1ኛ ተሰሎንቄ 1

AMHEVGአማርኛ8 ጥቅሶች1:39 አዳምጥ
አዳምጥ 1:39 · መደበኛ · አስደናቂ በBiblight ይክፈቱ

1ጳውሎስና ስልዋኖስ ጢሞቴዎስም፥ በእግዚአብሔር አብ በጌታ በኢየሱስ ክርስቶስም ወደምትሆን ወደ ተሰሎንቄ ሰዎች ቤተ ክርስቲያን፤ ከእግዚአብሔር ከአባታችን ከጌታ ከኢየሱስ ክርስቶስም ጸጋ ሰላምም ለእናንተ ይሁን።

2በጸሎታችን ጊዜ ስለ እናንተ ስናሳስብ፥ የእምነታችሁን ስራ የፍቅራችሁንም ድካም በጌታችንም በኢየሱስ ክርስቶስ ያለውን የተስፋችሁን መጽናት በአምላካችንና በአባታችን ፊት ሳናቋርጥ እያሰብን፥ እግዚአብሔርን ሁል ጊዜ በሁላችሁ ምክንያት እናመሰግናለን፤

4በእግዚአብሔር የምትወደዱ ወንድሞች ሆይ፥ እንደ ተመረጣችሁ አውቀናልና።

5ወንጌላችን በኃይልና በመንፈስ ቅዱስ በብዙ መረዳትም እንጂ በቃል ብቻ ወደ እናንተ አልመጣምና፤ በእናንተ ዘንድ ስለ እናንተ እንዴት እንደ ነበርን ታውቃላችሁ።

6ደግሞ እናንተ ቃሉን በብዙ መከራ ከመንፈስ ቅዱስ ደስታ ጋር ተቀብላችሁ፥ እኛንና ጌታን የምትመስሉ ሆናችሁ፤

7ስለዚህም በመቄዶንያና በአካይያ ላሉት ምእመናን ሁሉ ምሳሌ ሆናችሁላቸው።

8ከእናንተ ወጥቶ የጌታ ቃል በመቄዶንያና በአካይያ ብቻ አልተሰማምና፥ ነገር ግን ምንም እንድንናገር እስከማያስፈልግ ድረስ፥ በእግዚአብሔር ዘንድ የሚሆን እምነታችሁ በሁሉ ስፍራ ተወርቶአል።

9እነርሱ ራሳቸው ወደ እናንተ መግባታችን እንዴት እንደነበረ ስለ እኛ ይናገራሉና፤ ለሕያውና ለእውነተኛ አምላክም ታገለግሉ ዘንድ፥ ከሙታንም ያስነሳውን ልጁን እርሱንም ኢየሱስን ከሚመጣው ቍጣ የሚያድነንን ከሰማይ ትጠብቁ ዘንድ፥ ከጣዖቶች ወደ እግዚአብሔር እንዴት ዘወር እንዳላችሁ ይናገራሉ።

ማብራሪያ

1:1-5 መልካም ነገር ሁሉ ከእግዚአብሔር የሚመጣ እንደመሆኑ መጠን፣ ኃጢአተኞች መልካም ነገር ከእግዚአብሔር በክርስቶስ በቀር ከሌላ ሊጠብቁ አይችሉም። ከሁሉ የላቀው መልካም ነገርም እንደ አባታችን ከእግዚአብሔር፣ ስለ ክርስቶስ ሊጠበቅ ይገባል። እኛ ስለ ራሳችን ብቻ ሳይሆን ስለ ሌሎችም መጸለይ ይገባናል፤ ሳናቋርጥም እነርሱን ማሰብ አለብን። እውነተኛ እምነት ባለበት ሁሉ ይሰራል፤ ልብንም ሕይወትንም ይነካል። እምነት በፍቅር ይሠራል፤ ለእግዚአብሔር ባለን ፍቅርና ለባልንጀራችን ባለን ፍቅር ይገለጻል። የተመሠረተ የዘላለም ሕይወት ተስፋ ባለበት ሁሉ፣ ይህ በትዕግሥት መኖር ይገለጣል፤ በምናደርገውም ሁሉ ራሳችንን ለእግዚአብሔር ለማስደሰት ስንጥር የእውነተኛነት ምልክት ነው።

ሙሉ ማብራሪያውን ያንብቡ ድምፅ፣ ሙሉ ማብራሪያ እና ከመስመር ውጭ ንባብ

ትርጉሞች8 · 6

ENGNIV Paul, Silas and Timothy, To the church of the Thessalonians in God the Father and the Lord Jesus Christ: Grace and peac… English BCV ካብ ጳውሎስን ስልዋኖስን ጢሞቴዎስን፥ ናብታ ኣብ እግዚኣብሄር ኣቦናን፥ ኣብ ጐይታና ኢየሱስ ክርስቶስን ዘላ ቤተ ክርስቲያን ተሰሎንቄ፥ ኻብ እግዚኣብሄር ኣቦናን፥ ካብ ጐይታና ኢየሱስ ክርስቶ… ትግርኛ GAZBIB Phaawulos, Silwaanosii fi Ximotewos biraa, gara waldaa warra Tasaloniiqee isa kan Waaqayyoo abbaa fi kan gooftaa Yesus … Afaan Oromoo BCV GIZ እምጳውሎስ ወስልዋኖስ ወጢሞቴዎስ ለቤተ ክርስቲያን ዘተሰሎንቄ፤ ምእመናን በእግዚአብሔር፣ አቡነ ወእግዚእነ ኢየሱስ ክርስቶስ፣ ሰላም ለክሙ ወጸጋ እግዚአብሔር አቡነ ወእግዚእነ ኢየሱስ ክርስቶ… giz GAZGAZ Phaawulos, Silwaanosii fi Ximotewos biraa, gara waldaa warra Tasaloniiqee isa kan Waaqayyoo abbaa fi kan gooftaa Yesus … Afaan Oromoo BCV aksum ካብ ጳውሎስን ስልዋኖስን ጢሞቴዎስን፥ ናብታ ኣብ እግዚኣብሄር ኣቦናን፥ ኣብ ጐይታና ኢየሱስ ክርስቶስን ዘላ ቤተ ክርስቲያን ተሰሎንቄ፥ ኻብ እግዚኣብሄር ኣቦናን፥ ካብ ጐይታና ኢየሱስ ክርስቶ… ትግርኛ AMHNIV ከጳውሎስ፣ ከሲላስና ከጢሞቴዎስ፤ የእግዚአብሔር አብና የጌታ የኢየሱስ ክርስቶስ ለሆኑት ለተሰሎንቄ ሰዎች ቤተ ክርስቲያን፤ ከእግዚአብሔር ከአባታችን ከጌታም ከኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋና ሰላም ለ… አማርኛ SWAHSUV Paulo, na Silwano, na Timotheo, kwa kanisa la Wathesalonike, lililo katika Mungu Baba, na katika Bwana Yesu Kristo. Nee… Kiswahili