1ኛ ሳሙኤል 11

AMHNIVአማርኛ15 ጥቅሶች3:38 አዳምጥ
አዳምጥ 3:38 · መደበኛ · አስደናቂ በBiblight ይክፈቱ

1አሞናዊው ናዖስ ወጥቶ ኢያቢስ ገለዓድን ከበባት፤ የኢያቢስም ሰዎች ሁሉ፣ “ከእኛ ጋር ቃል ኪዳን አድርግ፣ እኛም እንገዛልሃለን” አሉት።

2አሞናዊው ናዖስ፣ “ከእናንተ ጋር ቃል ኪዳን የማደርገው የእያንዳንዳችሁን ቀኝ ዐይን አውጥቼ እስራኤልን ሁሉ ካዋረድሁ በኋላ ብቻ ነው” ሲል መለሰ።

3የኢያቢስም ሽማግሌዎች፣ “ወደ መላው እስራኤል መልእክተኞችን እንድንልክ የሰባት ቀን ጊዜ ስጠን፤ ሊታደገን የሚመጣ ሰው ከሌለ፣ ለአንተ እንገዛለን” አሉት።

4መልእክተኞቹም ሳኦል ወዳለበት ወደ ጊብዓ መጥተው ይህን ለሕዝቡ በተናገሩ ጊዜ፣ ሕዝቡ ሁሉ ድምፃቸውን ከፍ አድርገው አለቀሱ፤

5በዚህ ጊዜ፣ ሳኦል በሬዎቹን እየነዳ ከዕርሻ ተመለሰ፤ እርሱም፣ “ሕዝቡ የሚያለቅሰው ምን ሆኖ ነው?” ሲል ጠየቀ። እነርሱም የኢያቢስ ሰዎች ያሏቸውን ነገሩት።

6ሳኦል ይህን በሰማ ጊዜ የእግዚአብሔር መንፈስ በኀይል ወረደበት፤ እጅግ ተቈጣ።

7ጥንድ በሬዎች ወስዶ ቈራረጠ፤ ሥጋቸውንም በመልእክተኞች እጅ ልኮ፣ “ሳኦልንና ሳሙኤልን የማይከተል ሰው በሬው እንደዚህ ይቈራረጣል” ሲል በመላው እስራኤል አስነገረ። ታላቅ ፍርሀት ከእግዚአብሔር ዘንድ በሕዝቡ ላይ ወደቀ፤ ሕዝቡም እንደ አንድ ሰው ሆኖ ወጣ።

8ሳኦል ቤዜቅ በተባለ ስፍራ ሰራዊቱን በሰበሰበ ጊዜ፤ ቊጥራቸው ከእስራኤል ሦስት መቶ ሺህ፣ ከይሁዳም ሠላሳ ሺህ ነበር።

9ከዚያ ለመጡትም መልእክተኞች፣ “ለኢያቢስ ገለዓድ ሰዎች፣ ‘ነገ ፀሓይ ሞቅ በሚልበት ጊዜ ነጻ ትሆናላችሁ’ ብላችሁ ንገሯቸው” አሏቸው። መልእክተኞቹም ሄደው ለኢያቢስ ሰዎች ይህንኑ በነገሯቸው ጊዜ በደስታ ፈነደቁ።

10ለአሞናውያንም፣ “እኛ ነገ እጃችንን እንሰጣችኋለን፤ እናንተም መልካም መስሎ የታያችሁን ሁሉ ልታደርጉብን ትችላላችሁ” አሏቸው።

11በማግስቱ ሳኦል ሰራዊቱን ከሦስት ቦታ ከፈለው፤ ሊነጋጋ ሲል፣ የአሞናውያንን ሰፈር ጥሰው በመግባት ፀሓይ ሞቅ እስኪል ድረስ ፈጇቸው። በሕይወት የተረፉትም ሁለት እንኳን ሆነው በአንድ ላይ ሊሆኑ እስከማይችሉ ድረስ ተበታተኑ።

12ሕዝቡ ሳሙኤልን፣ “ሳኦል እንዴት ሊገዛን ይችላል!’ ያሉት እነማን ነበሩ? እነዚህን ሰዎች እንገድላቸው ዘንድ አምጣቸው” አሉት።

13ሳኦል ግን፣ “ይህ ዕለት እግዚአብሔር እስራኤልን የታደገበት ቀን ሰለሆነ፣ በዛሬው ዕለት ማንም ሰው አይገደልም” አለ።

14ከዚያም ሳሙኤል ሕዝቡን፣ “ኑና ወደ ጌልገላ እንሂድ፤ ንግሥናውን እናጽና” አለ።

15ሕዝቡ ሁሉ ወደ ጌልገላ ሄደ፤ የሳኦልንም ንጉሥነት በእግዚአብሔር ፊት አጸና። በዚያም ሕዝቡ የኅብረት መሥዋዕት በእግዚአብሔር ፊት አቀረበ፤ ሳኦልና እስራኤላውያንም ሁሉ ታላቅ በዓል አደረጉ።

ማብራሪያ

11:1-11 የሳኦል አገዛዝ የመጀመሪያው ፍሬ ያቤስ-ገለዓድን ከአሞናውያን ማዳን ነበር። ሕይወታቸውን ለማዳን ሲሉ ሰዎች ነጻነታቸውን ይተዋሉ፥ ዓይናቸውም እንዲወጣ እስከመፈቀድ ይደርሳሉ፤ ታዲያ እንደ ቀኝ ዓይናችን ውድ የሆነብንን ኃጢአት ትተን ከገሃነም እሳት ከመጣል መዳን ጥበብ አይደለምን? የሳኦልን እምነትና መተማመን ተመልከቱ፥ በዚያም ላይ የተመሠረተውንም ጽናቱንና ቁርጠኝነቱን። በዚህም ጉዳይ ላይ ያለውን ትጋትም ተመልከቱ።

ሙሉ ማብራሪያውን ያንብቡ ድምፅ፣ ሙሉ ማብራሪያ እና ከመስመር ውጭ ንባብ

ትርጉሞች8 · 6

AMHEVG እንዲህም ሆነ፤ ከአንድ ወር በኋላ አሞናዊው ናዖስ ወጣ፥ በኢያቢስ ገለዓድም ሰፈረ፤ የኢያቢስም ሰዎች ሁሉ፦ ቃል ኪዳን አድርግልን፥ እኛም እንገዛልሃለን፡ አሉት። አማርኛ ENGNIV Nahash the Ammonite went up and besieged Jabesh Gilead. And all the men of Jabesh said to him, “Make a treaty with us, … English BCV ከምዙይ ድማ ኾነ፦ ብድሕሪ ሓደ ወርሒ ናዖስ ንጉስ ኣሞናውያን ደዪቡ ነታ ኣብ ገለዓድ ዘላ ኸተማ ኢያቤስ ከበባ። ኵሎም ሰብ ኢያቤስ ከዓ ንናዖስ “ክንግዝአልካስ ኪዳን እተወልና” በልዎ። ትግርኛ GAZBIB Baras Nahaash mootiin Amoonotaa mandara Yaabesh-Giil'aaditti duulee, itti in marse; namoonni Yaabesh hundinuus Nahaashi… Afaan Oromoo BCV GIZ ወእምዝ እምድኅረ አሐዱ ወርኅ ዓርገ ናአስ ዐሞናዊ ወተዐየነ ኀበ ኢያቢስ ዘገለዓድ ወይቤልዎ ኵሉ ሰብአ ገለዓድ ለናአስ ዐሞናዊ፦ ተማሐል ምስሌነ ወንትቀነይ ለከ። giz GAZGAZ Baras Nahaash mootiin Amoonotaa mandara Yaabesh-Giil'aaditti duulee, itti in marse; namoonni Yaabesh hundinuus Nahaashi… Afaan Oromoo BCV aksum ከምዙይ ድማ ኾነ፦ ብድሕሪ ሓደ ወርሒ ናዖስ ንጉስ ኣሞናውያን ደዪቡ ነታ ኣብ ገለዓድ ዘላ ኸተማ ኢያቤስ ከበባ። ኵሎም ሰብ ኢያቤስ ከዓ ንናዖስ “ክንግዝአልካስ ኪዳን እተወልና” በልዎ። ትግርኛ SWAHSUV Ikawa, kama baada ya mwezi mmoja, Nahashi, Kiswahili