1ኛ ቆሮንቶስ 9

AMHEVGአማርኛ26 ጥቅሶች3:45 አዳምጥ
አዳምጥ 3:45 · መደበኛ · አስደናቂ በBiblight ይክፈቱ

1እኔ ነጻ አይደለሁምን? ሐዋርያስ አይደለሁምን? ጌታችንን ኢየሱስ ክርስቶስንስ አላየሁትምን? እናንተስ በጌታ ሥራዬ አይደላችሁምን?

2የሐዋርያነቴ ማኅተም በጌታ እናንተ ናችሁና ለሌሎች ሐዋርያ ባልሆን ለእናንተስ ምንም ቢሆን ሐዋርያ ነኝ።

3ለሚመረምሩኝ መልሴ ይህ ነው። ልንበላና ልንጠጣ መብት የለንምን?

5እንደ ሌሎቹ ሐዋርያትና እንደ ጌታ ወንድሞች እንደ ኬፋም፥ እኅት ሚስታችንን ይዘን ልንዞር መብት የለንምን?

6ወይስ ሥራን ለመተው መብት የሌለን እኔና በርናባስ ብቻ ነን?

7ከቶ በገዛ ገንዘቡ በወታደርነት የሚያገለግል ማን ነው? ወይስ ወይን ተክሎ ፍሬውን የማይበላ ማን ነው? ወይስ መንጋ እየጠበቀ ከመንጋው ወተት የማይጠጣ ማን ነው?

8ይህን በሰው ሥልጣን ብቻ እላለሁን? ሕግስ ደግሞ ያን አይልምን፦

9“የሚያበራየውን በሬ አፉን አትሰር” ተብሎ በሙሴ ሕግ ተጽፎአልና። እግዚአብሔርስ ስለ በሬዎች ይገደዋልን?

10ይህን የሚለው ፈጽሞ ስለ እኛ አይደለምን? የሚያርስ በተስፋ ሊያርስ የሚያበራይም እንዲካፈል በተስፋ ሊያበራይ ስለሚገባው በእውነት ስለ እኛ ተጽፎአል።

11እኛ መንፈሳዊን ነገር የዘራንላችሁ ከሆንን የእናንተን የሥጋዊን ነገር እኛ ብናጭድ ትልቅ ነገር ነውን?

12ሌሎች በእናንተ ላይ ይህን መብት የሚካፈሉ ከሆኑ እኛማ ይልቁን እንዴታ? ነገር ግን የክርስቶስን ወንጌል እንዳንከለክል በሁሉ እንታገሣለን እንጂ በዚህ መብት አልተጠቀምንም።

13በመቅደስ ነገር የሚያገለግሉ ከመቅደስ የሆነውን ነገርን እንዲመገቡ፥ በመሠዊያውም የሚጸኑ ከመሠዊያው እንዲካፈሉ አታውቁምን?

14እንዲሁ ደግሞ ወንጌልን የሚሰብኩ ከወንጌል ቀለብ እንዲቀበሉ ጌታ ደንግጎአል።

15እኔ ግን ከእነዚህ ሁሉ ምንም አልተጠቀምሁም። እንዲህ እንዲሆንልኝ ይህን አልጽፍም፤ ማንም ትምክህቴን ከንቱ ከሚያደርግብኝ ሞት ይሻለኛልና።

16ወንጌልን ብሰብክ እንኳ የምመካበት የለኝም፤ ግድ ደርሶብኝ ነውና፤ ወንጌልንም ባልሰብክ ወዮልኝ።

17ይህን በፈቃዴ ባደርገው ደመወዝ አለኝና፤ ያለ ፈቃዴ ግን ባደርገው መጋቢነት በአደራ ተሰጥቶኛል።

18እንግዲህ ደመወዜ ምንድር ነው? ወንጌልን እየሰበክሁ በወንጌል ካለኝ መብት በሙሉ እንዳልጠቀም ወንጌልን ያለ ዋጋ ብናገር ነው።

19ከሰው ሁሉ አርነት የወጣሁ ስሆን የሚበልጡትን እንድጠቅም እንደ ባሪያ ራሴን ለሁሉ አስገዛለሁ።

20አይሁድንም እጠቅም ዘንድ ከአይሁድ ጋር እንደ አይሁዳዊ ሆንሁ፤ ከሕግ በታች ያሉትን እጠቅም ዘንድ፥ እኔ ራሴ ከሕግ በታች ሳልሆን፥ ከሕግ በታች ላሉት ከሕግ በታች እንዳለሁ ሆንሁ፤

21ሕግ የሌላቸውን እጠቅም ዘንድ፥ ያለ እግዚአብሔር ህግ ሳልኖር ነገር ግን በክርስቶስ ሕግ በታች ሳለሁ፥ ሕግ ለሌላቸው ሕግ እንደ ሌለኝ ሆንሁ፤

22ደካሞችን እጠቅም ዘንድ ለደካሞች እንደ ደካማ ሆንሁ፤ በሁሉ መንገድ አንዳንዶችን አድን ዘንድ፥ ከሁሉ ጋር በሁሉ ነገር እንደ እነርሱ ሆንሁ።

23በወንጌልም ማኅበረተኛ እሆን ዘንድ ስለ ወንጌል ሁሉን አደርጋለሁ።

24በእሽቅድምድም ስፍራ የሚሮጡት፥ ሁሉ እንዲሮጡ ነገር ግን አንዱ ብቻ ዋጋውን እንዲቀበል አታውቁምን? እንዲሁም ታገኙ ዘንድ ሩጡ።

25የሚታገልም ሁሉ በነገር ሁሉ ሰውነቱን ይገዛል፤ እነዚያም የሚጠፋውን አክሊል ሊያገኙ ነው፥ እኛ ግን የማይጠፋውን።

26ስለዚህ እኔ ያለ አሳብ እንደሚሮጥ ሁሉ እንዲሁ አልሮጥም፥ ነፋስን እንደሚጎስም ሁሉ እንዲሁ አልጋደልም፤

27ነገር ግን ለሌሎች ከሰበክሁ በኋላ ራሴ የተጣልሁ እንዳልሆን ሥጋዬን እየጎሰምሁ አስገዛዋለሁ።

ማብራሪያ

9:1-14 ለአገልጋይ ለአንድ ሕዝብ ከሚያሳየው መልካም ፈቃድ፣ እና በመካከላቸው ለሚያከናውነው ትጉህና ስኬታማ አገልግሎት መልካም ያልሆነ ምላሽ ማግኘት አዲስ ነገር አይደለም። የአንዳንዶችን ትችት ለመመለስ፣ ሐዋርያው ራሱን ለሌሎች መልካም ሲል እንደ ራስን የመካድ ምሳሌ አድርጎ በሚያሳይ መንገድ መልስ ይሰጣል። ልክ እንደ ሌሎች ሐዋርያት የማግባት፣ እንዲሁም በእጆቹ ሳይሠራ ለሚስቱ፣ እና ካሉትም ለልጆቹ የሚያስፈልገውን ከቤተክርስቲያናት ለመጠየቅ መብት ነበረው። ነፍሳችንን መልካም ለማድረግ የሚፈልጉ ምግብ ሊቀርብላቸው ይገባል። ነገር ግን መብቱን በመጠየቅ ስኬቱን ከማደናቀፍ ይልቅ መብቱን ተወ። አገልጋያቸውን መደገፍ የሕዝቡ ግዴታ ነው። እርሱ (አገልጋዩ) እንደ ጳውሎስ መብቱን ሊተው ይችላል፤ ነገር ግን ተገቢውን ድጋፍ የሚከለክሉ ወይም የሚነፍጉ የክርስቶስን ትእዛዝ ይጥሳሉ።

9:15-23 የአገልጋይ ክብር የሚሆነው ራሱን መካዱ፣ ክርስቶስን ለማገልገል እና ነፍሳትን ለማዳን ነው። አንድ አገልጋይ ግን የወንጌልን ሲል መብቱን ሲተው፣ ከኃላፊነቱና ከሥራው ከሚጠበቀው በላይ ያደርጋል።

ሙሉ ማብራሪያውን ያንብቡ ድምፅ፣ ሙሉ ማብራሪያ እና ከመስመር ውጭ ንባብ

ትርጉሞች8 · 6

ENGNIV Am I not free? Am I not an apostle? Have I not seen Jesus our Lord? Are you not the result of my work in the Lord? English BCV ሓራዶ ኣይኮንኩን እየ? ሃዋርያዶ ኣይኮንኩን እየ? ንጐይታና ኢየሱስ ክርስቶስከ ኣይረአኽዎን ድየ? ንስኻትኩምከ፥ ብጐይታ ፍረ ስራሐይዶ ኣይኮንኩምን? ትግርኛ GAZBIB Ani birmaduu mitii ree? Ani ergamaa mitii ree? Ani gooftaa keenya Yesusin hin arginee ree? Isin bu'aa hojii ani gooftaa… Afaan Oromoo BCV GIZ ኢኮንኩኑ አግዓዜ ወኢኮንኩኑ ሐዋርያ? አኮኑ እግዚእነ ኢየሱስ ክርስቶስ ዘርኢኩ ወኢኮንክሙኑ አንትሙ ግብርየ በእግዚእነ? giz GAZGAZ Ani birmaduu mitii ree? Ani ergamaa mitii ree? Ani gooftaa keenya Yesusin hin arginee ree? Isin bu'aa hojii ani gooftaa… Afaan Oromoo BCV aksum ሓራዶ ኣይኮንኩን እየ? ሃዋርያዶ ኣይኮንኩን እየ? ንጐይታና ኢየሱስ ክርስቶስከ ኣይረአኽዎን ድየ? ንስኻትኩምከ፥ ብጐይታ ፍረ ስራሐይዶ ኣይኮንኩምን? ትግርኛ AMHNIV እኔ ነጻ ሰው አይደለሁምን? ሐዋርያስ አይደለሁምን? ጌታችንን ኢየሱስን አላየሁትምን? እናንተስ በጌታ የድካሜ ፍሬዎች አይደላችሁምን? አማርኛ SWAHSUV Je! Mimi si huru? Mimi si mtume? Mimi sikumwona Yesu Bwana wetu? Ninyi si kazi yangu katika Bwana? Kiswahili