የሐዋርያት ሥራ 21

AMHEVGአማርኛ39 ጥቅሶች5:51 አዳምጥ
አዳምጥ 5:51 · መደበኛ · አስደናቂ በBiblight ይክፈቱ

1ከእነርሱም ተለይተን ተነሣን፤ በቀጥታም ሄደን ወደ ቆስ በነገውም ወደ ሩድ ከዚያም ወደ ጳጥራ መጣን፤

2ወደ ፊንቄም የሚሻገር መርከብ አግኝተን ገባንና ተነሣን።

3ቆጵሮስንም ባየናት ጊዜ በስተ ግራችን ተውናት ወደ ሶርያም ሄደን ወደ ጢሮስ ደረስን፥ መርከቡ ሸክሙን በዚያ የሚያራግፍ ነበርና።

4ደቀ መዛሙርትንም ባገኘን ጊዜ በዚያ ሰባት ቀን ተቀመጥን፤ እነርሱም ጳውሎስን ወደ ኢየሩሳሌም እንዳይወጣ በመንፈስ አሉት።

5ጊዜውንም በፈጸምን ጊዜ ወጥተን ሄድን፤ ሁላቸውም ከሚስቶቻቸውና ከልጆቻቸው ጋር እስከ ከተማው ውጭ ድረስ ሸኙን፥ በባሕሩም ዳር ተንበርክከን ጸለይን፤

6እርስ በርሳችንም ተሰነባብተን ወደ መርከብ ወጣን፥ እነዚያም ወደ ቤታቸው ተመለሱ።

7እኛም የባሕሩን መንገድ ጨርሰን ከጢሮስ ወደ አካ ደረስን፥ ለወንድሞችም ሰላምታ ሰጥተን ከእነርሱ ዘንድ አንድ ቀን ተቀመጥን።

8በነገውም ወጥተን ወደ ቂሣርያ መጣን፥ ከሰባቱም አንድ በሚሆን በወንጌላዊው ፊልጶስ ቤት ገብተን በእርሱ ዘንድ ተቀመጥን።

9ለእርሱም ትንቢት የሚናገሩ አራት ደናግል ሴቶች ልጆች ነበሩት።

10አያሌ ቀንም ተቀምጠን ሳለን ነቢይ የነበረ አጋቦስ የሚሉት አንድ ሰው ከይሁዳ ወረደ።

11ወደ እኛም መጣና የጳውሎስን መታጠቂያ ወስዶ የገዛ እጁንና እግሩን አስሮ፦ “እንዲሁ መንፈስ ቅዱስ፦ ‘ይህ መታጠቂያ ያለውን ሰው አይሁድ በኢየሩሳሌም እንደዚህ ያስሩታል በአሕዛብም እጅ አሳልፈው ይሰጡታል፥’ ይላል፡” አለ።

12ይህንም በሰማን ጊዜ እኛም በዚያ የሚኖሩትም ወደ ኢየሩሳሌም እንዳይወጣ ለመንነው።

13ጳውሎስ ግን መልሶ፦ “እያለቀሳችሁ ልቤንም እየሰበራችሁ ምን ማድረጋችሁ ነው? እኔ ስለ ጌታ ስለ ኢየሱስ ስም በኢየሩሳሌም ለመሞት እንኳ ተሰናድቼአለሁ እንጂ ለእስራት ብቻ አይደለም፡” አለ።

14ምክርንም ሊቀበል እምቢ ባለ ጊዜ፦ “የጌታ ፈቃድ ይሁን፡” ብለን ዝም አልን።

15ከዚህም ቀን በኋላ ተዘጋጅተን ወደ ኢየሩሳሌም ወጣን።

16በቂሣርያም ከነበሩ ደቀ መዛሙርት አንዳንዶች ደግሞ ከእኛ ጋር መጡ፥ እነርሱም ወደምናድርበት ወደ ቀደመው ደቀ መዝሙር ወደ ቆጵሮሱ ምናሶን ወደሚሉት ቤት መሩን።

17ወደ ኢየሩሳሌም በደረስን ጊዜ ወንድሞች በደስታ ተቀበሉን።

18በነገውም ጳውሎስ ከእኛ ጋር ወደ ያዕቆብ ዘንድ ገባ ሽማግሌዎችም ሁሉ መጡ።

19ሰላምታም ካቀረበላቸው በኋላ በእርሱ ማገልገል እግዚአብሔር በአሕዛብ መካከል ያደረገውን በእያንዳንዱ ተረከላቸው።

20እነርሱም በሰሙ ጊዜ እግዚአብሔርን አመሰገኑ አሉትም፦ “ወንድም ሆይ፥ በአይሁድ መካከል አምነው የነበሩት ስንት አእላፋት እንደ ሆኑ ታያለህ፤ ሁላቸውም ለሕግ የሚቀኑ ናቸው።

21ልጆቻቸውንም እንዳይገርዙ በሥርዓትም እንዳይሄዱ ብለህ በአሕዛብ መካከል ያሉት አይሁድ ሁሉ ሙሴን ይክዱ ዘንድ እንድታስተምር ስለ አንተ ነግረዋቸዋል።

22እንግዲህ ምን ይሁን? የአንተን መምጣት ይሰማሉና ብዙዎች የግድ ሳይሰበሰቡ አይቀሩም።

23እንግዲህ ይህን የምንልህን አድርግ፤ ስለት ያለባቸው አራት ሰዎች በእኛ ዘንድ አሉ።

24እነዚህንም ይዘህ ከእነርሱ ጋር ንጻ፥ ራሳቸውንም እንዲላጩ ገንዘብ ክፈልላቸው፤ ሁሉም ስለ አንተ የተማሩት ከንቱ እንደ ሆነና አንተ ራስህ ደግሞ ሕጉን እየጠበቅህ በሥርዓት እንድትመላለስ ያውቃሉ።

25አምነው ስለ ነበሩ አሕዛብ ግን ለጣዖት ከተሠዋ ከደምም ከታነቀም ከዝሙትም ነፍሳቸውን እንዲጠብቁ ፈርደን እኛ ጽፈንላቸዋል።”

26በዚያን ጊዜ ጳውሎስ ሰዎችን ይዞ በማግሥቱ ከእነርሱ ጋር እየነጻ፥ መንጻታቸውን የሚፈጽሙበትን ቀን አስታውቆ ወደ መቅደስ ገባ። በዚያም ቀን ስለ እያንዳንዳቸው መሥዋዕትን አቀረቡ።

27ሰባቱ ቀንም ይፈጸም ዘንድ ሲቀርብ ከእስያ የመጡ አይሁድ በመቅደስ አይተውት ሕዝብን ሁሉ አወኩና፦ “የእስራኤል ሰዎች ሆይ፥ እርዱን ሕዝብን ሕግንም ይህንም ስፍራ ሲቃወም ሰውን ሁሉ በየስፍራው የሚያስተምረው ሰው ይህ ነው፤ ጨምሮም የግሪክን ሰዎች ደግሞ ወደ መቅደስ አግብቶ ይህን የተቀደሰ ስፍራ አርክሶአል፥” ብለው እየጮኹ እጃቸውን ጫኑበት።

29በፊት የኤፌሶኑን ጥሮፊሞስን ከእርሱ ጋር በከተማ አይተውት ነበርና ጳውሎስም ወደ መቅደስ ያገባው መስሎአቸው ነው።

30ከተማውም ሁሉ ታወከ ሕዝቡም ሁሉ ተሰበሰቡ ጳውሎስንም ይዘው ከመቅደስ ውጭ ጎተቱት፥ ወዲያውም ደጆች ተዘጉ።

31ሊገድሉትም ሲፈልጉ፦ “ኢየሩሳሌም ፈጽማ ታወከች፡” የሚል ወሬ ወደ ጭፍራው ሻለቃ ወጣ፤

32እርሱም ያን ጊዜ ወታደሮችን ከመቶ አለቆች ጋር ይዞ እየሮጠ ወረደባቸው፤ እነርሱም የሻለቃውንና ወታደሮችን ባዩ ጊዜ ጳውሎስን መምታት ተዉ።

33በዚያን ጊዜም የሻለቃው ቀርቦ ያዘውና በሁለት ሰንሰለት ይታሰር ዘንድ አዞ ማን እንደ ሆነና ምን እንዳደረገ ጠየቀ።

34ሕዝቡም እኵሌቶቹ እንዲህ እኵሌቶቹም እንዲያ እያሉ ይጮኹ ነበር፤ ስለ ጫጫታውም እርግጡን ማወቅ ባልተቻለ ጊዜ፥ ወደ ወታደሮች ሰፈር ይወስዱት ዘንድ አዘዘ።

35ወደ ደረጃውም በደረሰ ጊዜ ስለ ሕዝቡ ግፊያ ወታደሮች እንዲሸከሙት ሆነ፤

36ብዙ ሕዝብ፦ “አስወግደው፡” እያሉና እየጮኹ ይከተሉ ነበርና።

37ወደ ሰፈርም ሊያገቡት በቀረቡ ጊዜ፥ ጳውሎስ የሻለቃውን፦ “አንድ ነገር ብነግርህ ትፈቅዳለህን?” አለው። እርሱም፦ “የግሪክ ቋንቋ ታውቃለህን?

38አንተ ከዚህ ዘመን አስቀድሞ ከነፍሰ ገዳዮቹ አራቱን ሺህ ሰዎች አሸፍተህ ወደ ምድረ በዳ ያወጣህ የግብፅ ሰው አይደለህምን?” አለ።

39ጳውሎስ ግን፦ “እኔስ አይሁዳዊ በኪልቅያ ያለው የጠርሴስ ሰው ሆኜ ስመ ጥር በሆነ ከተማ የምኖር ነኝ፤ ለሕዝቡ እናገር ዘንድ እንድትፈቅድልኝ እለምንሃለሁ፡” አለ።

40በፈቀደለትም ጊዜ ጳውሎስ በደረጃው ላይ ቆሞ በእጁ ወደ ሕዝቡ ጠቀሰ እጅግም ጸጥታ በሆነ ጊዜ በዕብራይስጥ ቋንቋ እየተናገረ እንዲህ አለ።

ማብራሪያ

21:1-7 ጉዳዮቻችን መልካም በሆነ መንገድ ሲከናወኑ መለኮታዊ ጥበቃ መታወቅ አለበት። ጳውሎስ በደረሰበት ሁሉ ደቀ መዛሙርት መኖራቸውን መረመረ፣ አገኛቸውም። መከራዎቹን አስቀድመው በማየት፣ ለእርሱ ካላቸው ፍቅር የተነሳና ስለ ቤተ ክርስቲያን ካላቸው ስጋት የተነሳ፣ እርሱ በነጻነት ቢቀጥል ለእግዚአብሔር ክብር ይበልጥ እንደሚሆን በስህተት አሰቡ። ነገር ግን ከዚህ እንዲመለስ ሊያሳምኑት ያሳዩት ብርቱ ጥረት፣ የእርሱን መንፈሳዊ ቁርጠኝነት ይበልጥ ገለጠው። በምሳሌም በትምህርትም ጭምር ሁል ጊዜ እንድንጸልይ፣ ያለማቋረጥ እንድንጸልይ አስተምሮናል። የመጨረሻ መሰናበቻቸው በጸሎት ተጣፍጦ ነበር።

፳፩፥፰-፲፰ ጳውሎስ ስለ ችግሮቹ ግልጽ የሆነ ማስጠንቀቂያ ተሰጥቶት ነበር፤ ይህም ሲመጡበት ድንጋጤ ወይም ፍርሃት እንዳይሆኑበት ነው። ወደ እግዚአብሔር መንግሥት የምንገባው በብዙ መከራ ውስጥ አልፈን እንደሆነ የተሰጠን አጠቃላይ ማስታወቂያ ለእኛም ተመሳሳይ ጥቅም ሊኖረው ይገባል። የእነርሱ ማልቀስ ቁርጠኝነቱን ማዳከም እና ማርገብ ጀመረ። ጌታችን መስቀላችንን እንድንሸከም ነግሮን የለምን? ሕሊናውን ሳይጎዳ ሊያደርግላቸው የማይችለውን ነገር እንዲያደርግላቸው በብርቱ መለመናቸው አስጨነቀው። ችግር ሲመጣብን ስናይ፣ "የጌታ ፈቃድ ይሁን፣ መፍትሔ የለውም" ብቻ ሳይሆን፣ "የጌታ ፈቃድ ይሁን" ማለት ይገባናል። ምክንያቱም ፈቃዱ ጥበቡ ነውና፣ ሁሉንም እንደ ምክሩ ያደርጋል። ችግር ሲመጣ፣ የጌታ ፈቃድ እንደሆነ በማሰብ ሐዘናችን ሊረግብ ይገባል። ሲመጣብንም ስናይ፣ የጌታ ፈቃድ እንደሚሆን በማሰብ ፍርሃታችን ሊረግብ ይገባል። "አሜን፣ ይሁንልን" ልንል ይገባል። የኢየሱስ ክርስቶስ አንጋፋ ደቀ መዝሙር መሆን ክብር ነው፤ በእግዚአብሔር ጸጋ በግዴታው መንገድ ለረጅም ጊዜ መጽናት፣ በሃይማኖት ጸንቶ እየጨመረ በመሄድ ልምድ እያገኘ እስከ ደህና ሽምግልና መድረስ። ከእነዚህ አንጋፋ ደቀ መዛሙርት ጋር ማደርን አንድ ሰው ይመርጣል፤ ምክንያቱም የዘመናቸው ብዛት ጥበብን ያስተምራልና። በኢየሩሳሌም የነበሩ ብዙ ወንድሞች ጳውሎስን በደስታ ተቀበሉት። ምናልባት ጳውሎስ በእኛ ዘንድ ቢሆን በደስታ እንቀበለው ነበር ብለን እናስብ ይሆናል። ነገር ግን ትምህርቱን በደስታ የማንቀበል ከሆነ፣ እርሱንም በደስታ አንቀበለውም ነበር።

ሙሉ ማብራሪያውን ያንብቡ ድምፅ፣ ሙሉ ማብራሪያ እና ከመስመር ውጭ ንባብ

ትርጉሞች8 · 6

ENGNIV After we had torn ourselves away from them, we put out to sea and sailed straight to Cos. The next day we went to Rhode… English BCV ካብኣቶም ተፈሊና ብመርከብ ምስ ተልዓልና፥ መንገድና ኣቕኒዕና ናብ ቆስ ከድና፤ ንፅባሒቱ ኸዓ፥ ሮዶስ ኣብ እትብሃል ደሴት በፃሕና፤ ካብኣውን ናብ ጳጥራ ኣተና። ትግርኛ GAZBIB Akka kanatti nagaa isaanitti dhaamnee giddiitti gargar baanee, utuu hin jal'atin markabaan ceenee, Qos biyya bishaan ke… Afaan Oromoo BCV GIZ ወሖርነ ንሕነሂ ወእሙንቱሂ አተዉ፤ ወረዊጸነ በጻሕነ ብሔረ ቆስያ፤ ወበሳኒታ ወረድነ ሩድ፡ ወእምህየ ሖርነ ለጳጥራ። giz GAZGAZ Akka kanatti nagaa isaanitti dhaamnee giddiitti gargar baanee, utuu hin jal'atin markabaan ceenee, Qos biyya bishaan ke… Afaan Oromoo BCV aksum ካብኣቶም ተፈሊና ብመርከብ ምስ ተልዓልና፥ መንገድና ኣቕኒዕና ናብ ቆስ ከድና፤ ንፅባሒቱ ኸዓ፥ ሮዶስ ኣብ እትብሃል ደሴት በፃሕና፤ ካብኣውን ናብ ጳጥራ ኣተና። ትግርኛ AMHNIV ከእነርሱ ከተለየን በኋላ ቀጥታ በመርከብ ወደ ቆስ ተጓዝን፤ በማግስቱም ወደ ሩድ፣ ከዚያም ወደ ጳጥራ አመራን። አማርኛ SWAHSUV Ikawa tulipokwisha kujitenga nao na kuabiri, tukafika Kosi kwa tanga moja, na siku ya pili yake tukafika Rodo na kutoka… Kiswahili