የሐዋርያት ሥራ 21

AMHNIVአማርኛ40 ጥቅሶች7:15 አዳምጥ
አዳምጥ 7:15 · መደበኛ · አስደናቂ በBiblight ይክፈቱ

1ከእነርሱ ከተለየን በኋላ ቀጥታ በመርከብ ወደ ቆስ ተጓዝን፤ በማግስቱም ወደ ሩድ፣ ከዚያም ወደ ጳጥራ አመራን።

2በዚያም ወደ ፊንቄ የሚሄድ መርከብ ስላገኘን፣ ተሳፍረን ጒዞአችንን ቀጠልን።

3ቆጵሮስ በታየችን ጊዜ፣ ወደ ግራ ትተናት ዐለፍንና ወደ ሶርያ አመራን፤ መርከባችን ጭነቱን በጢሮስ ማራገፍ ስለ ነበረበት፣ እኛም እዚያው ወረድን።

4ደቀ መዛሙርትንም በዚያ አግኝተን፣ ሰባት ቀን ከእነርሱ ጋር ተቀመጥን። እነርሱም በመንፈስ ሆነው ጳውሎስ ወደ ኢየሩሳሌም እንዳይሄድ ነገሩት።

5የቈይታ ጊዜያችን ባለቀ ጊዜ፣ ትተናቸው ጒዞአችንን ቀጠልን፤ ደቀ መዛሙርቱም ሁሉ ከሚስቶቻቸውና ከልጆቻቸው ጋር እስከ ከተማው ውጭ ድረስ ሸኙን፤ በባሕሩም ዳር ተንበርክከን ጸለይን፤

6ከተሰነባበትንም በኋላ እኛ ወደ መርከቡ ገባን፤ እነርሱም ወደ ቤታቸው ተመለሱ።

7ከጢሮስ ተነሥተን ጒዞአችንን በመቀጠል ጴጤሌማይስ ደረስን፤ ከመርከብ ወርደንም ለወንድሞች ሰላምታ ካቀረብን በኋላ፣ አንድ ቀን ከእነርሱ ጋር ቈየን።

8በማግስቱ ከዚያ ተነሥተን ቂሳርያ ደረስን፤ ከሰባቱ ወንጌላውያን አንዱ በሆነው በፊልጶስ ቤትም ዐረፍን።

9እርሱም ትንቢት የሚናገሩ አራት ደናግል ሴቶች ልጆች ነበሩት።

10በዚያም ብዙ ቀን ከተቀመጥን በኋላ አጋቦስ የተባለ ነቢይ ከይሁዳ ወረደ፤

11ወደ እኛም መጣና የጳውሎስን መታጠቂያ ወሰደ፤ የራሱንም እጅና እግር በማሰር፣ “መንፈስ ቅዱስ፣ ‘በኢየሩሳሌም ያሉ አይሁድ የዚህን መታጠቂያ ባለቤት እንዲህ አድርገው በማሰር ለአሕዛብ አሳልፈው ይሰጡታል’ ይላል” አለ።

12ይህን ስንሰማ እኛና በዚያም የሚኖሩት ጳውሎስ ወደ ኢየሩሳሌም እንዳይሄድ ለመነው።

13ጳውሎስ ግን፣ “ለምን እንዲህ እያለቀሳችሁ ልቤን ታባቡታላችሁ? እኔ መታሰር ቀርቶ ስለ ጌታ ኢየሱስ ስም በኢየሩሳሌም ለመሞት እንኳን ዝግጁ ነኝ” አላቸው።

14ምክራችንን አልቀበል ስላለን፣ “እንግዲህ የጌታ ፈቃድ ይሁን” ብለን ተውነው።

15ከዚህ በኋላ፣ ተዘጋጅተን ወደ ኢየሩሳሌም ወጣን።

16በቂሳርያ ከነበሩት ደቀ መዛሙርትም አንዳንዶቹ ወደ ምናሶን ቤት ይዘውን መጡ፤ እኛም በዚያው ተቀመጥን። ምናሶን የቆጵሮስ ሰው ሲሆን፣ ከመጀመሪያዎቹ ደቀ መዛሙርት አንዱ ነበረ።

17ኢየሩሳሌም በደረስን ጊዜ፣ ወንድሞች በደስታ ተቀበሉን።

18በማግስቱም ጳውሎስና ሌሎቻችንም ያዕቆብን ለማየት ሄድን፤ ሽማግሌዎችም ሁሉ በዚያ ነበሩ።

19ጳውሎስም ሰላምታ ካቀረበላቸው በኋላ፣ እግዚአብሔር በእርሱ አገልግሎት አማካይነት በአሕዛብ መካከል ያደረገውን ሁሉ በዝርዝር አስረዳቸው።

20እነርሱም ይህን ሲሰሙ፣ እግዚአብሔርን አመሰገኑ፤ ጳውሎስንም እንዲህ አሉት፤ “ወንድም ሆይ፤ በብዙ ሺህ የሚቈጠሩ አይሁድ እንዳመኑ ተመልከት፤ ሁሉም ደግሞ ለሙሴ ሕግ የሚቀኑ ናቸው።

21በአሕዛብ መካከል የሚኖሩ አይሁድ ሁሉ ሙሴን እንዲተዉና ልጆቻቸውን እንዳይገርዙ፣ በቈየው ልማዳችን መሠረት እንዳይኖሩ እንደምታስተምር ስለ አንተ ተነግሮአቸዋል።

22መምጣትህን መስማታቸው የማይቀር ነውና፣ እንግዲህ ምን እናድርግ?

23ስለዚህ የምንልህን አድርግ። ስእለት ያለባቸው አራት ሰዎች በእኛ ዘንድ አሉ፤

24እነዚህን ሰዎች ይዘህ ከእነርሱ ጋር የመንጻቱን ሥርዐት ፈጽም፤ ራሳቸውንም እንዲላጩ የሚጠየቀውን ገንዘቡን ክፈልላቸው፤ በዚህም ስለ አንተ የተነገራቸው ሰዎች ሁሉ፣ የሰሙት እውነት እንዳልሆነና አንተ ራስህ ሕጉን ጠብቀህ የምትኖር መሆንህን ያውቃሉ።

25ከአሕዛብ ወገን ያመኑትን በተመለከተ ግን ለጣዖት የተሠዋ ምግብ፣ ደምና ታንቆ የሞተ ከብት እንዳይበሉ፣ ደግሞም ከዝሙት ርኵሰት ራሳቸውን እንዲጠብቁ ወስነን ጽፈንላቸዋል።”

26ጳውሎስም በማግስቱ ሰዎቹን ይዞ ሄደ፤ አብሮአቸውም የመንጻቱን ሥርዐት ፈጸመ። ከዚያም የመንጻቱ ሥርዐት መቼ እንደሚያበቃና የእያንዳንዳቸውም መሥዋዕት መቼ እንደሚቀርብ ለማስታወቅ ወደ ቤተ መቅደስ ገባ።

27ሰባቱ ቀንም ሊፈጸም ሲቃረብ፣ ከእስያ አውራጃ የመጡት አይሁድ ጳውሎስን በቤተ መቅደስ ባዩት ጊዜ፣ ሕዝቡን ሁሉ አነሣሥተው ያዙት፤

28እንዲህም እያሉ ጮኹ፤ “የእስራኤል ሰዎች ሆይ፤ ርዱን! ሕዝባችንንና ሕጋችንን እንዲሁም ይህን ስፍራ በማጥላላት በደረሰበት ስፍራ የሚገኙትን ሰዎች ሁሉ የሚያስተምረው ሰው ይህ ነው፤ ከዚህም በላይ ግሪኮችን ወደ ቤተ መቅደስ እያስገባ ይህን የተቀደሰ ስፍራ የሚያረክሰው እርሱ ነው።”

29ይህንም ያሉት ቀደም ሲል፣ የኤፌሶኑን ሰው ጥሮፊሞስን ከጳውሎስ ጋር በከተማው ውስጥ ስላዩት፣ ጳውሎስ እርሱንም ወደ ቤተ መቅደስ ይዞ የገባ ስለ መሰላቸው ነበር።

30ከተማው በሙሉ ታወከ፤ ሕዝቡም ከየአቅጣጫው እየተሯሯጡ መጡ፤ ጳውሎስንም ይዘው እየጐተቱት ከቤተ መቅደሱ ግቢ አወጡት፤ በሮቹም ወዲያውኑ ተዘጉ።

31ሊገድሉት ሲፈልጉም የኢየሩሳሌም ከተማ ፍጹም ታወከች፤ ወሬውም ለሮማ ጦር አዛዥ ደረሰው።

32እርሱም ወዲያው አንዳንድ የጦር መኰንኖችንና ወታደሮችን ይዞ እየሮጠ ወደ እነርሱ ወረደ፤ እነርሱም መኰንኖቹንና ወታደሮቹን ባዩ ጊዜ ጳውሎስን መደብደብ ተዉ።

33የጦር አዛዡም ቀርቦ ያዘው፤ በሁለት ሰንሰለትም እንዲታሰር ትእዛዝ ሰጠ፤ ከዚያም ማን መሆኑንና ምን እንዳደረገ ጠየቀ።

34ሕዝቡም ከፊሉ አንድ ነገር ሲናገር፣ ከፊሉ ደግሞ ሌላ ይናገር ነበር፤ ከጫጫታው የተነሣም አዛዡ ምንም ነገር ሊሰማ አልቻለም፤ ስለዚህ ጳውሎስ ወደ ጦር ሰፈር እንዲወሰድ አዘዘ።

35ከሕዝቡ ሁካታ የተነሣ፣ ጳውሎስ ወደ መውጫው ደረጃ ሲደርስ ወታደሮቹ ይሸከሙት ዘንድ ግድ ሆነባቸው።

36ከኋላ የተከተለውም ሕዝብ፣ “አስወግደው!” እያለ ይጮኽ ነበር።

37ወታደሮቹ ወደ ጦር ሰፈር ይዘውት ሊሄዱ ሲሉ፣ ጳውሎስ ጦር አዛዡን፣ “አንድ ነገር እንድነግርህ ፍቀድልኝ?” አለው። አዛዡም እንዲህ አለው፤ “የግሪክ ቋንቋ ታውቃለህ?

38አንተ ከዚህ ቀደም ዐመፅ አስነሥተህ፣ አራት ሺህ ነፍሰ ገዳዮችን ወደ በረሓ ያሸፈትኸው ግብፃዊ አይደለህምን?”

39ጳውሎስም፣ “እኔስ በኪልቅያ ያለችው የታዋቂዋ የጠርሴስ ከተማ ነዋሪ የሆንሁ አይሁዳዊ ነኝ፤ ለሕዝቡ ንግግር እንዳደርግ ፍቀድልኝ” አለው።

40ጳውሎስም የጦር አዛዡን ካስፈቀደ በኋላ፣ በደረጃው ላይ ቆሞ ሕዝቡን በእጁ ጠቀሰ፤ ሁሉም ጸጥ ባሉ ጊዜ፣ በዕብራይስጥ ቋንቋ እንዲህ አለ፤

ማብራሪያ

21:1-7 ጉዳዮቻችን መልካም በሆነ መንገድ ሲከናወኑ መለኮታዊ ጥበቃ መታወቅ አለበት። ጳውሎስ በደረሰበት ሁሉ ደቀ መዛሙርት መኖራቸውን መረመረ፣ አገኛቸውም። መከራዎቹን አስቀድመው በማየት፣ ለእርሱ ካላቸው ፍቅር የተነሳና ስለ ቤተ ክርስቲያን ካላቸው ስጋት የተነሳ፣ እርሱ በነጻነት ቢቀጥል ለእግዚአብሔር ክብር ይበልጥ እንደሚሆን በስህተት አሰቡ። ነገር ግን ከዚህ እንዲመለስ ሊያሳምኑት ያሳዩት ብርቱ ጥረት፣ የእርሱን መንፈሳዊ ቁርጠኝነት ይበልጥ ገለጠው። በምሳሌም በትምህርትም ጭምር ሁል ጊዜ እንድንጸልይ፣ ያለማቋረጥ እንድንጸልይ አስተምሮናል። የመጨረሻ መሰናበቻቸው በጸሎት ተጣፍጦ ነበር።

፳፩፥፰-፲፰ ጳውሎስ ስለ ችግሮቹ ግልጽ የሆነ ማስጠንቀቂያ ተሰጥቶት ነበር፤ ይህም ሲመጡበት ድንጋጤ ወይም ፍርሃት እንዳይሆኑበት ነው። ወደ እግዚአብሔር መንግሥት የምንገባው በብዙ መከራ ውስጥ አልፈን እንደሆነ የተሰጠን አጠቃላይ ማስታወቂያ ለእኛም ተመሳሳይ ጥቅም ሊኖረው ይገባል። የእነርሱ ማልቀስ ቁርጠኝነቱን ማዳከም እና ማርገብ ጀመረ። ጌታችን መስቀላችንን እንድንሸከም ነግሮን የለምን? ሕሊናውን ሳይጎዳ ሊያደርግላቸው የማይችለውን ነገር እንዲያደርግላቸው በብርቱ መለመናቸው አስጨነቀው። ችግር ሲመጣብን ስናይ፣ "የጌታ ፈቃድ ይሁን፣ መፍትሔ የለውም" ብቻ ሳይሆን፣ "የጌታ ፈቃድ ይሁን" ማለት ይገባናል። ምክንያቱም ፈቃዱ ጥበቡ ነውና፣ ሁሉንም እንደ ምክሩ ያደርጋል። ችግር ሲመጣ፣ የጌታ ፈቃድ እንደሆነ በማሰብ ሐዘናችን ሊረግብ ይገባል። ሲመጣብንም ስናይ፣ የጌታ ፈቃድ እንደሚሆን በማሰብ ፍርሃታችን ሊረግብ ይገባል። "አሜን፣ ይሁንልን" ልንል ይገባል። የኢየሱስ ክርስቶስ አንጋፋ ደቀ መዝሙር መሆን ክብር ነው፤ በእግዚአብሔር ጸጋ በግዴታው መንገድ ለረጅም ጊዜ መጽናት፣ በሃይማኖት ጸንቶ እየጨመረ በመሄድ ልምድ እያገኘ እስከ ደህና ሽምግልና መድረስ። ከእነዚህ አንጋፋ ደቀ መዛሙርት ጋር ማደርን አንድ ሰው ይመርጣል፤ ምክንያቱም የዘመናቸው ብዛት ጥበብን ያስተምራልና። በኢየሩሳሌም የነበሩ ብዙ ወንድሞች ጳውሎስን በደስታ ተቀበሉት። ምናልባት ጳውሎስ በእኛ ዘንድ ቢሆን በደስታ እንቀበለው ነበር ብለን እናስብ ይሆናል። ነገር ግን ትምህርቱን በደስታ የማንቀበል ከሆነ፣ እርሱንም በደስታ አንቀበለውም ነበር።

ሙሉ ማብራሪያውን ያንብቡ ድምፅ፣ ሙሉ ማብራሪያ እና ከመስመር ውጭ ንባብ

ትርጉሞች8 · 6

AMHEVG ከእነርሱም ተለይተን ተነሣን፤ በቀጥታም ሄደን ወደ ቆስ በነገውም ወደ ሩድ ከዚያም ወደ ጳጥራ መጣን፤ አማርኛ ENGNIV After we had torn ourselves away from them, we put out to sea and sailed straight to Cos. The next day we went to Rhode… English BCV ካብኣቶም ተፈሊና ብመርከብ ምስ ተልዓልና፥ መንገድና ኣቕኒዕና ናብ ቆስ ከድና፤ ንፅባሒቱ ኸዓ፥ ሮዶስ ኣብ እትብሃል ደሴት በፃሕና፤ ካብኣውን ናብ ጳጥራ ኣተና። ትግርኛ GAZBIB Akka kanatti nagaa isaanitti dhaamnee giddiitti gargar baanee, utuu hin jal'atin markabaan ceenee, Qos biyya bishaan ke… Afaan Oromoo BCV GIZ ወሖርነ ንሕነሂ ወእሙንቱሂ አተዉ፤ ወረዊጸነ በጻሕነ ብሔረ ቆስያ፤ ወበሳኒታ ወረድነ ሩድ፡ ወእምህየ ሖርነ ለጳጥራ። giz GAZGAZ Akka kanatti nagaa isaanitti dhaamnee giddiitti gargar baanee, utuu hin jal'atin markabaan ceenee, Qos biyya bishaan ke… Afaan Oromoo BCV aksum ካብኣቶም ተፈሊና ብመርከብ ምስ ተልዓልና፥ መንገድና ኣቕኒዕና ናብ ቆስ ከድና፤ ንፅባሒቱ ኸዓ፥ ሮዶስ ኣብ እትብሃል ደሴት በፃሕና፤ ካብኣውን ናብ ጳጥራ ኣተና። ትግርኛ SWAHSUV Ikawa tulipokwisha kujitenga nao na kuabiri, tukafika Kosi kwa tanga moja, na siku ya pili yake tukafika Rodo na kutoka… Kiswahili