የሐዋርያት ሥራ 14

AMHEVGአማርኛ27 ጥቅሶች3:31 አዳምጥ
አዳምጥ 3:31 · መደበኛ · አስደናቂ በBiblight ይክፈቱ

1በኢቆንዮንም እንደ ቀድሞ ወደ አይሁድ ምኵራብ ገብተው ከአይሁድና ከግሪክ ሰዎች ብዙ እስኪያምኑ ድረስ ተናገሩ።

2ያላመኑት አይሁድ ግን የአሕዛብን ልብ በወንድሞች ላይ አነሣሡ አስከፉም።

3ምልክትና ድንቅ በእጃቸው ይደረግ ዘንድ እየሰጠ ለጸጋው ቃል ስለ መሰከረው ስለ ጌታ ገልጠው እየተናገሩ ረጅም ወራት ተቀመጡ።

4የከተማውም ሕዝብ ተከፍለው እኵሌቶቹ ከአይሁድ እኵሌቶቹም ከሐዋርያት ጋር ሆኑ።

5አሕዛብና አይሁድ ግን ከአለቆቻቸው ጋር ሊያንገላቱአቸውና ሊወግሩአቸው ባሰቡ ጊዜ፥

6አውቀው ልስጥራንና ደርቤን ወደሚባሉት ወደ ሊቃኦንያ ከተማዎች በእነርሱም ዙሪያ ወዳለው አገር ሸሹ፤

7በዚያም ወንጌልን ይሰብኩ ነበር።

8በልስጥራንም እግሩ የሰለለ፥ ከእናቱም ማኅፀን ጀምሮ አንካሳ የሆነ፥ ከቶም ሄዶ የማያውቅ አንድ ሰው ተቀምጦ ነበር።

9ይህም ሰው ጳውሎስ ሲናገር ይሰማ ነበር፤ እርሱም ትኵር ብሎ ተመለከተውና ይድን ዘንድ እምነት እንዳለው ባየ ጊዜ፥

10በታላቅ ድምፅ፦ “ቀጥ ብለህ በእግርህ ቁም፡” አለው። ብድግ ብሎም ተንሥቶ ይመላለስ ነበር።

11ሕዝቡም ጳውሎስ ያደረገውን ባዩ ጊዜ ድምፃቸውን ከፍ አድርገው በሊቃኦንያ ቋንቋ፦ “አማልክት ሰዎችን መስለው ወደ እኛ ወርደዋል፡” አሉ፤

12በርናባስንም ድያ አሉት፤ ጳውሎስንም እርሱ በመናገር ዋና ስለ ነበረ ሄርሜን አሉት።

13በከተማውም ፊት ቤተ መቅደስ ያለው የድያ ካህን ኮርማዎችንና የአበባን አክሊሎች ወደ ደጃፍ አምጥቶ ከሕዝቡ ጋር ሆኖ ሊሠዋላቸው ወደደ።

14ሐዋርያት በርናባስና ጳውሎስ ግን ይህን በሰሙ ጊዜ ልብሳቸውን ቀደው ወደ ሕዝቡ መካከል እየጮኹ ሮጡ፥

15እንዲህም አሉ፦ “እናንተ ሰዎች፥ ይህን ስለ ምን ታደርጋላችሁ? እኛ ደግሞ እንደ እናንተ የምንሰማ ሰዎች ነን፥ ከዚህም ከንቱ ነገር ሰማይንና ምድርን ባሕርንም በእነርሱም ያለውን ሁሉ ወደ ፈጠረ ወደ ሕያው እግዚአብሔር ዘወር ትሉ ዘንድ ወንጌልን እንሰብካለን።

16እርሱ ባለፉት ትውልዶች አሕዛብን ሁሉ በገዛ ራሳቸው ጐዳና ይሄዱ ዘንድ ተዋቸው።

17ከዚህም ሁሉ ጋር መልካም ሥራ እየሠራ፥ ከሰማይ ዝናብን ፍሬ የሚሆንበትንም ወራት ሲሰጠን፥ ልባችንንም በመብልና በደስታ ሲሞላው ራሱን ያለ ምስክር አልተወም።”

18ይህንም ብለው እንዳይሠዉላቸው ሕዝቡን በጭንቅ አስተዉአቸው።

19አይሁድ ግን ከአንጾኪያና ከኢቆንዮን መጡ፤ ሕዝቡንም አባብለው ጳውሎስን ወገሩ የሞተም መስሎአቸው ከከተማ ወደ ውጭ ጐተቱት።

20ደቀ መዛሙርት ግን ከበውት ሳሉ፥ ተነስቶ ወደ ከተማ ገባ። በነገውም ከበርናባስ ጋር ወደ ደርቤን ወጣ።

21በዚያችም ከተማ ወንጌልን ሰብከው እጅግ ደቀ መዛሙርትን ካደረጉ በኋላ፥ የደቀ መዛሙርትን ልብ እያጸኑ በሃይማኖትም ጸንተው እንዲኖሩ እየመከሩና፦ “ወደ እግዚአብሔር መንግሥት በብዙ መከራ እንገባ ዘንድ ያስፈልገናል፡” እያሉ፥ ወደ ልስጥራን ወደ ኢቆንዮንም ወደ አንጾኪያም ተመለሱ።

23በየቤተ ክርስቲያኑም ሽማግሌዎችን ከሾሙላቸው በኋላ ጦመውም ከጸለዩ በኋላ፥ ላመኑበት ለጌታ አደራ ሰጡአቸው።

24በጲስድያም አልፈው ወደ ጵንፍልያ መጡ፥

25በጴርጌንም ቃሉን ከተናገሩ በኋላ ወደ አጣልያ ወረዱ፥

26ከዚያም ስለ ፈጸሙት ሥራ ለእግዚአብሔር ጸጋ አደራ ወደ ተሰጡበት ወደ አንጾኪያ በመርከብ ሄዱ።

27በደረሱም ጊዜ ቤተ ክርስቲያኑን ሰብስበው እግዚአብሔር ከእነርሱ ጋር ያደረገውን ሁሉ ለአሕዛብም የሃይማኖትን ደጅ እንደ ከፈተላቸው ተናገሩ።

28ከደቀ መዛሙርትም ጋር አያሌ ቀን ተቀመጡ።

ማብራሪያ

14:1-7 ሐዋርያት በጣም በግልጽ፣ በመንፈስ ቅዱስ እንደዚህ ባለ ማረጋገጫና ማስረጃ እንዲሁም እንደዚህ ባለ ኃይል፤ በብርቱ ቅንዓትና ለሰዎች ነፍሳት ባላቸው እንደዚህ ያለ ጥልቅ ስጋት ተናገሩ፤ የሰሙአቸውም በእርግጥ እግዚአብሔር ከእነርሱ ጋር ነበር ከማለት በቀር አልቻሉም ነበር። ሆኖም ስኬቱ ለስብከታቸው መንገድ የተሰጠ ሳይሆን ያንን መንገድ ለተጠቀመው ለእግዚአብሔር መንፈስ የተሰጠ ነው። በአደጋዎችና በችግሮች መካከል መልካም በማድረግ መጽናት የጸጋ የተባረከ ማስረጃ ነው። የእግዚአብሔር አገልጋዮች የትም ቢሰደዱ እውነትን ለመናገር መጣር አለባቸው። በክርስቶስ ስምና ኃይል ሲቀጥሉ፣ እርሱም ለጸጋው ቃል ምስክርነት ከመስጠት ወደኋላ አላለም። እርሱ የእግዚአብሔር ቃል እንደሆነ አረጋግጦልናል፣ እኛም ነፍሳችንን በእርሱ ላይ ልንታመንበት እንችላለን። አሕዛብና አይሁድ እርስ በእርስ ጠላትነት ነበራቸው፣ ሆኖም ግን በክርስትያኖች ላይ አንድ ሆኑ። የቤተ ክርስቲያን ጠላቶች ለማጥፋት ቢተባበሩ፣ ወዳጆቿስ ለመጠበቅዋ አንድ መሆን የለባቸውምን? እግዚአብሔር ለሕዝቡ በማዕበል ውስጥ መጠጊያ አለው፤ እርሱም መሸሸጊያቸው ነው፣ ይሆናልም። በስደት ዘመን አማኞች የመምህራቸውን ሥራ ባይተዉም እንኳ አንድን ቦታ ለመልቀቅ ምክንያት ሊያገኙ ይችላሉ።

14:8-18 ለሚያምኑ ሁሉ ነገር ይቻላል። እጅግ ውድ የሆነውን የእግዚአብሔርን ስጦታ እምነት ሲኖረን፣ ከተወለድንበት መንፈሳዊ አቅመ ቢስነት እና ከዚያም ወዲህ ከተፈጠሩት የኃጢአት ልማዶች አገዛዝ ነፃ እንወጣለን፤ በጌታ መንገድ ቀና ብለን ለመቆም እና በደስታ ለመሄድ እንበቃለን። የእግዚአብሔር ልጅ ክርስቶስ በሰው አምሳል ተገልጦ ብዙ ተአምራትን ባደረገ ጊዜ፣ ሰዎች ለእርሱ መስዋዕት ከማድረግ የራቁ ከመሆናቸው የተነሳ ለትዕቢታቸውና ለክፋታቸው መስዋዕት አደረጉት፤ ጳውሎስና በርናባስ ግን አንድ ተአምር ባደረጉ ጊዜ እንደ አማልክት ተቆጠሩ።

ሙሉ ማብራሪያውን ያንብቡ ድምፅ፣ ሙሉ ማብራሪያ እና ከመስመር ውጭ ንባብ

ትርጉሞች8 · 6

ENGNIV At Iconium Paul and Barnabas went as usual into the Jewish synagogue. There they spoke so effectively that a great numb… English BCV ከምኡ ድማ ኣብ ኢቆንዮን፥ ጳውሎስን በርናባስን፥ ኣብ ቤተ ፀሎት ኣይሁድ(ሀ) ኣትዮም፥ ብዙሓት ኣይሁድን ግሪካውያንን ክሳዕ ዝኣምኑ ሰበኹ። ትግርኛ GAZBIB Phaawulosii fi Baarnaabaas mandara Iqoniiyumittis akkasuma mana sagadaa warra Yihudootaatti lixanii akki isaan itti lal… Afaan Oromoo BCV GIZ ወበሀገረ ኢቆንዮን ቦኡ ምኵራበ አይሁድ ወአረሚ ወነገሩ ዘከመ ይነግሩ ዘልፈ እስከ አምኑ ብዙኃን ጥቀ እምአይሁድ ወእምአረሚኒ። giz GAZGAZ Phaawulosii fi Baarnaabaas mandara Iqoniiyumittis akkasuma mana sagadaa warra Yihudootaatti lixanii akki isaan itti lal… Afaan Oromoo BCV aksum ከምኡ ድማ ኣብ ኢቆንዮን፥ ጳውሎስን በርናባስን፥ ኣብ ቤተ ፀሎት ኣይሁድ(ሀ) ኣትዮም፥ ብዙሓት ኣይሁድን ግሪካውያንን ክሳዕ ዝኣምኑ ሰበኹ። ትግርኛ AMHNIV በኢቆንዮንም ጳውሎስና በርናባስ አብረው ወደ አይሁድ ምኵራብ ገቡ፤ በዚያም በሚገባ ስላስተማሩ፣ ከአይሁድም ከግሪክም እጅግ ብዙ ሰዎች አመኑ። አማርኛ SWAHSUV Ikawa huko Ikonio wakaingia pamoja katika sinagogi la Wayahudi; na kwa vile walivyonena, kundi kubwa la Wayahudi na la … Kiswahili