡብ ነፋስ በነፈሰ ጊዜም እንዳሰቡት የሆነላቸው መስሎአቸው መልሕቁን ነቅለው፣ የቀርጤስን ዳርቻ በመያዝ ተጓዙ።

14ብዙም ሳይቈይ ግን፣ ‘ሰሜናዊ ምሥራቅ’ የሚሉት ኀይለኛ ዐውሎ ነፋስ ከደሴቲቱ ተነሥቶ ቍልቍል መጣባቸው።

15መርከቢቱም በማዕበሉ ስለ ተያዘች፣ ወደ ነፋሱ ልትገፋ አልቻለችም፤ ስለዚህ መንገድ ለቀን በነፋሱ ተነዳን።

16ቄዳ የተባለችውን ትንሽ ደሴት ተገን አድርገን በማለፍ፣ የመርከቧን ሕይወት አድን ጀልባ በብዙ ድካም ለማትረፍ ቻልን፤

17ጀልባዋንም ወደ ላይ ጐትተው ካወጧት በኋላ መርከቧ እንዳትፈራርስ ዙሪያዋን በገመድ ጠምጥመው አሰሯት፤ ስርቲስ ከተባለው አሸዋማ ደለል ጋር ሄደው እንዳይላተሙ ስለ ፈሩም፣ የመርከቧን ሸራ አውርደው እንዲሁ በዘፈቀደ እንድትነዳ አደረጉ።

18ማዕበሉም ክፉኛ ስላንገላታን፣ በማግስቱ ጭነቱን እያነሡ ወደ ባሕር ይጥሉ ጀመር፤

19በሦስተኛውም ቀን፣ የመርከቧን ሸራ ማውጫና ማውረጃ መሣሪያ በገዛ እጃቸው ነቃቅለው ወደ ባሕር ጣሉት።

20ብዙ ቀን፣ ፀሓይንም ከዋክብትንም ማየት ስላልተቻለና ነፋስ ስለ በረታብን፣ ለመትረፍ የነበረን ተስፋ ሁሉ ተሟጠጠ።

21ሰዎቹ እህል ሳይቀምሱ ብዙ ቀን ከቈዩ በኋላ፣ ጳውሎስ በመካከላቸው ቆሞ እንዲህ አለ፤ “እናንት ሰዎች ሆይ፤ የነገርኋችሁን ሰምታችሁ ቢሆን ኖሮ፣ ከቀርጤስ ባልተነሣችሁና ይህ ጒዳትና ጥፋት ባልደረሰባችሁ ነበር።

22አሁንም ቢሆን አይዟችሁ መርከቧ እንጂ ከእናንተ አንዲት ነፍስ እንኳ አትጠፋምና።

23በትላንትናዋ ሌሊት፣ የእርሱ የሆንሁትና የማመልከው እግዚአብሔር የላከው መልአክ በአጠገቤ ቆሞ፣

24‘ጳውሎስ ሆይ፤ አትፍራ፤ በቄሳር ፊት መቆም ይገባሃል፤ ከአንተ ጋር የሚጓዙትንም ሰዎች ሕይወት እግዚአብሔር አትርፎልሃል’ አለኝ።

25ስለዚህ፣ እናንት ሰዎች ሆይ፤ አይዞአችሁ እርሱ እንደ ነገረኝ እንደዚያው እንደሚሆን በእግዚአብሔር አምናለሁና።

26ይሁን እንጂ፣ ወደ አንዲት ደሴት በነፋስ ተወስደን እዚያ መጣላችን አይቀርም።”

27በዐሥራ አራተኛው ሌሊት በአድርያ ባሕር ላይ ከወዲያ ወዲህ ስንገላታ፣ እኩለ ሌሊት ገደማ መርከበኞቹ ወደ መሬት የተቃረቡ መሰላቸው፤

28የጥልቀት መለኪያውን ገመድ ወደ ታች ጥለው ሲመለከቱት የውሃው ጥልቀት አርባ ሜትር ያህል ሆኖ አገኙት፤ ከጥቂት ጊዜ በኋላም ደግመው ሲጥሉ ጥልቀቱ፣ ሠላሳ ሜትር ያህል ሆነ።

29ከቋጥኞቹም ጋር እንዳንላተም በመፍራት፣ አራት መልሕቆች ከመርከቡ በስተኋላ ጣሉ፤ ምነው በነጋ እያሉም ይለምኑ ነበር።

30መርከበኞቹም ከመርከቡ በስተ ፊት መልሕቅ የሚጥሉ መስለው፣ ትንሿን ጀልባ በማውረድ ከመርከቧ ሊያመልጡ ሞከሩ።

31ጳውሎስም የመቶ አለቃውንና ወታደሮቹን፣ “እነዚህ ሰዎች መርከቡ ላይ ካልቈዩ እናንተም ልትተርፉ አትችሉም” አላቸው።

32በዚህ ጊዜ ወታደሮቹ ገመዶቹን ቈርጠው ትንሿ ጀልባ ባሕሩ ላይ ተንሳፋ እንድትቀር ለቀቋት።

33ልክ ሊነጋጋ ሲል፣ ጳውሎስ ሁሉም ምግብ እንዲበሉ እንዲህ ሲል ለመናቸው፤ “ዐሥራ አራት ቀን ሙሉ ልባችሁ ተንጠልጥሎ ምንም ሳትቀምሱ ጦማችሁን ሰነበታችሁ፤

34ስለዚህ ስለሚያበረታችሁ አሁን እህል እንድትቀምሱ እለምናችኋላሁ፤ ከእናንተ መካከል ከራሱ ጠጒር አንዲት እንኳ የሚነካበት ማንም የለምና።”

35ይህን ካለ በኋላም፣ እንጀራ ይዞ በሁሉም ፊት እግዚአብሔርን አመሰገነ፤ ቈርሶም ይበላ ጀመር።

36ሁሉም ተበራቱና እንጀራውን ራሳቸው ወስደው በሉ።

37በመርከቡም ላይ በአጠቃላይ ሁለት መቶ ሰባ ስድስት ሰዎች ነበርን።

38በልተውም ከጠገቡ በኋላ ስንዴውን ወደ ባሕር በመጣል የመርከቡን ክብደት አቃለሉ።

39በነጋም ጊዜ፣ ወደ የብስ መቅረባቸውን አላወቁም ነበር፤ ነገር ግን ዳር ዳሩ አሸዋማ የሆነ የባሕር ሰርጥ አይተው፣ ቢቻላቸው መርከቡን ገፍተው ወደዚያ ለማድረስ ወሰኑ።

40ከዚያም መልሕቆቹን ቈርጠው ባሕር ውስጥ ጥለው ሄዱ፤ የመቅዘፊያውንም ገመድ በዚያው ጊዜ ፈቱ፤ የፊተኛውንም ሸራ ለነፋስ ከፍ አድርገው ወደ ባሕሩ ዳርቻ አቀኑ።

41ነገር ግን መርከቡ ከአሸዋ ቍልል ጋር ተላትሞ፤ መሬት ነካ፤ የፊተኛው ክፍሉም አሸዋው ውስጥ ተቀርቅሮ አልነቃነቅ አለ፤ የኋለኛው ክፍሉም በማዕበሉ ክፉኛ ስለ ተመታ ይሰባበር ጀመር።

42ወታደሮቹም ከእስረኞች ማንም ዋኝቶ ለማምለጥ ቢሞክር ለመግደል ተስማሙ።

43የመቶ አለቃው ግን ጳውሎስ እንዲተርፍ ስለ ፈለገ፣ ያሰቡትን እንዳይፈጽሙ ከለከላቸው፤ መዋኘት የሚችሉ ከመርከብ እየዘለሉ አስቀድመው ከባሕሩ ወደ ምድር እንዲወጡ፣

44የተቀሩት ደግሞ በሳንቃዎች ወይም በመርከቡ ስብርባሪ እየተንጠላጠሉ እንዲወጡ አዘዘ። በዚህ መንገድ ሁሉም በደኅና ወደ ምድር ደረሱ።

ማብራሪያ

27:1-11 ጳውሎስ ወደ ሮሜ እንዲሄድ በእግዚአብሔር ምክር ተወስኖ ነበር፤ ይህም በፈስጦስ ምክር ከመወሰኑ በፊት ነበር፤ ምክንያቱም እግዚአብሔር በዚያ ለእርሱ የሚያስፈጽመው ሥራ ነበረውና። የተጓዙበት መንገድና የቆሙባቸው ስፍራዎች እዚህ ተዘርዝረዋል። እግዚአብሔርም በእርሱ ምክንያት ለሚሰቃዩት በእርሱ እንዲታመኑ ያበረታታል፤ ምክንያቱም እነርሱ በጭራሽ ከማይጠብቋቸው ሰዎች ሳይቀር ወዳጅነት እንዲያደርጉላቸው በልባቸው ውስጥ ሊያስገባ ይችላልና። መርከበኞች ነፋሱን በተሻለ መንገድ መጠቀም አለባቸው፤ እኛም በዚህ ዓለም ውቅያኖስ በምናደርገው ጉዞአችን እንዲሁ ማድረግ አለብን። ነፋሳት ተቃራኒ ሲሆኑም ቢሆን በቻልነው መጠን ወደፊት መገስገስ አለብን። በአስቸጋሪ መለኮታዊ አቅርቦቶች ወደኋላ የማይገፉ ብዙዎች በምቹ መለኮታዊ አቅርቦቶች ደግሞ ወደፊት አይገሰግሱም። ብዙ እውነተኛ ክርስቲያኖችም የነፍሳቸውን ጉዳይ አስመልክቶ ቦታቸውን ለማስጠበቅ እጅግ እንደሚቸገሩ ያማርራሉ። እያንዳንዱ ያማረ ወደብ አስተማማኝ ወደብ አይደለም። ብዙዎች ለጥሩ አገልጋዮች ክብር ይሰጣሉ፣ ምክራቸውን ግን አይቀበሉም። ውጤቱ ግን ኃጢአተኞችን የተስፋቸው ከንቱነትና የአድራጎታቸው ሞኝነት እንደሆነ ያሳምናል (ወይም ያስረዳል)።

27:12-20 በዚህ ዓለም ውቅያኖስ ላይ በምቹ ነፋስ ተገፍተው የሚጓዙ ሰዎች፣ ሊያጋጥማቸው የሚችለውን ማዕበል አያውቁም፤ ስለሆነም ዓላማቸውን እንደደረሱ በቀላሉ መገመት የለባቸውም። ወደ ሰማይ እስክንገባ ድረስ ፍጹም ደኅንነትን በፍጹም መጠበቅ የለብንም። ለብዙ ቀናት ፀሐይንና ከዋክብትን አላዩም። የእግዚአብሔር ሕዝብ በመንፈሳዊ ጉዳዮቻቸው አንዳንድ ጊዜ እንዲህ ያለ የሚያሳዝን ሁኔታ ያጋጥማቸዋል፤ በጨለማ ይሄዳሉ፣ ብርሃንም የላቸውም። የዚህ ዓለም ሃብት ምን እንደሆነ ተመልከቱ፦ እንደ በረከት ቢመኝም፣ ሸክም የሚሆንበት ጊዜ ሊመጣ ይችላል፤ በደኅንነት ለመሸከም ከሚችሉት በላይ ከባድ ብቻ ሳይሆን፣ የያዘውንም ሰው ሊያስጠምቅ የሚችል ከባድ ነው። የዚህ ዓለም ልጆች ሕይወታቸውን ለማዳን ሲሉ ገንዘባቸውን አባካኞች ሊሆኑ ይችላሉ፤ ነገር ግን በመንፈሳዊ ተግባራት፣ በምጽዋት ሥራዎችና ስለ ክርስቶስ በመሰቃየት ግን ለመስጠት ይቆጥባሉ። ማንኛውም ሰው ሕይወቱን ከማጣት ይልቅ ገንዘቡን ማጣትን ይመርጣል፤ ነገር ግን ብዙዎች ደግሞ ገንዘባቸውን ከማጣት ይልቅ እምነትንና መልካም ሕሊናን ማጥፋትን ይመርጣሉ። መርከበኞቹ የተጠቀሙባቸው መንገዶች አልተሳኩም፤ ነገር ግን ኃጢአተኞች ራሳቸውን የማዳን ተስፋቸውን ሁሉ ሲጥሉ፣ የእግዚአብሔርን ቃል ለመረዳትና በኢየሱስ ክርስቶስ በኩል ባለው ምሕረቱ ሙሉ በሙሉ ለመታመን ዝግጁ ይሆናሉ።

ሙሉ ማብራሪያውን ያንብቡ ድምፅ፣ ሙሉ ማብራሪያ እና ከመስመር ውጭ ንባብ

ትርጉሞች8 · 6

AMHEVG ወደ ኢጣሊያም በመርከብ እንሄድ ዘንድ በተቈረጠ ጊዜ፥ ጳውሎስንና ሌሎችን እስረኞች ከአውግስጦስ ጭፍራ ለነበረ ዩልዮስ ለሚሉት ለመቶ አለቃ አሳልፈው ሰጡአቸው። አማርኛ ENGNIV When it was decided that we would sail for Italy, Paul and some other prisoners were handed over to a centurion named J… English BCV ናብ ኢጣልያ ብመርከብ ክንከይድ ምስ ተወሰነ፥(ሀ) ንጳውሎስን ንኻልኦት እሱራትን፥ ነቲ ኣብ ሰራዊት ቄሳር ሓለቓ ሚእቲ ዝኾነ ዩልዮስ ዝስሙ ኣመሓላለፍዎም። ትግርኛ GAZBIB Markabaan biyya Ixaaliyaa dhaquu keenyatu murtoo ta'e. Warri kana murtoo godhan, Phaawulosin, jarreen hidhaman tokkos Y… Afaan Oromoo BCV GIZ ወእምዝ አዘዘ ፊስጦስ ይሰድዎ ኀበ ቄሣር ኢጣልያ፤ ወተውህበ ጳውሎስ ወካልኣንኒ ሙቁሓን ምስሌሁ ለብእሲ እምነ ሐራ ሰብስጥያ ዘስሙ ዩልዮስ ሐቤ ምእት። giz GAZGAZ Markabaan biyya Ixaaliyaa dhaquu keenyatu murtoo ta'e. Warri kana murtoo godhan, Phaawulosin, jarreen hidhaman tokkos Y… Afaan Oromoo BCV aksum ናብ ኢጣልያ ብመርከብ ክንከይድ ምስ ተወሰነ፥(ሀ) ንጳውሎስን ንኻልኦት እሱራትን፥ ነቲ ኣብ ሰራዊት ቄሳር ሓለቓ ሚእቲ ዝኾነ ዩልዮስ ዝስሙ ኣመሓላለፍዎም። ትግርኛ SWAHSUV Basi ilipoamriwa tuabiri hata Italia, wakamtia Paulo na wafungwa wengine katika mikono ya akida mmoja, jina lake Yulio,… Kiswahili