2ኛ ቆሮንቶስ 2

AMHEVGአማርኛ17 ጥቅሶች2:19 አዳምጥ
አዳምጥ 2:19 · መደበኛ · አስደናቂ በBiblight ይክፈቱ

1ነገር ግን ዳግመኛ በኀዘን ወደ እናንተ እንዳልመጣ ስለ እኔ ቆረጥሁ።

2እኔስ ባሳዝናችሁ፥ እንግዲያስ በእኔ ምክንያት ከሚያዝን በቀር ደስ የሚያሰኘኝ ማን ነው?

3ደስ ሊያሰኙኝ ከሚገባቸውም በመምጣቴ ኀዘን እንዳይሆንብኝ ይህንኑ ጻፍሁላችሁ፥ ደስታዬ የሁላችሁ ደስታ ነው ብዬ በሁላችሁ ታምኜአለሁና።

4በብዙ መከራና ከልብ ጭንቀት በብዙም እንባ ጽፌላችሁ ነበርና፤ ይህም እናንተን አብዝቼ የምወድበትን ፍቅር እንድታውቁ እንጂ እንዳሳዝናችሁ አይደለም።

5ነገር ግን ማንም አሳዝኖ ቢሆን፥ እንዳልከብድባችሁ፥ በክፍል ሁላችሁን እንጂ እኔን ያሳዘነ አይደለም።

6እንደዚህ ላለ ሰው ይህ ከእናንተ የምትበዙት የቀጣችሁት ቅጣት ይበቃዋልና እንደዚህ ያለው ከልክ በሚበዛ ኀዘን እንዳይዋጥ፥

7ይልቅ ተመልሳችሁ ይቅር ማለትና ማጽናናት ይገባችኋል።

8ስለዚህ ከእርሱ ጋር ፍቅርን እንድታጸኑ እለምናችኋለሁ፤

9ስለዚህ ደግሞ ጽፌ ነበርና፤ በሁሉ የምትታዘዙ እንደ ሆናችሁ የእናንተን መፈተን አውቅ ዘንድ አሳቤ ነበር።

10እናንተ ግን ይቅር የምትሉትን እኔ ደግሞ ይቅር እለዋለሁ፤ እኔም ይቅር ካልሁ፥ ይቅር ያልሁትን ስለ እናንተ በክርስቶስ ፊት ይቅር ብዬአለሁ፥

11በሰይጣን እንዳንታለል፤ የእርሱን አሳብ አንስተውምና።

12ስለ ክርስቶስም ወንጌል ወደ ጢሮአዳ በመጣሁ ጊዜ፥ ለጌታ ሥራ በር ምንም ቢከፈትልኝ፥ ቲቶን ወንድሜን ስላላገኘሁት መንፈሴ ዕረፍት አልነበረውም፥

13ነገር ግን ከእነርሱ ተሰናብቼ ወደ መቄዶንያ ወጣሁ።

14ነገር ግን በክርስቶስ ሁልጊዜ ድል በመንሣቱ ለሚያዞረን በእኛም በየስፍራው ሁሉ የእውቀቱን ሽታ ለሚገልጥ ለአምላክ ምስጋና ይሁን፤

15በሚድኑቱና በሚጠፉቱ ዘንድ ለእግዚአብሔር የክርስቶስ መዓዛ ነንና፤

16ለእነዚህ ለሞት የሚሆን የሞት ሽታ ለእነዚያም ለሕይወት የሚሆን የሕይወት ሽታ ነን። ለዚህም ነገር የሚበቃ ማን ነው?

17የእግዚአብሔርን ቃል ቀላቅለው እንደሚሸቃቅጡት እንደ ብዙዎቹ አይደለንምና፤ በቅንነት ግን ከእግዚአብሔር እንደ ተላክን በእግዚአብሔር ፊት በክርስቶስ ሆነን እንናገራለን።

ማብራሪያ

2:1-4 ሐዋርያው ከእነርሱ ጋር ደስ የሚያሰኝ መገናኘት እንዲኖረው ምኞቱ ነበር፤ ለራሳቸውም ሆነ ለእርሱም መጽናኛ የሚሆነውን ነገር እንደሚያደርጉ በሙሉ እምነት ጽፎላቸው ነበር፤ ስለዚህም ከእርሱ ዘንድ ማንኛውንም የጭንቀት ምክንያት ለማስወገድ በደስታ ፈቃደኞች እንደሚሆኑ ነበር። ህመምን መስጠት ግዴታ በሚሆንበት ጊዜም እንኳ፣ ሁልጊዜም በፈቃደኝነት ሳይሆን በልዩ ጥንቃቄ ልናደርገው ይገባል።

2:5-11 ሐዋርያው፣ በስህተት የነበረውን ሰው ስህተቱን ተገንዝቦ በቅጣቱም እጅግ አዝኖ ስለነበር፣ እንደገና ወደ ህብረታቸው እንዲቀበሉት ይመኛል። ስለ ኃጢአት የሚሰማ ሐዘን እንኳ ለሌሎች ግዴታዎች ብቁ እንዳያደርግና ወደ ተስፋ መቁረጥ እንዳይመራ መጠንቀቅ ይገባል። ሰይጣን ንስሐ የገባውን ሰው ስለ እግዚአብሔርና ስለ ሃይማኖት ክፉ ነገር እንዲያስብ በመፈተንና ወደ ተስፋ መቁረጥ በመምራት ጥቅም እንዳያገኝ አደጋ እንደነበረ ሁሉ፣ በክርስቲያኖች ላይ ደግሞ ይቅር የማይሉ እንደሆኑ ክፉ ወሬ በማምጣት፣ መከፋፈልን በመፍጠርና የአገልግሎቱን ስኬት በማደናቀፍ በክርስቶስ አብያተ ክርስቲያናትና በአገልጋዮቹ ላይም…

ሙሉ ማብራሪያውን ያንብቡ ድምፅ፣ ሙሉ ማብራሪያ እና ከመስመር ውጭ ንባብ

ትርጉሞች8 · 6