ትንቢተ ሶፎንያስ 1

AMHEVGአማርኛ18 ጥቅሶች3:13 አዳምጥ
አዳምጥ 3:13 · መደበኛ · አስደናቂ በBiblight ይክፈቱ

1በይሁዳ ንጉሥ በአሞጽ ልጅ በኢዮስያስ ዘመን ወደ ሕዝቅያስ ልጅ ወደ አማርያ ልጅ ወደ ጎዶልያስ ልጅ ወደ ኵሲ ልጅ ወደ ሶፎንያስ የመጣ የእግዚአብሔር ቃል ይህ ነው።

2“ነገርን ሁሉ ከምድር ፊት ፈጽሜ አጠፋለሁ፥ ይላል እግዚአብሔር።

3ሰውንና እንስሳን አጠፋለሁ፤ የሰማይን ወፎችና የባሕርን ዓሣዎች ማሰናከያንም ከኃጢአተኞች ጋር አጠፋለሁ፤ ሰውንም ከምድር ፊት እቈርጣለሁ፥ ይላል እግዚአብሔር።

4“እጄንም በይሁዳ ላይ በኢየሩሳሌምም በሚኖሩት ሁሉ ላይ እዘረጋለሁ፤ ከዚህም ስፍራ የበኣልን ቅሬታና የጣዖታቱን ካህናት ስም አጠፋለሁ፤

5በሰገነትም ላይ ለሰማይ ሠራዊት የሚሰግዱትን፥ በእግዚአብሔርና በንጉሣቸው በሚልኮም ምለው የሚሰግዱትን፥

6እግዚአብሔርንም ከመከተል የተመለሱትን፥ እግዚአብሔርንም ያልፈለጉትንና ያልጠየቁትን አጠፋለሁ።

7የእግዚአብሔር ቀን ቀርቦአልና፥ እግዚአብሔር መሥዋዕትን አዘጋጅቶአልና፥ የጠራቸውንም ቀድሶአልና በጌታ በእግዚአብሔር ፊት ዝም በሉ።

8በእግዚአብሔርም መሥዋዕት ቀን አለቆችንና የንጉሥን ልጆች እንግዳ ልብስ የሚለብሱትንም ሁሉ እቀጣለሁ።

9በዚያም ቀን በመድረኩ ላይ የሚዘልሉትን፥ የጌታቸውን ቤት ዓመፃንና ሽንገላን የሚሞሉትን እቀጣለሁ።

10“በዚያ ቀን፥ ይላል እግዚአብሔር፥ ከዓሣው በር የጩኸት ድምፅ፥ ከከተማውም በሁለተኛው ክፍል ውካታ፥ ከኮረብቶቹም ታላቅ ሽብር ይሆናል።

11እናንተ በመክቴሽ የምትኖሩ ሆይ፥ የከነዓን ሕዝብ ሁሉ ጠፍተዋልና፥ ብርም የተሸከሙ ሁሉ ተቈርጠዋልና አልቅሱ።

12በዚያም ዘመን ኢየሩሳሌምን በመብራት እመረምራለሁ፤ በአተላቸውም ላይ የሚቀመጡትን፥ በልባቸውም፦ “እግዚአብሔር መልካምን አያደርግም፥ ክፉም አያደርግም፡” የሚሉትን ሰዎች እቀጣለሁ።

13ብልጥግናቸውም ለምርኮ ይሆናል፥ ቤቶቻቸውም ይፈርሳሉ፤ ቤቶችንም ይሠራሉ፥ ነገር ግን አይቀመጡባቸውም፤ ወይንንም ይተክላሉ፥ የወይን ጠጁን ግን አይጠጡም።

14“ታላቁ የእግዚአብሔር ቀን ቀርቦአል፤ የእግዚአብሔር ቀን ድምፅ ቀርቦአል እጅግም ፈጥኖአል፤ ኃያሉም በዚያ በመራራ ልቅሶ ይጮኻል።

15ያ ቀን የመዓት ቀን የመከራና የጭንቀት ቀን፥ የመፍረስና የመጥፋት ቀን፥ የጨለማና የጭጋግ ቀን፥ የደመናና የድቅድቅ ጨለማ ቀን፥

16በተመሸጉ ከተሞችና በረዘሙ ግንቦች ላይ የመለከትና የሰልፍ ጩኸት ቀን ነው።

17በእግዚአብሔርም ላይ ኃጢአት ሠርተዋልና እንደ ዕውር እስኪሄዱ ድረስ ሰዎችን አስጨንቃለሁ፤ ደማቸውም እንደ ትቢያ፥ ሥጋቸውም እንደ ጕድፍ ይፈስሳል።

18በእግዚአብሔርም ቍጣ ቀን ብራቸውና ወርቃቸው ሊያድናቸው አይችልም፤ እርሱም በምድር የሚኖሩትን ሁሉ ፈጥኖ ይጨርሳቸዋልና ምድር ሁሉ በቅንዓቱ እሳት ትበላለች።”

ማብራሪያ

1:1-6 ውድመት እየመጣ ነው፣ ሙሉ ውድመት፤ ከሁሉን ቻይ ከእግዚአብሔር የሚመጣ ጥፋት። የእግዚአብሔር አገልጋዮች ሁሉም፦ ለክፉዎች ሰላም የለም! ብለው ያውጃሉ። እነዚህ አገላለጾች ምሳሌያዊ ናቸው፤ በየቦታው ውድመትን ያመለክታሉ፤ ምድሪቱም ያለ ነዋሪ ትቀራለች። የሚጠፉት ኃጢአተኞች በግልጽ ጣዖት አምላኪዎች የሆኑት፣ ይሖዋንና ጣዖታትን የሚያመልኩት፣ ወይም በእግዚአብሔርና በሞልኮም የሚምሉ ናቸው። ፍቅራቸውንና አምልኳቸውን በእግዚአብሔርና በጣዖታት መካከል ለመከፋፈል የሚያስቡ ሰዎች በእግዚአብሔር ዘንድ ተቀባይነትን ያጣሉ። በብርሃንና በጨለማ መካከል ምንስ ህብረት ሊኖር ይችላልና? ሰይጣን ግማሹን ካገኘ፣ ሁሉንም ይወስዳል፤ ጌታ ግማሹን ብቻ ካገኘ ግን፣ ምንም አይኖረውም። እግዚአብሔርን ችላ ማለት እግዚአብሔርን አለማክበርንና ንቀትን ያሳያል። ማንም ከመጥፋት ወደ ኋላ ከሚመለሱት መካከል እንዳንሆን፣ ነገር ግን ነፍስን ለማዳን ከሚያምኑት መካከል እንሁን።

ሙሉ ማብራሪያውን ያንብቡ ድምፅ፣ ሙሉ ማብራሪያ እና ከመስመር ውጭ ንባብ

ትርጉሞች8 · 6

ENGNIV The word of the Lord that came to Zephaniah son of Cushi, the son of Gedaliah, the son of Amariah, the son of Hezekiah,… English BCV እቲ ብዘመን ኢዮስያስ ወዲ ኣሞፅ ንጉስ ይሁዳ፥ ናብ ሶፎንያስ ወዲ ኩሺ፥ ወዲ ጎዶልያስ፥ ወዲ ኣማርያ፥ ወዲ ንጉስ ሕዝቅያስ፥ ዝመፀ ቓል እግዚኣብሄር እዙይ እዩ፦ ትግርኛ GAZBIB Kun dubbii Waaqayyoo isa bara Yosiyaas ilmi Amoon mootii Yihudaa ture gara Sefaaniyaa ilma Kuushii, ilma Gedaaliiyaa, i… Afaan Oromoo BCV GIZ ቃለ እግዚአብሔር ዘኮነ ኀበ ሶፎንያስ ወልደ ኵስ ወልደ ጎዶልያ አሞራዊ ዘስየዴቅያ በመዋዕለ ዮስያ ወልደ አሞጽ ንጉሠ ይሁዳ። giz GAZGAZ Kun dubbii Waaqayyoo isa bara Yosiyaas ilmi Amoon mootii Yihudaa ture gara Sefaaniyaa ilma Kuushii, ilma Gedaaliiyaa, i… Afaan Oromoo BCV aksum እቲ ብዘመን ኢዮስያስ ወዲ ኣሞፅ ንጉስ ይሁዳ፥ ናብ ሶፎንያስ ወዲ ኩሺ፥ ወዲ ጎዶልያስ፥ ወዲ ኣማርያ፥ ወዲ ንጉስ ሕዝቅያስ፥ ዝመፀ ቓል እግዚኣብሄር እዙይ እዩ፦ ትግርኛ AMHNIV በይሁዳ ንጉሥ በአሞጽ ልጅ በኢዮስያስ ዘመን ወደ ሕዝቅያስ ልጅ፣ ወደ አማርያ ልጅ፣ ወደ ጎዶልያስ ልጅ፣ ወደ ኵሲ ልጅ ወደ ሶፎንያስ የመጣ የእግዚአብሔር ቃል ይህ ነው፤ አማርኛ SWAHSUV Neno la Bwana lililomjia Sefania, mwana wa Kushi, mwana wa Gedalia, mwana wa Amaria, mwana wa Hezekia; katika siku za Y… Kiswahili