1ኛ ተሰሎንቄ 3

AMHEVGአማርኛ11 ጥቅሶች2:04 አዳምጥ
አዳምጥ 2:04 · መደበኛ · አስደናቂ በBiblight ይክፈቱ

1ስለዚህ ወደ ፊት እንታገሥ ዘንድ ባልተቻለን ጊዜ፥ በአቴና ብቻችንን ልንቀር በጎ ፈቃዳችን ሆነ።

2ስለ እምነታችሁም እንዲያጸናችሁና እንዲመክራችሁ ወንድማችንን የእግዚአብሔርንም አገልጋይ ከእኛ ጋርም አብሮ በክርስቶስ ወንጌል የሚሠራውን ጢሞቴዎስን ላክነው፤

3በዚህ መከራ ማንም እንዳይናውጥ፥ ለዚህ እንደ ተመረጥን ራሳችሁ ታውቃላችሁና።

4በእውነት ከእናንተ ጋር ሳለን፥ መከራ እንቀበል ዘንድ እንዳለን አስቀድመን እንነግራችሁ ነበር፤ እንዲሁም ደግሞ ሆነ፥ ይህንም ታውቃላችሁ።

5ስለዚህ እኔ ደግሞ ወደ ፊት እታገሥ ዘንድ ባልተቻለኝ ጊዜ፦ “ፈታኝ ምናልባት ፈትኖአቸዋል ድካማችንም ከንቱ ሆኖአል፡” ብዬ እምነታችሁን ለማወቅ ላክሁ።

6አሁን ግን ጢሞቴዎስ ከእናንተ ዘንድ ወደ እኛ መጥቶ ስለ እምነታችሁና ስለ ፍቅራችሁ የምስራች ብሎ በነገረን ጊዜ፥ እኛም እናያችሁ ዘንድ እንደምንናፍቅ ታዩን ዘንድ እየናፈቃችሁ ሁልጊዜ በመልካም እንደምታስቡን በነገረን ጊዜ፥

7ስለዚህ፥ ወንድሞች ሆይ፥ በእምነታችሁ በኩል በችግራችንና በመከራችን ሁሉ ስለ እናንተ ተጽናናን፤

8እናንተ በጌታ ጸንታችሁ ብትቆሙ፥ አሁን በሕይወት እንኖራለንና።

9ፊታችሁን ልናይ በእምነታችሁም የጎደለውን ልንሞላበት ሌሊትና ቀን ከመጠን ይልቅ እየጸለይን በአምላካችን ፊት ከእናንተ የተነሣ ስለምንደሰተው ደስታ ሁሉ፥ ለእግዚአብሔር በእናንተ ምክንያት ምን ያህል ምስጋና እናስረክብ ዘንድ እንችላለን?

11አምላካችንና አባታችን ራሱ ጌታችንም ኢየሱስ ክርስቶስ ወደ እናንተ መንገዳችንን ያቅና፤

12ጌታችንም ኢየሱስ ክርስቶስ ከቅዱሳኑ ሁሉ ጋር ሲመጣ፥ በአምላካችንና በአባታችን ፊት በቅድስና ነቀፋ የሌለበት አድርጎ ልባችሁን ያጸና ዘንድ፥ እኛ ደግሞ ለእናንተ እንደምንሆን ጌታ እርስ በእርሳችሁ ያላችሁን ለሁሉም የሚሆን ፍቅራችሁን ያብዛ ይጨምርም።

ማብራሪያ

3:1-5 በእግዚአብሔር መንገዶች ደስታችን በጨመረ ቁጥር፣ በዚያ ለመጽናት ያለን ፍላጎትም ይበልጥ ይጠነክራል። የሐዋርያው ዓላማም ተሰሎንቄ ክርስቲያኖችን በእምነታቸው ዓላማ ማለትም ኢየሱስ ክርስቶስ የዓለም አዳኝ እንደሆነ፣ እንዲሁም ሁሉንም ኪሳራዎቻቸውን ሊካካስና ሁሉንም ድካሞቻቸውን ሊክስ ከበቂ በላይ በሆነው በእምነታቸው ዋጋ ሊያጸናና ሊያጽናና ነበር። ነገር ግን ድካሞቹ ከንቱ ይሆናሉ ብሎ ፈራ። ዲያብሎስ አገልጋዮችን በቃልና በትምህርት ከመድከም ሊከለክል ባይችልም፣ ከተቻለው ግን የድካሞቻቸውን ውጤት ይከለክላል። ማንም ሰው በፈቃዱ በከንቱ መሥራት አይፈልግም። ወደ መንግሥቱ የምንገባው በብዙ መከራዎች ውስጥ ሆኖ መሆኑ የእግዚአብሔር ፈቃድና ዓላማ ነው። ሐዋርያትም ሰዎችን በሃይማኖት ውስጥ ዓለማዊ ብልጽግና ይጠብቃቸዋል ብለው ከማታለል ይልቅ፣ በሥጋቸው መከራ እንደሚገጥማቸው በግልጽ ነገሯቸው። በዚህም የእምነታችን ጀማሪ የሆነውን የታላቁን ጌታቸውን ምሳሌ ተከተሉ።

ሙሉ ማብራሪያውን ያንብቡ ድምፅ፣ ሙሉ ማብራሪያ እና ከመስመር ውጭ ንባብ

ትርጉሞች8 · 6