1ኛ ተሰሎንቄ 4

AMHNIVአማርኛ18 ጥቅሶች2:59 አዳምጥ
አዳምጥ 2:59 · መደበኛ · አስደናቂ በBiblight ይክፈቱ

1በቀረውስ ወንድሞች ሆይ፤ እግዚአብሔርን ደስ ለማሰኘት እንዴት መኖር እንደሚገባችሁ አስተምረናችኋል፤ በርግጥም እንደዚያው እየኖራችሁ ነው። ስለ ሆነም በጌታ በኢየሱስ የምንለምናችሁና የምንመክራችሁ ከዚህ በበለጠ ሁኔታ በዚሁ እንድትገፉበት ነው።

2በጌታ በኢየሱስ ሥልጣን ምን ዐይነት ትእዛዝ እንደ ሰጠናችሁ ታውቃላችሁ።

3የእግዚአብሔር ፈቃድ ከዝሙት ርቃችሁ እንድትቀደሱ ነው፤

4ደግሞም እያንዳንዱ የገዛ ሰውነቱን በቅድስናና በክብር መያዝ እንዳለበት እንዲያውቅ ነው፤

5ይህም እግዚአብሔርን እንደማያውቁ አሕዛብ በፍትወተ ሥጋ ምኞት አይሁን።

6በዚህም ነገር ማንም ተላልፎ ወንድሙን አያታል፤ ምክንያቱም ከዚህ በፊት እንደነገርናችሁና እንዳስጠነቀቅናችሁ ጌታ እንደ እነዚህ ያለውን ኀጢአት ሁሉ የሚፈጽሙትን ይበቀላል፤

7እግዚአብሔር በቅድስና እንድንመላለስ እንጂ ለርኵሰት አልጠራንምና።

8እንግዲህ ይህን ምክር ንቆ የማይቀበል፣ የናቀው ቅዱስ መንፈሱን የሰጣችሁን እግዚአብሔርን እንጂ ሰውን አይደለም።

9ስለ ወንድማማች መዋደድ ማንም እንዲጽፍላችሁ አያስፈልግም፤ ምክንያቱም እርስ በርሳችሁ እንድትዋደዱ እናንተ ራሳችሁ ከእግዚአብሔር ተምራችኋልና።

10በመላዪቱ መቄዶንያ የሚገኙትን ወንድሞች ሁሉ እንደምትወዷቸው የታወቀ ነው፤ ነገር ግን ወንድሞች ሆይ፤ ከዚህ በበለጠ እንድትገፉበት እንመክራችኋለን።

11ከዚህ በፊት እንዳዘዝናችሁ በገዛ እጃችሁ ሥሩ፤ በጸጥታ ኑሩ፤ በራሳችሁ ጒዳይ ላይ ብቻ አተኵሩ።

12ይውም በዕለት ተለት ኑሮአችሁ በውጭ ባሉት ዘንድ እንዲያስከብራችሁና በማንም ሰው ላይ ሸክም እንዳትሆኑ ነው።

13ወንድሞች ሆይ፤ አንቀላፍተው ስላሉ ሰዎች ሳታውቁ እንድትቀሩ አንፈልግም፤ ደግሞም ተስፋ እንደሌላቸው እንደ ሌሎች ሰዎች እንድታዝኑ አንሻም።

14ኢየሱስ እንደ ሞተና እንደ ተነሣ ካመንን፣ በኢየሱስ ሆነው ያንቀላፉትን እግዚአብሔር ከእርሱ ጋር እንደዚሁ ያመጣቸዋል።

15በጌታ ቃል የምንላችሁ ይህን ነው፤ እኛ በሕይወት ያለንና ጌታ እስኪመጣ ድረስ የምንቀር ያንቀላፉትን አንቀድምም፤

16ጌታ ራሱ በታላቅ ትእዛዝ፣ በመላእክት አለቃ ድምፅና በእግዚአብሔር የመለከት ድምፅ ከሰማይ ይወርዳልና። በክርስቶስ የሞቱትም አስቀድመው ይነሣሉ።

17ከዚያም በኋላ እኛ የቀረነው፣ በሕይወትም የምንኖረው ጌታን በአየር ላይ ለመቀበል ከእነርሱ ጋር በደመና እንነጠቃለን፤ በዚህም መሠረት ለዘላለም ከጌታ ጋር እንሆናለን።

18ስለዚህ በዚህ ቃል እርስ በርሳችሁ ተጽናኑ።

ማብራሪያ

4:1-8 በወንጌል እምነት መኖር ብቻውን በቂ አይደለም፤ በእምነት ሥራ መብዛት አለብን። ሁሉም ሊመላለሱበትና ሊሠሩበት የሚገባው ሕግ በጌታ በኢየሱስ ክርስቶስ የተሰጡ ትእዛዛት ናቸው። ቅድሳት፣ ይህም ነፍሳቸው በመንፈስ ቅዱስ ተጽዕኖ ሥር መታደስና የተሰጣቸውን ተግባራት በትኩረት መፈጸም፣ እግዚአብሔር ስለእነርሱ ያለው ፈቃድ ነው። ይህንን የነፍስ ወደ ቅድስና መታደስ ለመሻት፣ ወደ ተሳሳተ አጠቃቀማቸው የሚመሩትን የሰውነት ፍላጎቶችና ስሜቶች፣ እንዲሁም የፈቃድን ሐሳቦችና ዝንባሌዎች በጥብቅ መግታት ያስፈልጋል። ጌታ ቅድስና የጎደለው ሕይወት እንዲኖሩ ማንንም ወደ ቤተሰቡ አይጠራም፤ ነገር ግን በቅድስና በፊቱ እንዲመላለሱ እንዲማሩና እንዲችሉ ነው። አንዳንዶች የቅድስናን ትእዛዛት ከሰዎች ስለሚሰሙዋቸው ቀላል አድርገው ይይዟቸዋል፤ ነገር ግን እነርሱ የእግዚአብሔር ትእዛዛት ናቸውና እነርሱን መተላለፍ እግዚአብሔርን መናቅ ነው።

4:9-12 በሌሎች ዘንድ መልካም የሆነውን ነገር ልናስተውል ይገባልና፣ ይህንም እነሱን በማወደስ ከጊዜ ወደ ጊዜ የበለጠ እንዲያድጉ ልናበረታታቸው እንችላለን። እግዚአብሔር በመዳን መንገድ ያስተማራቸው ሁሉ እርስ በእርሳቸው እንዲዋደዱ ተምረዋል። የመንፈስ ትምህርት የሰዎችን ትምህርት ይበልጣል፤ እግዚአብሔር ካላስተማረ የሰዎች ትምህርት ከንቱና ፋይዳ የሌለው ነው። በዚህ ወይም በሌላ በማንኛውም ጸጋ የላቁ ሰዎች እስከ መጨረሻው ከመጽናት ጋር፣ በእርሱም የበለጠ ማደግ ያስፈልጋቸዋል። ጸጥ ያለና የተረጋጋ መንፈስ መያዝ እንዲሁም ሰላማዊና ጸጥ ያለ ምግባር ማሳየት እጅግ የሚመኝ ነው።

ሙሉ ማብራሪያውን ያንብቡ ድምፅ፣ ሙሉ ማብራሪያ እና ከመስመር ውጭ ንባብ

ትርጉሞች8 · 6

AMHEVG እንግዲህ በቀረውስ፥ ወንድሞች ሆይ፥ ልትመላለሱ እግዚአብሔርንም ደስ ልታሰኙ እንዴት እንደሚገባችሁ ከእኛ ዘንድ እንደ ተቀበላችሁ፥ እናንተ ደግሞ እንደምትመላለሱ፥ ከፊት ይልቅ ትበዙ ዘንድ በ… አማርኛ ENGNIV Finally, brothers, we instructed you how to live in order to please God, as in fact you are living. Now we ask you and … English BCV ብዝተረፈ ኣሕዋተይ፥ ንእግዚኣብሄር ምእንቲ ኽተሐጕስዎ፥ ከመይ ጌርኩም ክትነብሩ ኸም ዝግብአኩም፥ ካባና ተምሂርኩም ኢኹም። ድሮ እኳ ትነብርዎ ኣለኹም። ሕዚ ኸዓ ነዙይ ብዝበለፀ ኽትነብርዎ፥ … ትግርኛ GAZBIB Obboloota nana! Kana irraa kan hafe immoo Waaqayyoon gammachiisuudhaaf attamitti jiraachuun akka isin irra jiru barumsa… Afaan Oromoo BCV GIZ ወይእዜኒ አኀዊነ ንነግረክሙ ወናስተበቍዐክሙ በእግዚእነ ኢየሱስ ክርስቶስ ከመ ተአዘዝክሙ በኀቤነ በዘይደሉ ከመ ትሑሩ ወታሥምርዎ ለእግዚአብሔር በከመ ሖርክሙ ዓዲ ከመ ታብዝኁ ወታፈድፍዱ በዝ… giz GAZGAZ Obboloota nana! Kana irraa kan hafe immoo Waaqayyoon gammachiisuudhaaf attamitti jiraachuun akka isin irra jiru barumsa… Afaan Oromoo BCV aksum ብዝተረፈ ኣሕዋተይ፥ ንእግዚኣብሄር ምእንቲ ኽተሐጕስዎ፥ ከመይ ጌርኩም ክትነብሩ ኸም ዝግብአኩም፥ ካባና ተምሂርኩም ኢኹም። ድሮ እኳ ትነብርዎ ኣለኹም። ሕዚ ኸዓ ነዙይ ብዝበለፀ ኽትነብርዎ፥ … ትግርኛ SWAHSUV Iliyobaki, ndugu, tunakusihini na kuwaonya kwamba mwenende katika Bwana Yesu; kama mlivyopokea kwetu jinsi iwapasavyo k… Kiswahili