ትንቢተ ሶፎንያስ 1

AMHNIVአማርኛ18 ጥቅሶች3:45 አዳምጥ
አዳምጥ 3:45 · መደበኛ · አስደናቂ በBiblight ይክፈቱ

1በይሁዳ ንጉሥ በአሞጽ ልጅ በኢዮስያስ ዘመን ወደ ሕዝቅያስ ልጅ፣ ወደ አማርያ ልጅ፣ ወደ ጎዶልያስ ልጅ፣ ወደ ኵሲ ልጅ ወደ ሶፎንያስ የመጣ የእግዚአብሔር ቃል ይህ ነው፤

2“ማንኛውንም ነገር፣ ከምድር ገጽ አጠፋለሁ” ይላል እግዚአብሔር።

3“ሰውንና እንስሳን አጠፋለሁ፤ የሰማይን ወፎች፣ የባሕርንም ዓሦች አጠፋለሁ፤ ሰውን ከምድር ገጽ በማስወግድበት ጊዜ፣ ክፉዎች የፍርስራሽ ክምር ይሆናሉ” ይላል እግዚአብሔር።

4“እጄን በይሁዳ፣ በኢየሩሳሌምም በሚኖሩት ሁሉ ላይ አነሣለሁ፤ የበኣልን ትሩፍ፣ የጣዖታቱንና የአመንዝራ ካህናቱን ስም ሁሉ ከዚህ ስፍራ አጠፋለሁ፤

5የሰማይን ሰራዊት ለማምለክ፣ በሰገነት ላይ ወጥተው የሚሰግዱትን፣ ለእግዚአብሔር እየሰገዱ፣ በስሙም እየማሉ፣ በሚልኮምም ደግሞ የሚምሉትን፣

6እግዚአብሔርን ከመከተል ወደ ኋላ የሚመለሱትን፣ እግዚአብሔርን የማይፈልጉትን፣ እንዲረዳቸውም የማይጠይቁትን አጠፋለሁ።

7በልዑል እግዚአብሔር ፊት ዝም በሉ፤ የእግዚአብሔር ቀን ቀርቦአልና። እግዚአብሔር መሥዋዕት አዘጋጅቶአል፤ የጠራቸውንም ቀድሶአል።

8በእግዚአብሔር የመሥዋዕት ቀን፣ መሳፍንቱንና የንጉሡን ልጆች፣ እንግዳ ልብስ የሚለብሱትን ሁሉ እቀጣለሁ።

9በዚያን ቀን፣ በመድረኩ ላይ የሚዘሉትን ሁሉ፣ የአማልክቶቻቸውን ቤት፣ በዐመፅና በማጭበርበር የሚሞሉትን እቀጣለሁ።

10እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ “በዚያ ቀን ‘ከዓሣ በር’ ጩኸት በሁለተኛው አደባባይ ዋይታ፣ ከኰረብቶችም ታላቅ ሽብር ይሰማል።

11እናንት በመክቴሽ ገበያ የምትኖሩ ዋይ በሉ፤ ነጋዴዎቻችሁ ሁሉ ይደመሰሳሉ፤ በብር የሚነግዱትም ሁሉ ይሞታሉ።

12በዚያ ዘመን ኢየሩሳሌምን በመብራት እፈትሻለሁ፤ ተንደላቀው የሚኖሩትን፣ በዝቃጩ ላይ እንደ ቀረ የወይን ጠጅ የሆኑትን፣ ‘ክፉም ይሁን መልካም፣ እግዚአብሔር ምንም አያደርግም’ የሚሉትን ቸልተኞች እቀጣለሁ።

13ሀብታቸው ይዘረፋል፤ ቤታቸው ይፈራርሳል፤ ቤቶች ይሠራሉ፤ ነገር ግን አይኖሩባቸውም፤ ወይን ይተክላሉ፤ ጠጁን ግን አይጠጡም።

14“ታላቁ የእግዚአብሔር ቀን ቅርብ ነው፤ ቅርብ ነው ፈጥኖም ይመጣል፤ በእግዚአብሔር ቀን የሚሰማው ልቅሶ መራራ ነው፤ በዚያ ጦረኛውም ምርር ብሎ ይጮኻል፤

15ያ ቀን የመዓት ቀን፣ የመከራና የጭንቀት ቀን፣ የሁከትና የጥፋት ቀን፣ የጨለማና የጭጋግ ቀን፣ የደመናና የድቅድቅ ጨለማ ቀን ይሆናል፤

16ያ ቀን በተመሸጉ ከተሞችና፣ በረጃጅም ግንቦች ላይ፣ የመለከት ድምፅና የጦርነት ጩኸት የሚሰማበት ቀን ይሆናል።

17እንደ ዕውር እንዲራመዱ፣ በሰዎች ላይ ጭንቀት አመጣባቸዋለሁ፤ በእግዚአብሔር ላይ ኀጢአትን ሠርተዋልና። ደማቸው እንደ ትቢያ፣ ሥጋቸውም እንደ ጒድፍ ይጣላል።

18በእግዚአብሔር የቊጣ ቀን፣ ብራቸውም ሆነ ወርቃቸው፣ ሊያድናቸው አይችልም፤ መላዪቱ ምድር፣ በቅናቱ ትበላለች፤ በምድር በሚኖሩ ሁሉ ላይ፣ ድንገተኛ ፍጻሜ ያመጣባቸዋልና።”

ማብራሪያ

1:1-6 ውድመት እየመጣ ነው፣ ሙሉ ውድመት፤ ከሁሉን ቻይ ከእግዚአብሔር የሚመጣ ጥፋት። የእግዚአብሔር አገልጋዮች ሁሉም፦ ለክፉዎች ሰላም የለም! ብለው ያውጃሉ። እነዚህ አገላለጾች ምሳሌያዊ ናቸው፤ በየቦታው ውድመትን ያመለክታሉ፤ ምድሪቱም ያለ ነዋሪ ትቀራለች። የሚጠፉት ኃጢአተኞች በግልጽ ጣዖት አምላኪዎች የሆኑት፣ ይሖዋንና ጣዖታትን የሚያመልኩት፣ ወይም በእግዚአብሔርና በሞልኮም የሚምሉ ናቸው። ፍቅራቸውንና አምልኳቸውን በእግዚአብሔርና በጣዖታት መካከል ለመከፋፈል የሚያስቡ ሰዎች በእግዚአብሔር ዘንድ ተቀባይነትን ያጣሉ። በብርሃንና በጨለማ መካከል ምንስ ህብረት ሊኖር ይችላልና? ሰይጣን ግማሹን ካገኘ፣ ሁሉንም ይወስዳል፤ ጌታ ግማሹን ብቻ ካገኘ ግን፣ ምንም አይኖረውም። እግዚአብሔርን ችላ ማለት እግዚአብሔርን አለማክበርንና ንቀትን ያሳያል። ማንም ከመጥፋት ወደ ኋላ ከሚመለሱት መካከል እንዳንሆን፣ ነገር ግን ነፍስን ለማዳን ከሚያምኑት መካከል እንሁን።

ሙሉ ማብራሪያውን ያንብቡ ድምፅ፣ ሙሉ ማብራሪያ እና ከመስመር ውጭ ንባብ

ትርጉሞች8 · 6

AMHEVG በይሁዳ ንጉሥ በአሞጽ ልጅ በኢዮስያስ ዘመን ወደ ሕዝቅያስ ልጅ ወደ አማርያ ልጅ ወደ ጎዶልያስ ልጅ ወደ ኵሲ ልጅ ወደ ሶፎንያስ የመጣ የእግዚአብሔር ቃል ይህ ነው። አማርኛ ENGNIV The word of the Lord that came to Zephaniah son of Cushi, the son of Gedaliah, the son of Amariah, the son of Hezekiah,… English BCV እቲ ብዘመን ኢዮስያስ ወዲ ኣሞፅ ንጉስ ይሁዳ፥ ናብ ሶፎንያስ ወዲ ኩሺ፥ ወዲ ጎዶልያስ፥ ወዲ ኣማርያ፥ ወዲ ንጉስ ሕዝቅያስ፥ ዝመፀ ቓል እግዚኣብሄር እዙይ እዩ፦ ትግርኛ GAZBIB Kun dubbii Waaqayyoo isa bara Yosiyaas ilmi Amoon mootii Yihudaa ture gara Sefaaniyaa ilma Kuushii, ilma Gedaaliiyaa, i… Afaan Oromoo BCV GIZ ቃለ እግዚአብሔር ዘኮነ ኀበ ሶፎንያስ ወልደ ኵስ ወልደ ጎዶልያ አሞራዊ ዘስየዴቅያ በመዋዕለ ዮስያ ወልደ አሞጽ ንጉሠ ይሁዳ። giz GAZGAZ Kun dubbii Waaqayyoo isa bara Yosiyaas ilmi Amoon mootii Yihudaa ture gara Sefaaniyaa ilma Kuushii, ilma Gedaaliiyaa, i… Afaan Oromoo BCV aksum እቲ ብዘመን ኢዮስያስ ወዲ ኣሞፅ ንጉስ ይሁዳ፥ ናብ ሶፎንያስ ወዲ ኩሺ፥ ወዲ ጎዶልያስ፥ ወዲ ኣማርያ፥ ወዲ ንጉስ ሕዝቅያስ፥ ዝመፀ ቓል እግዚኣብሄር እዙይ እዩ፦ ትግርኛ SWAHSUV Neno la Bwana lililomjia Sefania, mwana wa Kushi, mwana wa Gedalia, mwana wa Amaria, mwana wa Hezekia; katika siku za Y… Kiswahili