2ኛ ቆሮንቶስ 2

AMHNIVአማርኛ17 ጥቅሶች2:53 አዳምጥ
አዳምጥ 2:53 · መደበኛ · አስደናቂ በBiblight ይክፈቱ

1እንግዲህ ላሳዝናችሁ ስላልፈለግሁ ወደ እናንተ ዳግመኛ ላለመምጣት ወሰንሁ፤

2እኔ ባሳዝናችሁም እንኳ፣ ከእናንተው ካሳዘንኋችሁ በቀር ደስ የሚያሰኘኝ ማን አለ?

3ባለፈው ጊዜ እንደዚያ የጻፍሁላችሁ ወደ እናንተ ስመጣ ደስ ሊያሰኙኝ የሚገባቸው ሰዎች እንዳያሳዝኑኝ በማለት ነው፤ ምክንያቱም የእኔ ደስታ የሁላችሁ ደስታ እንደሚሆን አምናለሁ።

4እንደዚያ ስጽፍላችሁ በትልቅ ሐዘንና በልብ ጭንቀት፣ በብዙም እንባ ውስጥ ነበርሁ፤ ይህንንም ያደረግሁት ለእናንተ ያለኝን ጽኑ ፍቅር እንድታውቁ በማለት እንጂ፣ እናንተን ለማሳዘን አልነበረም።

5ማንም ሰውን ቢያሳዝን፣ ነገር ማጋነን አይሁንብኝና ያሳዘነው እኔን ብቻ ሳይሆን በመጠኑም ቢሆን ሁላችሁንም ነው።

6እንደዚህ ያለው ሰው ብዙዎች የወሰኑበት ቅጣት በቂው ነው።

7ደግሞም ከልክ በላይ አዝኖ ተስፋ እንዳይቈርጥ፣ ይቅር ልትሉትና ልታጽናኑት ይገባችኋል።

8ስለዚህ አሁንም የምትወዱት መሆናችሁን እንድትገልጹለት እለምናችኋለሁ።

9የጻፍሁላችሁም፣ የሚያጋጥማችሁን ፈተና መቋቋማችሁንና በሁሉም ነገር ታዛዦች መሆናችሁን ለማወቅ ነበር።

10እናንተ ይቅር የምትሉትን ሰው እኔም ይቅር እለዋለሁ፤ በርግጥ ይቅር የምለው ነገር ካለ፣ በክርስቶስ ፊት ይቅር የምለው ስለ እናንተ ስል ነው።

11ይህንንም የምናደርገው ሰይጣን መግቢያ ቀዳዳ እንዳያገኝ ነው፤ የእርሱን ዕቅድ አንስተውምና።

12የክርስቶስን ወንጌል ለመስበክ ወደ ጢሮአዳ በሄድሁ ጊዜ፣ ጌታ በር ከፍቶልኝ ነበር፤

13ይሁን እንጂ ወንድሜን ቲቶን እዚያ ስላላገኘሁት መንፈሴ አላረፈም፤ ስለዚህ ተሰናብቻቸው ወደ መቄዶንያ ሄድሁ።

14ነገር ግን በክርስቶስ ሁል ጊዜ በድል አድራጊነት እያዞረ ለሚመራን፣ የዕውቀቱንም መዐዛ በእኛ አማካይነት በየስፍራው ለሚገልጥ አምላክ ምስጋና ይሁን፤

15ምክንያቱም በሚድኑትና በሚጠፉት መካከል ለእግዚአብሔር የክርስቶስ መዐዛ ነን።

16ለሚጠፉት ወደ ሞት የሚወስድ የሞት ሽታ፣ ለሚድኑት ግን ወደ ሕይወት የሚወስድ የሕይወት ሽታ ነን፤ ታዲያ፣ ለዚህ ብቁ የሚሆን ማን ነው?

17እኛኮ ትርፍ ለማግኘት ብለን የእግዚአብሔርን ቃል ቀላቅለው እንደሚሸቃቅጡት እንደ ብዙዎቹ አይደለንም፤ ነገር ግን ከእግዚአብሔር እንደተላኩ ሰዎች በክርስቶስ ሆነን በእግዚአብሔር ፊት በቅንነት እንናገራለን።

ማብራሪያ

2:1-4 ሐዋርያው ከእነርሱ ጋር ደስ የሚያሰኝ መገናኘት እንዲኖረው ምኞቱ ነበር፤ ለራሳቸውም ሆነ ለእርሱም መጽናኛ የሚሆነውን ነገር እንደሚያደርጉ በሙሉ እምነት ጽፎላቸው ነበር፤ ስለዚህም ከእርሱ ዘንድ ማንኛውንም የጭንቀት ምክንያት ለማስወገድ በደስታ ፈቃደኞች እንደሚሆኑ ነበር። ህመምን መስጠት ግዴታ በሚሆንበት ጊዜም እንኳ፣ ሁልጊዜም በፈቃደኝነት ሳይሆን በልዩ ጥንቃቄ ልናደርገው ይገባል።

2:5-11 ሐዋርያው፣ በስህተት የነበረውን ሰው ስህተቱን ተገንዝቦ በቅጣቱም እጅግ አዝኖ ስለነበር፣ እንደገና ወደ ህብረታቸው እንዲቀበሉት ይመኛል። ስለ ኃጢአት የሚሰማ ሐዘን እንኳ ለሌሎች ግዴታዎች ብቁ እንዳያደርግና ወደ ተስፋ መቁረጥ እንዳይመራ መጠንቀቅ ይገባል። ሰይጣን ንስሐ የገባውን ሰው ስለ እግዚአብሔርና ስለ ሃይማኖት ክፉ ነገር እንዲያስብ በመፈተንና ወደ ተስፋ መቁረጥ በመምራት ጥቅም እንዳያገኝ አደጋ እንደነበረ ሁሉ፣ በክርስቲያኖች ላይ ደግሞ ይቅር የማይሉ እንደሆኑ ክፉ ወሬ በማምጣት፣ መከፋፈልን በመፍጠርና የአገልግሎቱን ስኬት በማደናቀፍ በክርስቶስ አብያተ ክርስቲያናትና በአገልጋዮቹ ላይም…

ሙሉ ማብራሪያውን ያንብቡ ድምፅ፣ ሙሉ ማብራሪያ እና ከመስመር ውጭ ንባብ

ትርጉሞች8 · 6