1ኛ ቆሮንቶስ 8

AMHEVGአማርኛ13 ጥቅሶች1:52 አዳምጥ
አዳምጥ 1:52 · መደበኛ · አስደናቂ በBiblight ይክፈቱ

1ለጣዖት ስለ ተሠዋ ሥጋም፥ ሁላችን እውቀት እንዳለን እናውቃለን። እውቀት ያስታብያል ፍቅር ግን ያንጻል።

2ማንም አንዳች የሚያውቅ ቢመስለው ሊያውቅ እንደሚገባው ገና አላወቀም፤

3ማንም ግን እግዚአብሔርን ቢወድ እርሱ በእርሱ ዘንድ የታወቀ ነው።

4እንግዲህ ለጣዖት የተሠዋውን ሥጋ ስለ መብላት፥ ጣዖት ሁሉ በዓለም ከንቱ እንደ ሆነ ከአንዱም በቀር ማንም አምላክ እንደሌለ እናውቃለን።

5መቼም ብዙ አማልክትና ብዙ ጌቶች አሉ፤ ነገር ግን በሰማይ ሆነ በምድርም ሆነ አማልክት የተባሉ ምንም ቢኖሩ፥

6ለእኛስ ነገር ሁሉ ከእርሱ የሆነ እኛም ለእርሱ የሆንን አንድ አምላክ አብ አለን፥ ነገር ሁሉም በእርሱ በኩል የሆነ እኛም በእርሱ በኩል የሆንን አንድ ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ አለን።

7ነገር ግን ይህ እውቀት በሁሉ ዘንድ አይገኝም፤ አንዳንዶች ግን ጣዖትን እስከ አሁን ድረስ ስለ ለመዱ፦ “ለጣዖት የተሠዋ ነው” ብለው ይበላሉና ሕሊናቸው ደካማ ስለ ሆነ ይረክሳል።

8መብል ግን ወደ እግዚአብሔር አያቀርበንም፤ ባንበላም ምንም አይጎድለንም ብንበላም ምንም አይተርፈንም።

9ዳሩ ግን ይህ መብታችሁ ለደካሞች ዕንቅፋት እንዳይሆንባቸው ተጠንቀቁ።

10አንተ እውቀት ያለህ በጣዖት ቤት በማዕድ ስትቀመጥ አንድ ሰው ቢያይህ፥ ደካማ ሰው ቢሆን ለጣዖት የተሠዋውን ለመብላት ሕሊናው አይታነጽበትምን?

11በአንተ እውቀትም ይህ ደካማ ይጠፋል፥ እርሱም ክርስቶስ የሞተለት ወንድም ነው።

12እንዲህም ወንድሞችን እየበደላችሁ ደካማም የሆነውን ሕሊናቸውን እያቆሰላችሁ ክርስቶስን ትበድላላችሁ።

13ስለዚህም መብል ወንድሜን የሚያሰናክለው ከሆነ፥ ወንድሜን እንዳላሰናክለው ለዘላለም ከቶ ሥጋ አልበላም።

ማብራሪያ

8:1-6 እውቀት አለኝ ብሎ ከመታበይ የበለጠ የድንቁርና መገለጫ የለም። ብዙ ነገር ቢታወቅም፣ ለበጎ ዓላማ ካልዋለ ከንቱ ነው። ማንኛውንም ነገር አውቃለሁ ብለው የሚያስቡና በዚህ የሚኩራሩ፣ እውቀታቸውን በአግባቡ ለመጠቀም እጅግ ያነሰ ዕድል ያላቸው ናቸው። ሰይጣን አንዳንዶችን በአእምሮ ችሎታቸው እንዲኮሩ በማድረግ ያጎዳቸዋል፤ ሌሎችን ደግሞ ወደ ስሜታዊነት በመሳብ እንዲሁ ያጎዳቸዋል። ባለቤቱን የሚያሳብጥና እሱኑ እንዲተማመን የሚያደርግ እውቀት፣ የሚያውቀው ነገር ትክክል ቢሆንም እንኳ፣ እንደ ራስ-ጽድቅ ኩራት አደገኛ ነው። ቅዱስ ፍቅር ከሌለ ሁሉም ሰብዓዊ እውቀት ከንቱ ነው።

አሕዛብ ከፍተኛና ዝቅተኛ ደረጃ ያላቸው አማልክት፣ ብዙ አማልክትና ብዙ ጌቶች ነበሯቸው፤ እንዲሁ የተጠሩ ናቸው እንጂ በእውነት እንዲህ ያሉ አይደሉም። ክርስቲያኖች ግን የተሻለ ያውቃሉ። አንድ አምላክ ሁሉን ፈጥሯል፣ በሁሉም ላይም ሥልጣን አለው።

አንድ አምላክ፣ እርሱም አብ፣ ለሁሉም ሃይማኖታዊ አምልኮ ብቸኛው የአምልኮ ዓላማ የሆነውን መለኮትን ያመለክታል።

ሙሉ ማብራሪያውን ያንብቡ ድምፅ፣ ሙሉ ማብራሪያ እና ከመስመር ውጭ ንባብ

ትርጉሞች8 · 6