1ኛ ጴጥሮስ 4

AMHEVGአማርኛ18 ጥቅሶች2:55 አዳምጥ
አዳምጥ 2:55 · መደበኛ · አስደናቂ በBiblight ይክፈቱ

1ክርስቶስም በሥጋ ስለ እኛ መከራን ስለተቀበለ፥ ከእንግዲህ ወዲህ በሥጋ ልትኖሩ በቀረላችሁ ዘመን እንደ እግዚአብሔር ፈቃድ እንጂ እንደ ሰው ምኞት እንዳትኖሩ፥ እናንተ ደግሞ ያን አሳብ እንደ ዕቃ ጦር አድርጋችሁ ያዙት፥ በሥጋ መከራን የተቀበለ ኃጢአትን ትቶአልና።

3የአሕዛብን ፈቃድ ያደረጋችሁበት በመዳራትና በሥጋ ምኞትም በስካርም በዘፈንም ያለ ልክም በመጠጣት ነውርም ባለበት በጣዖት ማምለክ የተመላለሳችሁበት ያለፈው ዘመን ይበቃልና።

4በዚህም ነገር ወደዚያ መዳራት ብዛት ከእነርሱ ጋር ስለማትሮጡ እየተሳደቡ ይደነቃሉ፤

5ግን እነርሱ በሕያዋንና በሙታን ላይ ሊፈርድ ለተዘጋጀው መልስ ይሰጣሉ።

6እንደሰዎች በሥጋ እንዲፈረድባቸው በመንፈስ ግን እንደ እግዚአብሔር እንዲኖሩ ስለዚህ ምክንያት ወንጌል ለሙታን ደግሞ ተሰብኮላቸው ነበርና።

7ዳሩ ግን የነገር ሁሉ መጨረሻ ቀርቦአል። እንግዲህ እንደ ባለ አእምሮ አስቡ፥

8ትጸልዩም ዘንድ በመጠን ኑሩ፤ ፍቅር የኃጢአትን ብዛት ይሸፍናልና ከሁሉ በፊት እርስ በርሳችሁ አጥብቃችሁ ተዋደዱ።

9ያለ ማንጐራጐር እርስ በርሳችሁ እንግድነትን ተቀባበሉ፤

10ልዩ ልዩን የእግዚአብሔርን ጸጋ ደጋግ መጋቢዎች እንደ መሆናችሁ፥ እያንዳንዳችሁ የጸጋን ስጦታ እንደ ተቀበላችሁ መጠን በዚያው ጸጋ እርስ በርሳችሁ አገልግሉ፤

11ማንም ሰው የሚናገር ቢሆን፥ እንደ እግዚአብሔር ቃል ይናገር፤ የሚያገለግልም ቢሆን፥ እግዚአብሔር በሚሰጠኝ ኃይል ነው ብሎ ያገልግል፤ ክብርና ሥልጣን እስከ ዘላለም ድረስ ለእርሱ በሚሆነው በኢየሱስ ክርስቶስ በኩል እግዚአብሔር በነገር ሁሉ ይከብር ዘንድ፤ አሜን።

12ወዳጆች ሆይ፥ በእናንተ መካከል እንደ እሳት ሊፈትናችሁ ስለሚሆነው መከራ ድንቅ ነገር እንደ መጣባችሁ አትደነቁ፤

13ነገር ግን ክብሩ ሲገለጥ ደግሞ ሐሤት እያደረጋችሁ ደስ እንዲላችሁ፥ በክርስቶስ መከራ በምትካፈሉበት ልክ ደስ ይበላችሁ።

14ስለ ክርስቶስ ስም ብትነቀፉ የክብር መንፈስ የእግዚአብሔር መንፈስ በእናንተ ላይ ያርፋልና ብፁዓን ናችሁ።

15ከእናንተ ማንም ነፍሰ ገዳይ ወይም ሌባ ወይም ክፉ አድራጊ እንደሚሆን ወይም በሌሎች ጒዳይ እንደሚገባ ሆኖ መከራን አይቀበል፤

16ክርስቲያን እንደሚሆን ግን መከራን ቢቀበል ስለዚህ ስም እግዚአብሔርን ያመስግን እንጂ አይፈር።

17ፍርድ ከእግዚአብሔር ቤት ተነሥቶ የሚጀመርበት ጊዜ ደርሶአልና፤ አስቀድሞም በእኛ የሚጀመር ከሆነ ለእግዚአብሔር ወንጌል የማይታዘዙ መጨረሻቸው ምን ይሆን?

18ጻድቅም በጭንቅ የሚድን ከሆነ ዓመፀኛውና ኃጢአተኛው ወዴት ይታይ ዘንድ አለው?

19ስለዚህ ደግሞ እንደ እግዚአብሔር ፈቃድ መከራን የሚቀበሉ፥ መልካምን እያደረጉ ነፍሳቸውን ለታመነ ፈጣሪ አደራ ይስጡ።

ማብራሪያ

4:1-6 በኃጢአት ላይ ያሉ እጅግ ጠንካራና የላቁ መከራከሪያዎች የተወሰዱት ከክርስቶስ መከራ ነው። እርሱ ኃጢአትን ለማጥፋት ሞተ፤ እጅግ የከፋ መከራን በፈቃደኝነት ቢታገስም፣ በትንሹም ቢሆን ለኃጢአት ፈጽሞ አላስገዛም። የሰው የራሱ ብልሹነት ባይኖር ኖሮ ፈተናዎች ሊያሸንፉ አይችሉም ነበር፤ እውነተኛ ክርስቲያኖች ግን የራሳቸውን ምኞትና ፍላጎት ሳይሆን፣ የእግዚአብሔርን ፈቃድ የሕይወታቸውና የሥራቸው መመሪያ ያደርጋሉ። እውነተኛ ለውጥ በልብና በሕይወት ውስጥ ድንቅ ለውጥ ያመጣል። እርሱም አእምሮን፣ ፍርድን፣ ስሜቶችንና አኗኗርን ይለውጣል። አንድ ሰው እውነተኛ ለውጥ ሲያደርግ፣ የሕይወቱ ያለፈው ጊዜ እንዴት እንደጠፋ ሲያስብ ለእርሱ እጅግ ያሳዝነዋል። አንዲት ኃጢአት ሌላኛይቱን ትጎትታለች። እዚህ ላይ እርስ በእርስ ጥገኝነት ያላቸው ስድስት ኃጢአቶች ተጠቅሰዋል። የክርስቲያን ግዴታ ከከባድ ክፋት መራቅ ብቻ ሳይሆን፣ ወደ ኃጢአት ከሚመሩ ወይም ክፉ ከሚመስሉ ነገሮችም መራቅ ጭምር ነው። ወንጌል ለሞቱት ሰዎች ተሰብኮላቸው ነበር፤ እነዚህም በክፉ ሰዎች ትዕቢተኛና ሥጋዊ ፍርድ ምክንያት ክፉ አድራጊዎች ተብለው ተፈርደው ነበር፣ አንዳንዶቹም ሞትን እስከመቀበል ደርሰዋል። ነገር ግን በመንፈስ ቅዱስ ወደ መለኮታዊ ሕይወት ሕያው ስለተደረጉ፣ ለእግዚአብሔር እንደ እርሱ ያደሩ አገልጋዮች ሆነው ኖረዋል። ዓለም ቢሰድባቸውና ቢያንቋሽሻቸውም፣ ምእመናን አይጨነቁ።

፬፥፯-፲፩ በመድኃኒታችን አስቀድሞ የተነገረው የአይሁድ ቤተ ክርስቲያንና ሕዝብ መጥፋት እጅግ ቅርብ ነበር። የሞትና የፍርድ ፈጣን መቃረብም ሁሉንም ይመለከታል። እነዚህ ቃላት ደግሞ በተፈጥሮአቸው አእምሮአችንን ወደዚያ ይመራሉ። የመጨረሻችን መቃረብ በዓለማዊ ነገሮች ሁሉ ልባችንን ለመግዛትና በሃይማኖት ደግሞ ቀናኢዎች እንድንሆን ኃይለኛ መከራከሪያ ነው።

ሙሉ ማብራሪያውን ያንብቡ ድምፅ፣ ሙሉ ማብራሪያ እና ከመስመር ውጭ ንባብ

ትርጉሞች8 · 6

ENGNIV Therefore, since Christ suffered in his body, arm yourselves also with the same attitude, because he who has suffered i… English BCV እምበኣር ክርስቶስ ብስጋ ምእንታና መከራ ስለዝተቐበለ፥ ነቲ ብስጋ ኽትነብሩ ዝተረፈኩም ዘመን፥ ከም እግዚኣብሄር ፍቓድ እምበር፥ ከም ትምኒት ስጋኹም ምእንቲ ኸይትነብሩ፥ ንስኻትኩምውን ነዝ … ትግርኛ GAZBIB Kristos namummaa fooniitiin erga dhiphatee, isinis immoo akkuma isaa yaaduudhaan, akka nama lolaaf mi'a hidhatetti taa'… Afaan Oromoo BCV GIZ ወእመሰ ክርስቶስ ተሰቅለ በሥጋሁ በእንቲኣነ ወአንትሙኒ ተወልተዉ በይእቲ ኅሊና እስመ ዘሐመ በሥጋሁ ድኅነ እምኀጣውኡ። giz GAZGAZ Kristos namummaa fooniitiin erga dhiphatee, isinis immoo akkuma isaa yaaduudhaan, akka nama lolaaf mi'a hidhatetti taa'… Afaan Oromoo BCV aksum እምበኣር ክርስቶስ ብስጋ ምእንታና መከራ ስለዝተቐበለ፥ ነቲ ብስጋ ኽትነብሩ ዝተረፈኩም ዘመን፥ ከም እግዚኣብሄር ፍቓድ እምበር፥ ከም ትምኒት ስጋኹም ምእንቲ ኸይትነብሩ፥ ንስኻትኩምውን ነዝ … ትግርኛ AMHNIV እንግዲህ ክርስቶስ በሥጋው መከራን ስለ ተቀበለ እናንተም በዚሁ ዐላማ ታጥቃችሁ ተነሡ፤ ምክንያቱም በሥጋው መከራን የሚቀበል ሰው ኀጢአትን ትቶአል። አማርኛ SWAHSUV Basi kwa kuwa Kristo aliteswa katika mwili wake, ninyi nanyi jivikeni silaha ya nia ile ile; kwa maana yeye aliyeteswa … Kiswahili