1ኛ ሳሙኤል 11

AMHEVGአማርኛ15 ጥቅሶች2:54 አዳምጥ
አዳምጥ 2:54 · መደበኛ · አስደናቂ በBiblight ይክፈቱ

1እንዲህም ሆነ፤ ከአንድ ወር በኋላ አሞናዊው ናዖስ ወጣ፥ በኢያቢስ ገለዓድም ሰፈረ፤ የኢያቢስም ሰዎች ሁሉ፦ ቃል ኪዳን አድርግልን፥ እኛም እንገዛልሃለን፡ አሉት።

2አሞናዊውም ናዖስ፦ ቀኝ ዓይናችሁን ሁሉ በማውጣት ቃል ኪዳን አደርግላችኋለሁ፤ በእስራኤልም ሁሉ ላይ ስድብ አደረጋለሁ፡ አላቸው።

3የኢያቢስም ሽማግሌዎች፦ ወደ እስራኤል አገር ሁሉ መልክተኞችን እንድንልክ ሰባት ቀን ቆይልን፤ ከዚያም በኋላ የሚያድነን ባይኖር ወደ አንተ እንመጣለን፡ አሉት።

4መልክተኞቹም ሳኦል ወዳለበት ወደ ጊብዓ መጥተው ይህን ነገር በሕዝቡ ጆሮ ተናገሩ፤ ሕዝቡም ሁሉ ድምፃቸውን ከፍ አድርገው አለቀሱ።

5እነሆም፥ ሳኦል በሬዎቹን ተከትሎ ከእርሻው መጣ፤ ሳኦልም፦ ሕዝቡ የሚያለቅስ ምን ሆኖ ነው? አለ። የኢያቢስንም ሰዎች ነገር ነገሩት።

6ይህንም ነገር በሰማው ጊዜ በሳኦል ላይ የእግዚአብሔር መንፈስ በኃይል ወረደ፥ ቍጣውም እጅግ ነደደ።

7ጥምዱንም በሬዎች ወስዶ ቈራረጣቸው፥ ወደ እስራኤልም ዳርቻ ሁሉ በመልክተኞቹ እጅ ሰደደና፦ ሳኦልንና ሳሙኤልን ተከትሎ የማይወጣ ሁሉ፥ በበሬዎቹ እንዲሁ ይደረግ፡ አለ። ድንጋጤም በሕዝቡ ላይ ከእግዚአብሔር ዘንድ ወደቀ፥ እንደ አንድ ሰውም ሆነው ወጡ።

8በቤዜቅም ቈጠራቸው፤ የእስራኤልም ልጆች ሦስት መቶ ሺህ፥ የይሁዳም ሰዎች ሠላሳ ሺህ ነበሩ።

9የመጡትንም መልክተኞች፦ የኢያቢስ ገለዓድን ሰዎች፦ ነገ ፀሐይ በተኮሰ ጊዜ ማዳን ይሆንላችኋል፡ በሉአቸው፡ አሉአቸው። መልክተኞችም መጥተው ለኢያቢስ ሰዎች ነገሩ፤ ደስም አላቸው።

10የአያቢስም ሰዎች፦ ነገ እንወጣላችኋለን፥ ደስ የሚያሰኛችሁንም አድርጉብን፡ አሉ።

11በነጋውም ሳኦል ሕዝቡን በሦስት ወገን አደረጋቸው፤ ወገግም ባለ ጊዜ ወደ ሰፈሩ መካከል ገቡ፥ ቀትርም እስኪሆን ድረስ አሞናውያንን መቱ፤ የቀሩትም ተበተኑ፥ ሁለትም በአንድ ላይ ሆነው አልቀሩላቸውም።

12ሕዝቡም ሳሙኤልን፦ ሳኦል አይንገሥብን ያሉ እነማናቸው? አውጡአቸውና እንግደላቸው፡ አሉት።

13ሳኦልም፦ ዛሬ እግዚአብሔር ለእስራኤል ማዳን አድርጎአልና ዛሬ አንድ ሰው አይሞትም፡ አለ።

14ሳሙኤልም ሕዝቡን፦ ኑ፥ ወደ ጌልገላ እንሂድ፥ በዚያም መንግሥቱን እናድስ፡ አላቸው።

15ሕዝቡም ሁሉ ወደ ጌልገላ ሄዱ፥ በዚያም ሳኦልን በእግዚአብሔር ፊት በጌልገላ አነገሡት፤ በዚያም በእግዚአብሔር ፊት የደኅንነት መሥዋዕት አቀረቡ፤ በዚያም ሳኦልና የእስራኤል ሰዎች ሁሉ ታላቅ ደስታ አደረጉ።

ማብራሪያ

11:1-11 የሳኦል አገዛዝ የመጀመሪያው ፍሬ ያቤስ-ገለዓድን ከአሞናውያን ማዳን ነበር። ሕይወታቸውን ለማዳን ሲሉ ሰዎች ነጻነታቸውን ይተዋሉ፥ ዓይናቸውም እንዲወጣ እስከመፈቀድ ይደርሳሉ፤ ታዲያ እንደ ቀኝ ዓይናችን ውድ የሆነብንን ኃጢአት ትተን ከገሃነም እሳት ከመጣል መዳን ጥበብ አይደለምን? የሳኦልን እምነትና መተማመን ተመልከቱ፥ በዚያም ላይ የተመሠረተውንም ጽናቱንና ቁርጠኝነቱን። በዚህም ጉዳይ ላይ ያለውን ትጋትም ተመልከቱ።

ሙሉ ማብራሪያውን ያንብቡ ድምፅ፣ ሙሉ ማብራሪያ እና ከመስመር ውጭ ንባብ

ትርጉሞች8 · 6

ENGNIV Nahash the Ammonite went up and besieged Jabesh Gilead. And all the men of Jabesh said to him, “Make a treaty with us, … English BCV ከምዙይ ድማ ኾነ፦ ብድሕሪ ሓደ ወርሒ ናዖስ ንጉስ ኣሞናውያን ደዪቡ ነታ ኣብ ገለዓድ ዘላ ኸተማ ኢያቤስ ከበባ። ኵሎም ሰብ ኢያቤስ ከዓ ንናዖስ “ክንግዝአልካስ ኪዳን እተወልና” በልዎ። ትግርኛ GAZBIB Baras Nahaash mootiin Amoonotaa mandara Yaabesh-Giil'aaditti duulee, itti in marse; namoonni Yaabesh hundinuus Nahaashi… Afaan Oromoo BCV GIZ ወእምዝ እምድኅረ አሐዱ ወርኅ ዓርገ ናአስ ዐሞናዊ ወተዐየነ ኀበ ኢያቢስ ዘገለዓድ ወይቤልዎ ኵሉ ሰብአ ገለዓድ ለናአስ ዐሞናዊ፦ ተማሐል ምስሌነ ወንትቀነይ ለከ። giz GAZGAZ Baras Nahaash mootiin Amoonotaa mandara Yaabesh-Giil'aaditti duulee, itti in marse; namoonni Yaabesh hundinuus Nahaashi… Afaan Oromoo BCV aksum ከምዙይ ድማ ኾነ፦ ብድሕሪ ሓደ ወርሒ ናዖስ ንጉስ ኣሞናውያን ደዪቡ ነታ ኣብ ገለዓድ ዘላ ኸተማ ኢያቤስ ከበባ። ኵሎም ሰብ ኢያቤስ ከዓ ንናዖስ “ክንግዝአልካስ ኪዳን እተወልና” በልዎ። ትግርኛ AMHNIV አሞናዊው ናዖስ ወጥቶ ኢያቢስ ገለዓድን ከበባት፤ የኢያቢስም ሰዎች ሁሉ፣ “ከእኛ ጋር ቃል ኪዳን አድርግ፣ እኛም እንገዛልሃለን” አሉት። አማርኛ SWAHSUV Ikawa, kama baada ya mwezi mmoja, Nahashi, Kiswahili