1ኛ ቆሮንቶስ 8

AMHNIVአማርኛ13 ጥቅሶች2:25 አዳምጥ
አዳምጥ 2:25 · መደበኛ · አስደናቂ በBiblight ይክፈቱ

1ለጣዖት ስለ ተሠዋ ሥጋ ደግሞ ይህን እላለሁ፤ ሁላችንም ዕውቀት እንዳለን እናውቃለን። ዕውቀት ያስታብያል፤ ፍቅር ግን ያንጻል።

2ዐውቃለሁ የሚል ሰው፣ ማወቅ የሚገባውን ያህል ገና አላወቀም።

3እግዚአብሔርን የሚወድ ሰው ግን በእግዚአብሔር ዘንድ የታወቀ ነው።

4እንግዲህ፣ ለጣዖት የተሠዋ ሥጋ ስለ መብላት እንዲህ እላለሁ፤ በዚህ ዓለም ጣዖት ከንቱ እንደሆነና ከአንዱ ከእግዚአብሔር በስተቀር ሌላ አምላክ እንደሌለ እናውቃለን።

5መቼም ብዙ አማልክትና ብዙ ጌቶች አሉ፤ በሰማይም ሆነ በምድር አምላክ ተብለው የሚጠሩ አማልክት ቢኖሩም፤

6ለእኛ ግን ሁሉም ነገር ከእርሱ የሆነ፣ እኛም ለእርሱ የሆን አንድ አምላክ አብ አለን፤ ደግሞም ሁሉም ነገር በእርሱ አማካይነት የሆነ፣ እኛም በእርሱ አማካይነት የሆን አንድ ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ አለን።

7ነገር ግን ይህን የሚያውቁ ሁሉም አይደሉም፤ አንዳንድ ሰዎች እስከ አሁን ድረስ ጣዖትን ማምለክ ስለ ለመዱ፣ እንዲህ ያለውን ሥጋ ሲበሉ በርግጥ ለጣዖት እንደ ተሠዋ ያስባሉ፤ ኅሊናቸውም ደካማ ስለ ሆነ ይረክሳል።

8ነገር ግን ምግብ ወደ እግዚአብሔር አያቀርበንም፤ ባንበላ የሚጐድልብን ነገር የለም፤ ብንበላም የምናተርፈው ነገር አይኖርም።

9ነገር ግን ከነጻነታችሁ የተነሣ የምታደርጉት ለደካሞች ዕንቅፋት እንዳይሆን ተጠንቀቁ።

10አንተ ይህን የመሰለ ዕውቀት ኖሮህ፣ ደካማ ኅሊና ያለው ሰው በቤተ ጣዖት ስትበላ ቢያይህ፣ ለጣዖት የተሠዋውን ምግብ ለመብላት አይደፋፈርምን?

11ስለዚህ ክርስቶስ የሞተለት ይህ ደካማ ወንድም በአንተ ዕውቀት ምክንያት ጠፋ ማለት ነው።

12በዚህ መንገድ ወንድሞቻችሁን በመበደልና ደካማ ኅሊናቸውን በማቍሰል፣ ክርስቶስን ትበድላላችሁ።

13ስለዚህ እኔ የምበላው ነገር ወንድሜን የሚያሰናክለው ከሆነ፣ ወንድሜን ላለማሰናከል ስል ከቶ ሥጋ አልበላም።

ማብራሪያ

8:1-6 እውቀት አለኝ ብሎ ከመታበይ የበለጠ የድንቁርና መገለጫ የለም። ብዙ ነገር ቢታወቅም፣ ለበጎ ዓላማ ካልዋለ ከንቱ ነው። ማንኛውንም ነገር አውቃለሁ ብለው የሚያስቡና በዚህ የሚኩራሩ፣ እውቀታቸውን በአግባቡ ለመጠቀም እጅግ ያነሰ ዕድል ያላቸው ናቸው። ሰይጣን አንዳንዶችን በአእምሮ ችሎታቸው እንዲኮሩ በማድረግ ያጎዳቸዋል፤ ሌሎችን ደግሞ ወደ ስሜታዊነት በመሳብ እንዲሁ ያጎዳቸዋል። ባለቤቱን የሚያሳብጥና እሱኑ እንዲተማመን የሚያደርግ እውቀት፣ የሚያውቀው ነገር ትክክል ቢሆንም እንኳ፣ እንደ ራስ-ጽድቅ ኩራት አደገኛ ነው። ቅዱስ ፍቅር ከሌለ ሁሉም ሰብዓዊ እውቀት ከንቱ ነው።

አሕዛብ ከፍተኛና ዝቅተኛ ደረጃ ያላቸው አማልክት፣ ብዙ አማልክትና ብዙ ጌቶች ነበሯቸው፤ እንዲሁ የተጠሩ ናቸው እንጂ በእውነት እንዲህ ያሉ አይደሉም። ክርስቲያኖች ግን የተሻለ ያውቃሉ። አንድ አምላክ ሁሉን ፈጥሯል፣ በሁሉም ላይም ሥልጣን አለው።

አንድ አምላክ፣ እርሱም አብ፣ ለሁሉም ሃይማኖታዊ አምልኮ ብቸኛው የአምልኮ ዓላማ የሆነውን መለኮትን ያመለክታል።

ሙሉ ማብራሪያውን ያንብቡ ድምፅ፣ ሙሉ ማብራሪያ እና ከመስመር ውጭ ንባብ

ትርጉሞች8 · 6