1ኛ ጢሞቴዎስ 4

AMHNIVአማርኛ16 ጥቅሶች2:42 አዳምጥ
አዳምጥ 2:42 · መደበኛ · አስደናቂ በBiblight ይክፈቱ

1በኋለኞች ዘመናት አንዳንዶች እምነትን ክደው አታላይ መናፍስትንና የአጋንንትን ትምህርት እንደሚከተሉ መንፈስ በግልጥ ይናገራል።

2እንዲህ ያለው ትምህርት የሚመጣው ኅሊናቸው በጋለ ብረት የተጠበሰ ያህል ከደነዘዘባቸው ግብዝ ውሸተኞች ነው።

3እነርሱ፣ ሰዎች እንዳያገቡ ይከለክላሉ፤ የሚያምኑና እውነትን የሚያውቁ ሰዎች እግዚአብሔር የፈጠረውን በምስጋናም የሚቀበሉትን እንዳይበሉ ያዛሉ፤

4እግዚአብሔር የፈጠረው ማንኛውም ነገር መልካም ነውና፤ በምስጋና ከተቀበሉትም የሚጣል ምንም ነገር የለም፣

5በእግዚአብሔር ቃልና በጸሎት የተቀደሰ ነውና።

6ይህን ትእዛዝ ለወንድሞች ብታሳስብ፣ በእምነት ቃልና በተቀበልኸው መልካም ትምህርት ታንጸህ የክርስቶስ ኢየሱስ በጎ አገልጋይ ትሆናለህ።

7እግዚአብሔርን ከማያከብር ርባናቢስ አፈ ታሪክና ከአሮጊቶች ተረታ ተረት ራቅ፤ ይልቁንም ለእውነተኛ መንፈሳዊ ሕይወት ራስህን አሠልጥን።

8የአካል ብቃት ልምምድ ለጥቂት ነገር ይጠቅማልና፤ ለእውነተኛ መንፈሳዊ ሕይወት ራስን ማሠልጠን ግን ለአሁኑም ሆነ ለሚመጣው ሕይወት ተስፋ ስላለው ለሁለቱም ይጠቅማል።

9ይህ ቃል የታመነና ሙሉ ለሙሉ ሊቀበሉት የሚገባ ነው፤

10ለዚህ ብለን እንጥራለን፤ እንደክማለንም፤ ይኸውም ለሰዎች ሁሉ በተለይም ለሚያምኑት አዳኝ በሆነው በሕያው እግዚአብሔር ተስፋ ስለምናደርግ ነው።

11እነዚህን ነገሮች እዘዝ፤ አስተምርም።

12ወጣትነትህን ማንም አይናቅ፤ ነገር ግን ለሚያምኑት በንግግርና በኑሮ፣ በፍቅር፣ በእምነትና በንጽሕና አርኣያ ሁንላቸው።

13እኔ እስክመጣ ድረስ ለማንበብ፣ ለመምከርና ለማስተማር ትጋ።

14ሽማግሌዎች እጃቸውን በአንተ ላይ ሲጭኑ በትንቢት የተሰጠህን የጸጋ ስጦታ ቸል አትበል።

15ሰው ሁሉ ማደግህን ያይ ዘንድ በእነዚህ ነገሮች ላይ አትኵር፤ በትጋትም ፈጽማቸው፤

16ለሕይወትህና ለትምህርትህ ተጠንቀቅ፤ በእነዚህም ጽና፤ ይህን ብታደርግ፣ ራስህንና የሚሰሙህንም ታድናለህና።

ማብራሪያ

4:1-5 መንፈስ ቅዱስ በብሉይ ኪዳንም በአዲስ ኪዳንም ከክርስቶስ እምነትና ከእግዚአብሔር ንጹህ አምልኮ አጠቃላይ መዘንበል እንደሚኖር ተናግሯል። ይህ የሚከሰተው በወንጌል ዘመን ነው፣ ምክንያቱም እነዚያ የመጨረሻዎቹ ቀናት ተብለዋልና። ሐሰተኛ አስተማሪዎች እግዚአብሔር የፈቀደውን እንደ ክፉ ይከለክላሉ፤ እርሱ ግድ ያልሰጠበትን (ወይም ያላዘዘውን/ያልከለከለውን) ደግሞ እንደ ግዴታ ያዝዛሉ። እግዚአብሔር የፈቀደውን የሚጥሉ በምናባዊ ግዴታዎች ሳንታሰር፣ የእግዚአብሔርን ሕግ መስፈርቶች በመፈጸም፣ ለንቃትና ራስን ለመካድ ልምምድ እናገኛለን። ነገር ግን የነገሮችን ልክ ያለፈ ወይም ተገቢ ያልሆነ አጠቃቀምን ምንም አያጸድቅም፤ በጸሎትም የእግዚአብሔርን በረከት በእርሱ ላይ ካልፈለግን በቀር ምንም ነገር መልካም አይሆንልንም።

4:6-10 የውጫዊ ራስን የመካድ ተግባራት ብዙም አይጠቅሙም። ሥጋን ብንገድልስ፣ ኃጢአትን ካልገደልን ምን ይጠቅመናል? በባዶ ውጫዊ ነገሮች ላይ የሚደረግ ምንም ዓይነት ትጋት ብዙም ጥቅም ሊኖረው አይችልም።

ሙሉ ማብራሪያውን ያንብቡ ድምፅ፣ ሙሉ ማብራሪያ እና ከመስመር ውጭ ንባብ

ትርጉሞች8 · 6

AMHEVG መንፈስ ግን በግልጥ፦ “በኋለኞች ዘመናት አንዳንዶች የሚያስቱ መናፍስትንና በውሸተኞች ግብዝነት የተሰጠውን የአጋንንትን ትምህርት እያደመጡ፥ ሃይማኖትን ይክዳሉ፡” ይላል፤ በገዛ ሕሊናቸው እን… አማርኛ ENGNIV The Spirit clearly says that in later times some will abandon the faith and follow deceiving spirits and things taught … English BCV በቲ ዳሕረዋይ ዘመን ግና፥ ገሊኣቶም እምነቶም ክሒዶም፥ ንመታለልቲ መናፍስትን፥ ንትምህርቲ ኣጋንንትን ከም ዝስዕቡ፥ መንፈስ ብገሃድ ይነግር ኣሎ። ትግርኛ GAZBIB Bara booddetti namoonni tokko hafuurota wallaalchisoodhaa fi barsiisa hafuurota hamootaa duukaa bu'anii, amantii wangee… Afaan Oromoo BCV GIZ ወመንፈስ ገሃደ ይነግር ከመ በደኃሪ መዋዕል የዐልዉ ሃይማኖቶሙ ብዙኃን ወይተልውዎሙ ለአጋንንት እኩያን ወመስሕታን ወትምህርተ ሰይጣን ዘያናፍቅ። giz GAZGAZ Bara booddetti namoonni tokko hafuurota wallaalchisoodhaa fi barsiisa hafuurota hamootaa duukaa bu'anii, amantii wangee… Afaan Oromoo BCV aksum በቲ ዳሕረዋይ ዘመን ግና፥ ገሊኣቶም እምነቶም ክሒዶም፥ ንመታለልቲ መናፍስትን፥ ንትምህርቲ ኣጋንንትን ከም ዝስዕቡ፥ መንፈስ ብገሃድ ይነግር ኣሎ። ትግርኛ SWAHSUV Basi Roho anena waziwazi ya kwamba nyakati za mwisho wengine watajitenga na imani, wakisikiliza roho zidanganyazo, na m… Kiswahili