ታርታን ከፍተኛ የአሦር ወታደራዊ አዛዥ ማዕረግ ሆኖ በ2ኛ ነገ 18:17እና በኢሳ 20:1ተጠቅሷል። በ2 ነገሥት ላይ፣ ታርታን ከረብሰሪስና ከረብሻቄ ጋር በመሆን ንጉሥ ሕዝቅያስን ለማስፈራራትና እጁን እንዲሰጥ ለመጠየቅ በአሦሩ ንጉሥ በሰናክሬም ወደ ኢየሩሳሌም ተልኮ ነበር። በኢሳይያስ ላይ ደግሞ ታርታን የአሦሩ ንጉሥ በሆነው በሳርጎን የአሽዶድን ከተማ እንዲያጠቃ ተልኮ ነበር። ታርታን ለንጉሡ ሁለተኛ አዛዥ የነበረና ዋና ዋና ወታደራዊ ዘመቻዎችን የመራ ሊሆን ይችላል። ይህ ማዕረግ የአካድ ምንጭ ያለው ሲሆን የአሦር ሠራዊት ዋና አዛዥን ያመለክታል።
ታርታን
አማርኛየመሪ ማዕረግ ሲሆን፣ ለመጀመሪያ ጊዜ የተጠቀሰው በ2 ነገሥት 18.17 ነው።