የሐዋርያት ሥራ 13

AMHNIVአማርኛ52 ጥቅሶች9:09 አዳምጥ
አዳምጥ 9:09 · መደበኛ · አስደናቂ በBiblight ይክፈቱ

1በአንጾኪያ ባለችው ቤተ ክርስቲያን ነቢያትና መምህራን ነበሩ፤ እነርሱም፦ በርናባስ፣ ኔጌር የተባለው ስምዖን፣ የቀሬናው ሉክዮስ፣ የአራተኛው ክፍል ገዥ የሄሮድስ አብሮ አደግ የነበረው ምናሔና ሳውል ነበሩ።

2እነዚህም ጌታን እያመለኩና እየጾሙ ሳሉ፣ መንፈስ ቅዱስ፣ “በርናባስንና ሳውልን እኔ ለጠራኋቸው ሥራ ለዩልኝ” አለ።

3እነርሱም ከጾሙና ከጸለዩ በኋላ እጃቸውን ጭነው አሰናበቷቸው።

4በርናባስና ሳውልም በመንፈስ ቅዱስ ተልከው ወደ ሴሌውቅያ ወረዱ፤ ከዚያም በመርከብ ወደ ቆጵሮስ ሄዱ።

5ስልማና በደረሱም ጊዜ በአይሁድ ምኵራቦች የእግዚአብሔርን ቃል ሰበኩ፤ ዮሐንስም አብሮአቸው ሆኖ ይረዳቸው ነበር።

6የቆጵሮስን ደሴት ከዳር እስከ ዳር አቋርጠው ጳፉ በደረሱ ጊዜ፣ በርያሱስ የተባለ አንድ አይሁዳዊ ጠንቋይና ሐሰተኛ ነቢይ አገኙ፤

7እርሱም ሰርግዮስ ጳውሎስ ከተባለው አስተዋይ አገረ ገዥ ጋር ነበረ። ይህ አገረ ገዥ፣ የእግዚአብሔርን ቃል ለመስማት ፈልጎ በርናባስንና ሳውልን አስጠራቸው።

8ጠንቋዩ ኤልማስ ግን፣ የስሙ ትርጒም እንዲህ ነበርና፣ አገረ ገዡ እንዳያምን ለማደናቀፍ ስለ ፈለገ ተቃወማቸው።

9ጳውሎስ የተባለውም ሳውል በመንፈስ ቅዱስ ተሞልቶ፣ ትኵር ብሎ ተመለከተውና እንዲህ አለው፤

10“አንተ የጽድቅ ሁሉ ጠላት፣ ተንኰልንና ክፋትን ሁሉ የተሞላህ የዲያብሎስ ልጅ የጌታን ቀና መንገድ ከማጣመም አታርፍምን?

11አሁንም የጌታ እጅ በአንተ ላይ ነው፤ ዕውር ትሆናለህ፤ ከእንግዲህ የፀሓይን ብርሃን ለአንድ አፍታ እንኳ አታይም።” ወዲያውም ጭጋግና ጨለማ በላዩ ወረደ፤ እጁን ይዞ የሚመራውንም ሰው ለመፈለግ ወዲያ ወዲህ ይል ጀመር።

12አገረ ገዡም የሆነውን ነገር ባየ ጊዜ፣ በጌታ ትምህርት በመደነቅ አመነ።

13ጳውሎስና ጓደኞቹ ከጳፉ ተነሥተው በጵንፍልያ ወደምትገኘው ወደ ጴርጌን ሄዱ፤ ዮሐንስም ከእነርሱ ተለይቶ ወደ ኢየሩሳሌም ተመለሰ።

14እነርሱ ግን ከጴርጌን ተነሥተው በጲስድያ ውስጥ ወዳለችው ወደ አንጾኪያ ሄዱ፤ በሰንበት ቀንም ወደ ምኵራብ ገብተው ተቀመጡ።

15የሕግና የነቢያት መጻሕፍት ከተነበቡ በኋላ፣ የምኵራብ አለቆች፣ “ወንድሞች ሆይ፤ ሕዝቡን የሚመክር ቃል ካላችሁ ተናገሩ” ሲሉ ላኩባቸው።

16ጳውሎስም ተነሥቶ በእጁ በመጥቀስ እንዲህ አለ፤ “የእስራኤል ሰዎች ሆይ፤ ደግሞም እናንት እግዚአብሔርን የምትፈሩ ሁሉ፤ አድምጡ።

17የዚህ የእስራኤል ሕዝብ አምላክ፣ አባቶቻችንን መረጣቸው፤ በግብፅ ምድር እያሉም ከፍ ከፍ አደረጋቸው፤ በኀያል ክንዱም ከዚያ አወጣቸው።

18አርባ ዓመት ያህልም በበረሓ ታገሣቸው፤

19በከነዓን ምድር የነበሩትንም ሰባት መንግሥታት አጥፍቶ፣ ምድራቸውን ለገዛ ሕዝቡ ርስት አድርጎ አወረሳቸው።

20ይህም ሁሉ የተፈጸመው በአራት መቶ አምሳ ዓመት ያህል ጊዜ ውስጥ ነበር። “ከዚህ በኋላ፣ እስከ ነቢዩ ሳሙኤል ዘመን ድረስ መሳፍንትን ሰጣቸው።

21ከዚያም ሕዝቡ ንጉሥ እንዲያነግሥላቸው ለመኑት፤ እግዚአብሔርም ከብንያም ወገን፣ የቂስን ልጅ ሳኦልን ሰጣቸው፤ እርሱም አርባ ዓመት ገዛቸው።

22ሳኦልንም ከሻረው በኋላ፣ ዳዊትን አነገሠላቸው፤ ስለ እርሱም፣ ‘እንደ ልቤ የሆነና እኔ የምሻውን ሁሉ የሚያደርግ የእሴይን ልጅ ዳዊትን አገኘሁ’ ሲል መሰከረለት።

23እግዚአብሔርም በገባው ቃል መሠረት ከዚህ ሰው ዘር አዳኝ የሆነውን ኢየሱስን ለእስራኤል አመጣ።

24ኢየሱስ ከመምጣቱ በፊት፣ ዮሐንስ የእስራኤል ሕዝብ ሁሉ ንስሓ ገብተው እንዲጠመቁ ሰብኮላቸው ነበር።

25ዮሐንስ ተልእኮውን በማጠናቀቅ ላይ ሳለ፣ ‘እኔ ማን መሰልኋችሁ? እኔ እኮ እርሱ አይደለሁም፤ ነገር ግን የእግሩን ጫማ እንኳ መፍታት የማይገባ ከእኔ በኋላ ይመጣል’ ይል ነበር።

26“እናንት ከአብርሃም ዘር የተወለዳችሁ ወንድሞች፤ ደግሞም በመካከላችሁ እግዚአብሔርን የሚፈሩ ሁሉ፤ ይህ የድነት መልእክት የተላከው ለሁላችንም ነው።

27የኢየሩሳሌም ሰዎችና አለቆቻቸው ኢየሱስን አላወቁትም፤ ይሁን እንጂ በየሰንበቱ የሚነበበው የነቢያት ቃል እንዲፈጸም በእርሱ ፈረዱበት።

28ለሞት የሚያበቃው አንድም ምክንያት ባያገኙበትም እንኳ ጲላጦስ የሞት ፍርድ እንዲፈርድበት ተማጸኑት።

29ስለ እርሱ የተጻፈውን ሁሉ ከፈጸሙ በኋላ ከተሰቀለበት ዕንጨት አውርደው በመቃብር ውስጥ አስገቡት።

30እግዚአብሔር ግን ከሙታን አስነሣው።

31ከገሊላ ጀምሮ እስከ ኢየሩሳሌም ከእነርሱ ጋር ለነበሩትም ብዙ ቀን ታያቸው፤ እነርሱም አሁን ለሕዝቡ ምስክሮቹ ናቸው።

32“እኛም እግዚአብሔር ለአባቶች ቃል የገባውን የምሥራች ቃል ለእናንተ እንሰብካለን፤

33ኢየሱስንም ከሙታን በማስነሣቱ ለእነርሱ የገባውን ቃል ለእኛ ለልጆቻቸው ፈጽሞአል፤ ይኸውም በሁለተኛው መዝሙር እንዲህ ተብሎ ተጽፎአል፤ “ ‘አንተ ልጄ ነህ፤ እኔ ዛሬ ወለድሁህ።’

34ደግሞም፣ እርሱ እንዳልበሰበሰና እግዚአብሔርም ከሙታን እንዳስነሣው ለማረጋገጥ እንዲህ ብሎአል፤ “ ‘የተቀደሰውንና የታመነውን፣ የዳዊትን በረከት እሰጣችኋለሁ።’

35ስለዚህ በሌላም ስፍራ፣ “ ‘ቅዱስህ መበስበስን እንዲያይ አትፈቅድም’ ይላል።

36“ዳዊት በራሱ ዘመን የእግዚአብሔርን ፈቃድ ካገለገለ በኋላ አንቀላፍቶአል፤ ከአባቶቹም ጋር ተቀብሮ ሥጋው በስብሶአል።

37እግዚአብሔር ከሙታን ያስነሣው እርሱ ግን መበስበስን አላየም።

38እንግዲህ ወንድሞች ሆይ፤ የኀጢአት ይቅርታ የሚገኘው በኢየሱስ በኩል መሆኑ እንደ ተሰበከላችሁ ዕወቁ፤

39በእርሱ የሚያምን ሁሉ በሙሴ ሕግ በኩል ማግኘት ያልተቻለውን ጽድቅ ያገኛል።

40ስለዚህ ነቢያት እንዲህ ብለው የተናገሩት እንዳይደርስባችሁ ተጠንቀቁ፤

41“ ‘እናንት ፌዘኞች፤ ተመልከቱ፤ ተደነቁ፤ ጥፉም፤ ማንም ቢነግራችሁ፣ የማታምኑትን ሥራ፣ እኔ በዘመናችሁ እሠራለሁና።’ ”

42ጳውሎስና በርናባስ ከምኵራብ ሲወጡ፣ ሰዎቹ ስለ ዚሁ ነገር በሚቀጥለው ሰንበት እንዲነግሯቸው ለመኗቸው።

43ጉባኤው ከተበተነ በኋላም፣ ብዙ አይሁድና ወደ ይሁዲ ሃይማኖት ገብተው በመንፈሳዊ ነገር የበረቱ ሰዎች፣ ጳውሎስንና በርናባስን ተከተሏቸው፤ እነርሱም አነጋገሯቸው፤ በእግዚአብሔርም ጸጋ ጸንተው እንዲኖሩ መከሯቸው።

44በሚቀጥለውም ሰንበት የከተማው ሕዝብ፣ ጥቂቱ ሰው ብቻ ሲቀር፣ በሙሉ የእግዚአብሔርን ቃል ለመስማት ተሰበሰቡ።

45አይሁድም ብዙ ሕዝብ ባዩ ጊዜ፣ በቅናት ተሞሉ፤ የጳውሎስንም ንግግር እየተቃወሙ ይሰድቡት ነበር።

46ጳውሎስና በርናባስም በድፍረት እንዲህ አሏቸው፤ “የእግዚአብሔር ቃል በመጀመሪያ ለእናንተ መነገር አለበት፤ እናንተ ግን ናቃችሁት፤ በዚህም የዘላለም ሕይወት እንደማይገባችሁ በራሳችሁ ላይ ስለ ፈረዳችሁ፣ እኛም ወደ አሕዛብ ዞር ለማለት እንገደዳለን።

47ደግሞም ጌታ እንዲህ ብሎ አዞናል፤ “ ‘ድነትን እስከ ምድር ዳርቻ ታደርስ ዘንድ፣ ለአሕዛብ ብርሃን አድርጌሃለሁ።’ ”

48አሕዛብ ይህን በሰሙ ጊዜ ደስ አላቸው፤ ለእግዚአብሔርም ቃል ክብርን ሰጡ፤ ለዘላለም ሕይወት የተዘጋጁትም ሁሉ አመኑ።

49የጌታም ቃል በአካባቢው ባለው አገር ሁሉ ተስፋፋ።

50አይሁድ ግን በመንፈሳዊ ነገር የተጉትንና በኑሮ የከበሩትን ሴቶች እንዲሁም የከተማውን ታላላቅ ወንዶች ቀስቅሰው በጳውሎስና በበርናባስ ላይ ስደትን አስነሡ፤ ከአገራቸውም አስወጧቸው።

51ጳውሎስና በርናባስም ተቃውሞአቸውን ለመግለጽ የእግራቸውን ትቢያ አራግፈው ወደ ኢቆንዮን ሄዱ።

52ደቀ መዛሙርቱም በደስታና በመንፈስ ቅዱስ ተሞሉ።

ማብራሪያ

13:1-3 እዚህስ እንዴት ያለ ስብስብ ነበር! በእነዚህ ስሞች ጌታ ለሥራው የሚያገለግሉትን ሰዎች ከልዩ ልዩ ስፍራዎችና የሕይወት ደረጃዎች እንደሚያስነሳ እናያለን፤ ለክብሩ ያለው ቀናኢነትም ሰዎች የእሱን ዓላማ ለማስፈጸም ብለው አስደሳች የሚመስሉ ግንኙነቶችንና የሕይወት ዕድሎችን እንዲተው ያደርጋቸዋል። የክርስቶስ አገልጋዮች ለሥራው ሙሉ በሙሉ ብቁና ፈቃደኞች የሚሆኑት በክርስቶስ መንፈስ አማካይነት ነው፤ ሥራውን ከሚያሰናክሉ ከሌሎች ጭንቀቶችም የሚለዩት በዚህ መንፈስ ነው። የክርስቶስ አገልጋዮች በክርስቶስ ሥራ ላይ ተሰማርተው፤ በመንፈስ ቅዱስ መሪነት ደግሞ ለእግዚአብሔር አብ ክብር እንዲሠሩ የታሰቡ ናቸው። ተልእኳቸው ጠንክረው መሥራት እንጂ በከፍተኛ ቦታ መቀመጥ አይደለም። በርናባስና ሳኦል አሁን በጀመሩት ሥራ ላይ በረከት ተፈልጎላቸው ነበር፤ በሥራቸውም በመንፈስ ቅዱስ እንዲሞሉ ታስቦ ነበር። ምንም ያህል ዘዴዎች ቢተገበሩ ወይም ደንቦች ቢጠበቁ፣ አገልጋዮችን ለከበረ ሥራቸው ብቁ የሚያደርጋቸውና ወደዚያ የሚጠራቸው መንፈስ ቅዱስ ብቻ ነው።

ሐዋርያት ሥራ ፲፫፥፬-፲፫ ሰይጣን በተለየ መንገድ በታላላቅ ሰዎችና በሥልጣን ላይ ባሉ ሰዎች ላይ ሃይማኖተኞች እንዳይሆኑ አጥብቆ ይተጋል፤ ምሳሌያቸው ብዙዎችን ተጽዕኖ ስለሚያደርግ ነው። ሳኦል እዚህ ለመጀመሪያ ጊዜ ጳውሎስ ተብሎ የተጠራ ሲሆን ከዚህ በኋላም ሳኦል ተብሎ አልተጠራም። ሳኦል ዕብራዊ በነበረበት ጊዜ ስሙ ሲሆን፤ ጳውሎስ ደግሞ የሮሜ ዜጋ በነበረበት ጊዜ ስሙ ነው።

በመንፈስ ቅዱስ ቀጥተኛ ምሪት ሥር ሆኖ እሊማስን እውነተኛ ማንነቱን ገለጸለት፤ ነገር ግን በስሜት ወይንም በቁጣ አልነበረም። የማታለልና የክፋት ሙላት አንድን ሰው በእርግጥ የዲያብሎስ ልጅ ያደርገዋል። የኢየሱስን ትምህርት የሚቃወሙ ሁሉ ለጽድቅ ሁሉ ጠላቶች ናቸው፤ በእርሱ (በትምህርቱ) ጽድቅ ሁሉ ስለሚፈጸም። የጌታ የኢየሱስ መንገዶች ወደ ሰማይና ወደ ደስታ የሚወስዱ ብቸኛ ትክክለኛ መንገዶች ናቸው። ከእነዚህ መንገዶች ራሳቸውን የሚስቱ ብቻ ሳይሆኑ፣ ሌሎችንም በእነዚህ መንገዶች ላይ የሚያነሳሱ ብዙዎች አሉ። በአብዛኛው ልባቸው የደነደነ ከመሆኑ የተነሳ ክፉ ከመሥራት አይታቀቡም።

አገረ ገዢው በትምህርቱ ኃይል በራሱ ልብና ህሊና ላይ ባሳደረው ተጽዕኖ፣ እንዲሁም በእግዚአብሔር ኃይል ትምህርቱ በመረጋገጡ ተደነቀ። የክርስቶስ ትምህርት ያስደንቃል፤ እናም ስለእርሱ በበለጠ በምናውቅበት ጊዜ፣ በበለጠ ለመደነቅ ምክንያት እናገኛለን። እጁን ማረሻ ላይ ጭኖ ወደ ኋላ የሚመለከት ሁሉ ለእግዚአብሔር መንግሥት ተገቢ አይደለም። ተቃውሞን ለመጋፈጥና መከራን ለመጽናት ያልተዘጋጁ ሁሉ ለአገልግሎት ሥራ ተስማሚ አይደሉም።

13:14-31 እግዚአብሔርን ልናመልክ አንድ ላይ ስንሰበሰብ፣ የምናደርገው በጸሎትና በምስጋና ብቻ ሳይሆን የእግዚአብሔርን ቃል በማንበብና በመስማትም ጭምር መሆን አለበት። ቅዱሳት መጻሕፍትን በሕዝብ ጉባኤዎች ውስጥ ዝም ብሎ ማንበብ ብቻ በቂ አይደለም፤ ሊብራሩላቸውና ሕዝቡም ከነሱ ሊመከርና ሊበረታታ ይገባል። ይህ ቃሉ ጠቃሚ እንዲሆን የሚያስፈልገውን በማድረግ፣ ሰዎች ቃሉን ለራሳቸው እንዲተገብሩት መርዳት ነው። በዚህ ስብከት ውስጥ፣ አይሁዳውያንን የተስፋውን መሲሕ ክርስቶስን እንዲቀበሉና እንዲያቅፉ በተሻለ ሁኔታ ሊያሳምናቸው የሚችል ሁሉ ተነክቷል።

ሙሉ ማብራሪያውን ያንብቡ ድምፅ፣ ሙሉ ማብራሪያ እና ከመስመር ውጭ ንባብ

ትርጉሞች8 · 6

AMHEVG በአንጾኪያም ባለችው ቤተ ክርስቲያን ነቢያትና መምህራን ነበሩ፤ እነርሱም በርናባስ፥ ኔጌር የተባለው ስምዖንም፥ የቀሬናው ሉክዮስም፥ የአራተኛው ክፍል ገዥ የሄሮድስም ባለምዋል ምናሔ፥ ሳውልም… አማርኛ ENGNIV In the church at Antioch there were prophets and teachers: Barnabas, Simeon called Niger, Lucius of Cyrene, Manaen (who… English BCV ኣብታ ኣብ ኣንፆኪያ ዝነበረት ቤተ ክርስቲያን ከዓ፥ ነቢያትን መምህራንን ነበሩ። ንሳቶም ከዓ በርናባስን፥ እቲ “ፀሊም” ተብሂሉ ዝፅዋዕ ስምኦንን፥ ሉቅዮስ ቀሬናውን፥ ምስ ገዛኢ ርባዕ ክፍሊ… ትግርኛ GAZBIB Waldaa kristiiyaanaa Anxokiyaa keessa raajonnii fi barsiisonni turan; isaanis Baarnaabaas, Simi'oon ?Isa gurraachicha? … Afaan Oromoo BCV GIZ ወሀለዉ በቤተ ክርስቲያን ዘአንጾኪያ ነቢያት ወሊቃውንት፡ በርናባስ ወስምዖን ዘተሰምየ ኔጎር፡ ወሉቅዮስ ቀሬናዊ፡ ወምናሄ ወልደ ሐፃኒቱ ለሄሮድስ ንጉሥ፡ ወሳውል። giz GAZGAZ Waldaa kristiiyaanaa Anxokiyaa keessa raajonnii fi barsiisonni turan; isaanis Baarnaabaas, Simi'oon ?Isa gurraachicha? … Afaan Oromoo BCV aksum ኣብታ ኣብ ኣንፆኪያ ዝነበረት ቤተ ክርስቲያን ከዓ፥ ነቢያትን መምህራንን ነበሩ። ንሳቶም ከዓ በርናባስን፥ እቲ “ፀሊም” ተብሂሉ ዝፅዋዕ ስምኦንን፥ ሉቅዮስ ቀሬናውን፥ ምስ ገዛኢ ርባዕ ክፍሊ… ትግርኛ SWAHSUV Na huko Antiokia katika kanisa lililokuwako palikuwa na manabii na waalimu, nao ni Barnaba, na Simeoni aitwaye Nigeri, … Kiswahili