ትንቢተ ዘካርያስ 7

AMHEVGአማርኛ14 ጥቅሶች2:35 አዳምጥ
አዳምጥ 2:35 · መደበኛ · አስደናቂ በBiblight ይክፈቱ

1በንጉሡም በዳርዮስ በአራተኛው ዓመት ካሴሉ በሚባል በዘጠነኛው ወር በአራተኛው ቀን የእግዚአብሔር ቃል ወደ ዘካርያስ መጣ።

2የቤቴልም ሰዎች ሳራሳርንና ሬጌሜሌክን ሰዎቻቸውንም በእግዚአብሔር ፊት ይለምኑ ዘንድ፥

3ለሠራዊት ጌታ ለእግዚአብሔር ቤት ካህናት ለነቢያትም፦ “ባለፉት ዓመታት እንዳደረግሁት በአምስተኛው ወር መለየትና ማልቀስ ይገባኛልን?” ብለው ይናገሩ ዘንድ ልኮአቸው ነበር።

4የሠራዊትም ጌታ የእግዚአብሔር ቃል ወደ እኔ እንዲህ ሲል መጣ፦

5“ለምድሩ ሕዝብ ሁሉ ለካህናትም እንዲህ ብለህ ተናገራቸው፦ ‘በዚህ በሰባው ዓመት በአምስተኛውና በሰባተኛው ወር በጾማችሁና ባለቀሳችሁ ጊዜ፥ በውኑ ለእኔ ጾም ጾማችሁልኝ?

6በምትበሉበትና በምትጠጡበትስ ጊዜ፥ ለራሳችሁ የምትበሉና የምትጠጡ አይደላችሁምን?

7ኢየሩሳሌምና በዙሪያዋ ያሉ ከተሞች ገና ሰዎች ባሉባቸው ጊዜ፥ በምቾትም ተቀምጠው ሳሉ፥ ደቡቡና ቈላውም ሰዎች ባሉባቸው ጊዜ፥ እግዚአብሔር በቀደሙት ነቢያት እጅ የተናገረውን ቃል መስማት አይገባችሁምን?’ ”

8የእግዚአብሔርም ቃል ወደ ዘካርያስ እንዲህ ሲል መጣ፦

9“የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ብሎ ተናግሮአል፦ ‘እውነተኛውን ፍርድ ፍረዱ፤ ቸርነትንና ምሕረትን ሁላችሁ ለወንድሞቻችሁ አድርጉ፤

10መበለቲቱንና ድሀ አደጉን፥ መጻተኛውንና ችግረኛውን አትበድሉ፤ ከእናንተም ማንም በወንድሙ ላይ ክፉውን ነገር በልቡ አያስብ።’

11“እነርሱ ግን ደንደሳቸውን አዞሩ እንጂ መስማትን እምቢ አሉ፤ እንዳይሰሙም ጆሮአቸውን አደነቈሩ።

12የሠራዊትም ጌታ እግዚአብሔር በቀደሙት ነቢያት እጅ በመንፈሱ የላከውን ሕጉንና ቃሉን እንዳይሰሙ ልባቸውን እንደ አልማዝ አጠነከሩ፤ ስለዚህ ከሠራዊት ጌታ ከእግዚአብሔር ዘንድ ታላቅ ቍጣ መጣ።

13እኔ በጠራሁ ጊዜ እነርሱ እንዳልሰሙኝ፥ እንዲሁ እነርሱ በሚጠሩበት ጊዜ እኔ አልሰማም፥ ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር፤

14ወደማያውቁአቸውም አሕዛብ ሁሉ በዐውሎ ነፋስ በተንኋቸው። እንዲሁ ከእነርሱ በኋላ ምድሪቱ ባድማ ሆናለች፥ የሚተላለፍባትና የሚመላለስባትም አልነበረም፤ ያማረችውንም ምድር ባድማ አደረጉአት።”

ማብራሪያ

7:1-7 ጥርጣሬ በሚያጭሩ ጉዳዮች የእግዚአብሔርን ፈቃድ በእውነት ማወቅ ከፈለግን፣ ቃሉንና አገልጋዮቹን ብቻ ማማከር የለብንም፤ ነገር ግን በብርቱ ጸሎት ምሪቱን መፈለግ አለብን። የእግዚአብሔርን አሳብ ማወቅ የሚፈልጉ ሰዎች የእግዚአብሔርን አገልጋዮች ማማከር አለባቸው፤ ጥርጣሬ በሚያጭሩ ጉዳዮችም፣ ቅዱሳት መጻሕፍትን መመርመር ልዩ ሥራቸው የሆኑትን ሰዎች ምክር መጠየቅ አለባቸው። ከተማይቱና ቤተ መቅደሱ ሊጠናቀቁ እንደሆኑ በማየታቸው፣ አይሁዶች ጾማቸውን መቀጠል ይገባቸዋል ወይ ብለው ጥያቄ ያነሱ ይመስሉ ነበር። ለጥያቄያቸው የመጀመሪያው መልስ ስለ ግብዝነት የሰላ ተግሣጽ ነበር። እነዚህ ጾሞች በተሻለ መንገድና ለተሻለ ዓላማ ካልተጠበቁ በስተቀር በእግዚአብሔር ዘንድ ተቀባይነት አልነበራቸውም ነበር። የግዴታው ቅርፅ ነበረ፣ ነገር ግን ሕይወት፣ ነፍስ ወይም ኃይል አልነበረበትም።

ሙሉ ማብራሪያውን ያንብቡ ድምፅ፣ ሙሉ ማብራሪያ እና ከመስመር ውጭ ንባብ

ትርጉሞች8 · 6

ENGNIV In the fourth year of King Darius, the word of the Lord came to Zechariah on the fourth day of the ninth month, the mon… English BCV ዳርዮስ ምስ ነገሰ ኣብ ራብዓይ ዓመቱ፥ ካሴሉ ብዝበሃል ታሽዓይ ወርሒ፥ ብራብዐይቲ መዓልቲ ኸምዙይ ዝብል ቃል እግዚኣብሄር ናብ ዘካርያስ መፀ። ትግርኛ GAZBIB Daariyos mo'ee waggaa afuraffaatti, waggicha keessaa ji'a salgaffaa isa “Kisluu” jedhamutti, ji'icha keessaa guyyaa afu… Afaan Oromoo BCV GIZ ወእምዝ በራብዕ ዓመተ መንግሥቱ ለዳርዮስ ንጉሥ ኮነ ቃለ እግዚአብሔር ኀበ ዘካርያስ አመ ረቡዑ ለሠርቀ ታስዕ ወርኅ ወወርኁ ወርኅ ካሴል። giz GAZGAZ Daariyos mo'ee waggaa afuraffaatti, waggicha keessaa ji'a salgaffaa isa “Kisluu” jedhamutti, ji'icha keessaa guyyaa afu… Afaan Oromoo BCV aksum ዳርዮስ ምስ ነገሰ ኣብ ራብዓይ ዓመቱ፥ ካሴሉ ብዝበሃል ታሽዓይ ወርሒ፥ ብራብዐይቲ መዓልቲ ኸምዙይ ዝብል ቃል እግዚኣብሄር ናብ ዘካርያስ መፀ። ትግርኛ AMHNIV ዳርዮስ በነገሠ በአራተኛው ዓመት፣ ካሴሉ በተባለው በዘጠነኛው ወር፣ በአራተኛው ቀን የእግዚአብሔር ቃል ወደ ዘካርያስ እንዲህ ሲል መጣ፤ አማርኛ SWAHSUV Ikawa katika mwaka wa nne wa mfalme Dario, neno la Bwana lilimjia Zekaria, siku ya nne ya mwezi wa kenda, yaani, Kisleu. Kiswahili