የሐዋርያት ሥራ 15

AMHEVGአማርኛ38 ጥቅሶች5:31 አዳምጥ
አዳምጥ 5:31 · መደበኛ · አስደናቂ በBiblight ይክፈቱ

1አንዳንዶችም ከይሁዳ ወረዱና፦ “እንደ ሙሴ ሥርዓት ካልተገረዛችሁ ትድኑ ዘንድ አትችሉም፡” ብለው ወንድሞችን ያስተምሩ ነበር።

2በእነርሱና በጳውሎስ በበርናባስም መካከል ብዙ ጥልና ክርክር በሆነ ጊዜ፥ ስለዚህ ክርክር ጳውሎና በርናባስ ከእነርሱም አንዳንዶች ሌሎች ሰዎች ወደ ሐዋርያት ወደ ሽማግሌዎችም ወደ ኢየሩሳሌም ይወጡ ዘንድ ተቈረጠ።

3ቤተ ክርስቲያኑም በመንገድ እየረዳቸው እነርሱ የአሕዛብን መመለስ እየተረኩ በፊንቄና በሰማርያ አለፉ፥ ወንድሞችንም ሁሉ እጅግ ደስ አሰኙአቸው።

4ወደ ኢየሩሳሌምም በደረሱ ጊዜ ቤተ ክርስቲያንና ሐዋርያት ሽማግሌዎችም ተቀበሉአቸው፥ እግዚአብሔርም ከእነርሱ ጋር ያደረገውን ሁሉ አወሩ።

5ከፈሪሳውያን ወገን ግን ያመኑት አንዳንዶቹ ተነሥተው፦ “ትገርዙአቸው ዘንድና የሙሴን ሕግ እንዲጠብቁ ታዙአቸው ዘንድ ይገባል፡” አሉ።

6ሐዋርያትና ሽማግሌዎችም ስለዚህ ነገር ለመማከር ተሰበሰቡ።

7ከብዙ ክርክርም በኋላ ጴጥሮስ ተነሥቶ እንዲህ አላቸው ወንድሞች ሆይ፥ አሕዛብ ከአፌ የወንጌልን ቃል ሰምተው ያምኑ ዘንድ እግዚአብሔር በመጀመሪያው ዘመን ከእናንተ እኔን እንደ መረጠኝ እናንተ ታውቃላችሁ።

8ልብንም የሚያውቅ አምላክ ለእኛ ደግሞ እንደ ሰጠን መንፈስ ቅዱስን በመስጠት መሰከረላቸው፤

9ልባቸውንም በእምነት ሲያነጻ በእኛና በእነርሱ መካከል አንዳች አልለየም።

10እንግዲህ አባቶቻችንና እኛ ልንሸከመው ያልቻልነውን ቀንበር በደቀ መዛሙርት ጫንቃ ላይ በመጫን እግዚአብሔርን አሁን ስለ ምን ትፈታተናላችሁ?

11ነገር ግን በጌታ በኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋ እንደ እነርሱ ደግሞ እንድን ዘንድ እናምናለን።

12ሕዝቡም ሁሉ ዝም አሉ፥ በርናባስና ጳውሎስም እግዚአብሔር በእጃቸው በአሕዛብ መካከል ያደረገውን ምልክትና ድንቅ ሁሉ ሲተርኩላቸው ይሰሙ ነበር።

13እነርሱም ዝም ካሉ በኋላ ያዕቆብ እንዲህ ብሎ መለሰ፦ ወንድሞች ሆይ፥ ስሙኝ።

14እግዚአብሔር ለስሙ የሚሆንን ወገን ከአሕዛብ ይወስድ ዘንድ አስቀድሞ እንዴት እንደ ጐበኘ ስምዖን ተርኮአል።

15ከዚህም ጋር የነቢያት ቃል ይሰማማል፥ እንዲህ ተብሎ እንደ ተጻፈ፦

16‘ከዚህ በኋላ የቀሩት ሰዎችና በስሜ የተጠሩት አሕዛብ ሁሉ ጌታን ይፈልጉ ዘንድ እመለሳለሁ፥ የወደቀችውንም የዳዊትን ድንኳን እንደ ገና እሠራታለሁ፥ ፍራሽዋንም እንደ ገና እሠራታለሁ እንደ ገናም አቆማታለሁ፡ ይላል ይህን የሚያደርግ ጌታ።

18ከጥንት ጀምሮ ሥራው ሁሉ በእግዚአብሔር ዘንድ የታወቀ ነው።

19“ስለዚህ ከአሕዛብ ወደ እግዚአብሔር የዞሩትን እንዳናስቸግራቸው፥

20ነገር ግን ከጣዖት ርኵሰትና ከዝሙት ከታነቀም ከደምም ይርቁ ዘንድ እንድንጽፍላቸው እቈርጣለሁ።

21ሙሴስ ከቀደሙት ትውልድ ጀምሮ በሰንበት በሰንበት በምኵራቦቹ ሲያነቡ በየከተማው እርሱን የሚሰብኩ አሉት።

22ያን ጊዜ ሐዋርያትና ሽማግሌዎች ከቤተ ክርስቲያኑ ሁሉ ጋር ከእነርሱ የተመረጡትን ሰዎች ከጳውሎስና ከበርናባስ ጋር ወደ አንጾኪያ ይልኩ ዘንድ ፈቀዱ፤ እነርሱም በወንድሞች መካከል ዋናዎች ሆነው በርስያን የተባለው ይሁዳና ሲላስ ነበሩ።

23እንዲህም ጽፈው በእነርሱ እጅ ላኩ፦ “ሐዋርያትና ሽማግሌዎች ወንድሞችም በአንጾኪያና በሶርያ በኪልቅያም ለሚኖሩ ከአሕዛብ ወገን ለሆኑ ወንድሞች ሰላምታ ያቀርባሉ።

24ያላዘዝናቸው ሰዎች ከእኛ ወጥተው፦ ትገረዙ ዘንድና ሕግን ትጠብቁ ዘንድ ይገባችኋል፡ ብለው ልባችሁን እያወኩ በቃል እንዳናወጡአችሁ ስለ ሰማን፥

25ስለ ጌታችን ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ ስም ነፍሳቸውን ከሰጡት ከምንወዳቸው ከበርናባስና ከጳውሎስ ጋር የተመረጡትን ሰዎች ወደ እናንተ እንልክ ዘንድ በአንድ ልብ ሆነን ፈቀድን።

27ራሳቸውም ደግሞ በቃላቸው ያንኑ ይነግሩአችሁ ዘንድ ይሁዳንና ሲላስን ልከናል።

28ለጣዖት ከተሠዋ፥ ከደምም፥ ከታነቀም፥ ከዝሙትም ትርቁ ዘንድ፣ ከዚህ ከሚያስፈልገው በቀር ሌላ ሸክም እንዳንጭንባችሁ እኛና መንፈስ ቅዱስ ፈቅደናልና፤ ከዚህም ሁሉ ራሳችሁን ብትጠብቁ በመልካም ትኖራላችሁ። ጤና ይስጣችሁ።”

30እነርሱም ተሰናብተው ወደ አንጾኪያ ወረዱ፥ ሕዝቡንም ሰብስበው ደብዳቤውን ሰጡአቸው።

31ባነበቡትም ጊዜ ከምክሩ የተነሣ ደስ አላቸው።

32ይሁዳና ሲላስም ደግሞ ነቢያት ነበሩና ወንድሞችን በብዙ ቃል መክረው አጸኑአቸው።

33አያሌ ቀንም ከተቀመጡ በኋላ ከወንድሞች በሰላም ተሰናብተው ወደ ሐዋርያት ሄዱ።

34ሲላስ ግን በዚያ ይኖር ዘንድ ፈቀደ።

35ጳውሎስና በርናባስም ከሌሎች ከብዙ ሰዎች ጋር ደግሞ የጌታን ቃል እያስተማሩና ወንጌልን እየሰበኩ በአንጾኪያ ይቀመጡ ነበር።

36ከጥቂት ቀንም በኋላ ጳውሎስ በርናባስን፦ “ተመልሰን የጌታን ቃል በተናገርንበት በየከተማው ሁሉ ወንድሞችን እንጐብኛቸው፥ እንዴት እንዳሉም እንወቅ” አለው።

37በርናባስም ማርቆስ የተባለውን ዮሐንስን ደግሞ ከእነርሱ ጋር ይወስድ ዘንድ አሰበ፤

38ጳውሎስ ግን ይህን ከእነርሱ ጋር ሊወስድ አልፈቀደም፥ ከእነርሱ ዘንድ ከጵንፍልያ ተለይቶ ነበርና፥ ወደ ሥራም ከእነርሱ ጋር አልመጣም ነበርና።

39ስለዚህም እርስ በርሳቸው እስኪለያዩ ድረስ መከፋፋት ሆነ፥ በርናባስም ማርቆስን ይዞ በመርከብ ወደ ቆጵሮስ ሄደ።

40ጳውሎስ ግን ሲላስን መረጠ፥ ወንድሞችም ለእግዚአብሔር ጸጋ አደራ ከሰጡት በኋላ ወጣ፤

41አብያተ ክርስትያናትንም እያጸና በሶርያና በኪልቅያ ይዞር ነበር።

ማብራሪያ

15:1-6 አንዳንድ ከይሁዳ የመጡ ሰዎች በአንጾኪያ ለነበሩት ከአሕዛብ የተመለሱ አማኞች ሙሴ እንደሰጠው መላውን የሥርዓት ሕግ ካልጠበቁ በስተቀር መዳን እንደማይችሉ አስተማሩ፤ በዚህም የክርስቲያንን ነፃነት ለማጥፋት ፈለጉ። እኛ እንደምናደርገው የማያደርጉ ሁሉ የተሳሳቱ እንደሆኑ ማሰብ በእኛ ውስጥ ያለ እንግዳ ዝንባሌ ነው። ትምህርታቸው በጣም ተስፋ አስቆራጭ ነበር። ጥበበኞችና መልካም ሰዎች እስከቻሉ ድረስ ክርክሮችንና ጭቅጭቆችን ለማስወገድ ይፈልጋሉ፤ ነገር ግን ሐሰተኛ አስተማሪዎች የወንጌልን ዋና እውነቶች ሲቃወሙ ወይም ጎጂ ትምህርቶችን ሲያስተዋውቁ፣ እኛ እነርሱን ከመቃወም ወደ ኋላ ልንል አይገባንም።

፲፭፥፯-፳፩ "ልባቸውን በእምነት በማንጻት" ከሚሉት ቃላት እንዲሁም ከቅዱስ ጴጥሮስ ንግግር እንደምንረዳው፣ በእምነት የምናገኘው ጽድቅና በመንፈስ ቅዱስ የምናገኘው ቅድሳት ሊለያዩ እንደማይችሉ፤ ሁለቱም የእግዚአብሔር ስጦታዎች እንደሆኑ እንመለከታለን። ወንጌልን ስለሰማን እግዚአብሔርን ልንባርክ ትልቅ ምክንያት አለን። የልቦች መርማሪ የሆነው ታላቁ አምላክ የሚያጸድቀውን እንዲሁም በመንፈስ ቅዱስ ማኅተም የሚያረጋግጠውን እምነት እንዲኖረን እንመኛለን። ያን ጊዜ ልቦቻችንና ሕሊናዎቻችን ከኃጢአት ዕዳ ይነጻሉ፤ በክርስቶስ ደቀ መዛሙርት ላይ አንዳንዶች ሊጭኑባቸው ከሚሞክሩት ሸክምም ነጻ እንወጣለን።

ጳውሎስና በርናባስ ግልጽ በሆኑ እውነታዎች እንዳሳዩት፣ እግዚአብሔር የሙሴን ሕግ ሳይጨምሩ ንጹሕ የሆነውን ወንጌል ለአሕዛብ መስበክን ተቀብሎ ነበር፤ ስለዚህም ያንን ሕግ በእነርሱ ላይ ማስገደድ እግዚአብሔር የሠራውን ሥራ ማፍረስ ነበር።

ሙሉ ማብራሪያውን ያንብቡ ድምፅ፣ ሙሉ ማብራሪያ እና ከመስመር ውጭ ንባብ

ትርጉሞች8 · 6

ENGNIV Some men came down from Judea to Antioch and were teaching the brothers: “Unless you are circumcised, according to the … English BCV ካብ ይሁዳ ናብ ኣንፆኪያ ናይ ሶርያ ዝኸዱ ሰባት ድማ፥ ነቶም ኣሕዋት ከም “ስርዓት ሙሴ እንተ ዘይተገሪዝኩም ክትድሕኑ ኣይትኽእሉን ኢኹም” ኢሎም መሃርዎም። ትግርኛ GAZBIB Jarreen kutaa biyya Yihudaatii, Anxokiyaa biyya Sooriyaatti gad bu'an tokko immoo, ?Akka seerri Musee ajajutti yoo dhag… Afaan Oromoo BCV GIZ ወቦ እለ ወረዱ እምብሔረ ይሁዳ ወመሀርዎሙ ለሕዝብ ወይቤልዎሙ፦ “እምከመ ኢተገዘርክሙ በሕገ ሙሴ ኢትክሉ ሐዪወ።” giz GAZGAZ Jarreen kutaa biyya Yihudaatii, Anxokiyaa biyya Sooriyaatti gad bu'an tokko immoo, ?Akka seerri Musee ajajutti yoo dhag… Afaan Oromoo BCV aksum ካብ ይሁዳ ናብ ኣንፆኪያ ናይ ሶርያ ዝኸዱ ሰባት ድማ፥ ነቶም ኣሕዋት ከም “ስርዓት ሙሴ እንተ ዘይተገሪዝኩም ክትድሕኑ ኣይትኽእሉን ኢኹም” ኢሎም መሃርዎም። ትግርኛ AMHNIV አንዳንድ ሰዎችም ከይሁዳ ወደ አንጾኪያ ወርደው፣ “በሙሴ ሥርዐት መሠረት ካልተገረዛችሁ ልትድኑ አትችሉም” በማለት ወንድሞችን ማስተማር ጀመሩ። አማርኛ SWAHSUV Wakashuka watu waliotoka Uyahudi wakawafundisha wale ndugu ya kwamba, Msipotahiriwa kama desturi ya Musa hamwezi kuokok… Kiswahili