ትንቢተ ዘካርያስ 4

AMHNIVአማርኛ14 ጥቅሶች2:19 አዳምጥ
አዳምጥ 2:19 · መደበኛ · አስደናቂ በBiblight ይክፈቱ

1ከእኔ ጋር ይነጋገር የነበረው መልአክም ተመልሶ፣ አንድ ሰው ከእንቅልፉ እንደሚነቃ አነቃኝ፤

2እርሱም፣ “ምን ታያለህ?” አለኝ። እኔም እንዲህ አልሁ፤ “እነሆ፤ በዐናቱ ላይ የዘይት ማሰሮ ያለበት ሁለንተናው ወርቅ የሆነ መቅረዝ አየሁ፤ በመቅረዙም ላይ ሰባት ቧንቧዎች ያሏቸው ሰባት መብራቶች ነበሩ።

3ደግሞም አንዱ ከዘይቱ ማሰሮ በስተ ቀኝ፣ ሌላውም በስተ ግራ የሆኑ ሁለት የወይራ ዛፎች አሉ።”

4ያነጋግረኝ የነበረውንም መልአክ፣ “ጌታዬ ሆይ፤ እነዚህ ምንድን ናቸው” አልሁት።

5እርሱም፣ “ምን እንደሆኑ አታውቅምን?” አለኝ። እኔም፣ “ጌታዬ ሆይ፤ አላውቅም” አልሁት።

6ከዚያም እንዲህ አለኝ፤ “ለዘሩባቤል የተላከው የእግዚአብሔር ቃል ይህ ነው፤ ‘በመንፈሴ እንጂ በኀይልና በብርታት አይደለም’ ይላል እግዚአብሔር ጸባኦት።

7“ታላቅ ተራራ ሆይ፤ አንተ ምንድን ነህ? በዘሩባቤል ፊት ደልዳላ ሜዳ ትሆናለህ፤ ሰዎች፣ ‘ሞገስ ይሁንለት! ሞገስ ይሁንለት!’ ብለው እየጮኹ፣ እርሱ መደምደሚያውን ድንጋይ ያወጣል።”

8ደግሞም የእግዚአብሔር ቃል ወደ እኔ እንዲህ ሲል መጣ፤

9“የዘሩባቤል እጆች የዚህን ቤተ መቅደስ መሠረት ጣሉ፤ የሚፈጽሙትም የእርሱ እጆች ናቸው። ከዚያም እግዚአብሔር ጸባኦት እኔን ወደ እናንተ እንደ ላከኝ ታውቃላችሁ።

10“የጥቂቱን ነገር ቀን የናቀ ማን ነው? ሰዎች በዘሩባቤል እጅ ቱንቢውን ሲያዩ ይደሰታሉ። “እነዚህ ሰባቱ በምድር ሁሉ የሚዘዋወሩ የእግዚአብሔር ዐይኖች ናቸው።”

11ከዚያም መልአኩን፣ “ከመቅረዙ በስተ ቀኝና በስተ ግራ ያሉት እነዚህ ሁለት የወይራ ዛፎች ምንድን ናቸው?” አልሁት።

12እንደ ገናም፣ “በሁለቱ የወርቅ ቧንቧዎች አጠገብ የወርቅ ዘይት የሚያፈሱት እነዚህ ሁለት የወይራ ቅርንጫፎች ምንድን ናቸው?” አልሁት።

13እርሱም፣ “ምን እንደሆኑ አታውቅምን?” አለኝ። እኔም፣ “ጌታዬ ሆይ፤ አላውቅም” አልሁት።

14እርሱም፣ “እነዚህ ሁለቱ የምድርን ሁሉ ጌታ ለማገልገል የተቀቡ ናቸው” አለኝ።

ማብራሪያ

፬፡፩-፯ የነቢዩ መንፈስ ፈቃደኛ ነበር፤ ሥጋ ግን ደካማ ነበረ። እግዚአብሔር በሚናገረን ጊዜ ሁሉ እንድያነቃን እንለምነው ዘንድ ይገባናል፤ ከዚያም እኛ ራሳችንን ማንቃት ይኖርብናል። ቤተክርስቲያን ይህን ጨለማ ዓለም ለማብራት፣ እንዲሁም የመለኮታዊውን መገለጥ ብርሃን ለማቅረብ የተተከለች የወርቅ መቅረዝ ወይም መብራት መያዣ ናት። ከመቅረዙ በሁለቱም ወገን ሁለት የወይራ ዛፎች ታይተዋል፤ ከእነርሱም ዘይት ያለማቋረጥ ወደ ኩባያው ይፈስስ ነበር።

እግዚአብሔር የጸጋውን ዓላማ ስለ ቤተክርስቲያኑ፣ ከሰው ጥበብ ወይም ከሰው ጉልበት ውጭ ሙሉ በሙሉ ይፈጽማል። አንዳንድ ጊዜ መሳሪያዎቹን ቢጠቀምም፣ እርሱ ግን አያስፈልጉትም። ይህ የቤተክርስቲያንን አገልጋዮችና አባላት ለማብራትና ለመቀደስ የሚውለውን የመለኮታዊ ጸጋ ብዛት ይወክል ነበር፤ ይህም በምንም የሰው ኃይል ሊገኝ ወይም ሊከለከል አይችልም።

ራእዩ የመቅደሱ ግንባታ መልካም ሥራ በስኬት እንደሚጠናቀቅ ያረጋግጥልናል። ችግሩ እንደ ታላቅ ተራራ ተመስሎ ቀርቧል። ነገር ግን ችግሮች ሁሉ ይጠፋሉ፤ ተቃውሞዎችም ሁሉ ይወገዳሉ። እምነት ተራሮችን ያንቀሳቅሳል፣ ሜዳም ያደርጋቸዋል። ክርስቶስ ዘሩባቤል ነው፤ የተራራ ያህል የሆኑ ችግሮች ሥራውን ይጋረጡት ነበር፤ ነገር ግን ለእርሱ የሚከብደው የለም። ከእግዚአብሔር ጸጋ የሚመጣው ነገር ሁሉ፣ በእምነት ወደ እግዚአብሔር ጸጋ ሊሰጥ ይችላል፤ እርሱ የገዛ እጆቹን ሥራ አይተውምና።

ሙሉ ማብራሪያውን ያንብቡ ድምፅ፣ ሙሉ ማብራሪያ እና ከመስመር ውጭ ንባብ

ትርጉሞች8 · 6