ትንቢተ ዘካርያስ 11

AMHEVGአማርኛ17 ጥቅሶች3:02 አዳምጥ
አዳምጥ 3:02 · መደበኛ · አስደናቂ በBiblight ይክፈቱ

1ሊባኖስ ሆይ፥ ደጆችህን ክፈት፥ እሳትም ዝግባዎችህን ትብላ።

2የጥድ ዛፍ ሆይ፥ ዝግባ ወድቆአልና፥ ከበርቴዎችም ጠፍተዋልና ዋይ በል፤ እናንተም የባሳን ዛፎች ሆይ፥ ጽኑው ጫካ ተቈርጦአልና ዋይ በሉ።

3የእረኞች ክብር ተዋርዶአልና የዋይታቸው ድምፅ ተሰምቶአል፤ የዮርዳኖስ ትዕቢት ተዋርዶአልና የአንበሶች ግሣት ድምፅ ተሰምቶአል።

4አምላኬ እግዚአብሔር እንዲህ ብሎአል፦ “ለእርድ የሚሆኑትን በጎች ጠብቅ።

5የገዙአቸው ያርዱአቸዋል፥ ራሳቸውንም እንደ በደለኞች አድርገው አይቈጥሩም፤ የሸጡአቸውም፦ ባለ ጠጋ ሆነናልና እግዚአብሔር ይመስገን፡ ይላሉ፤ እረኞቻቸውም አይራሩላቸውም።

6ከእንግዲህ ወዲህ በምድር ላይ ለሚኖሩ አልራራም፥” ይላል እግዚአብሔር፤ “እነሆም፥ ሰውን ሁሉ በባልንጀራውና በንጉሡ እጅ አሳልፌ እሰጣለሁ፤ ምድሪቱንም ይመታሉ፥ ከእጃቸውም አላድናቸውም።”

7እኔም ለእርድ የሚሆኑትን በጎች፥ የመንጋውን ችግረኞች ጠበቅሁ። ሁለት በትሮችንም ወሰድሁ፤ የአንዲቱን ስም ውበት የሁለተኛይቱንም ስም ማሰሪያ ብዬ ጠራሁ፤ መንጋውንም ጠበቅሁ።

8በአንድ ወርም ሦስቱን እረኞች አጠፋሁ፤ ነፍሴም ተሰቀቀቻቸው፥ ነፍሳቸውም ደግሞ እኔን ጠላች።

9እኔም፦ “እናንተን አልጠብቅም፤ የሚሞተው ይሙት፥ የሚጠፋውም ይጥፋ፤ የቀረውም እያንዳንዱ የባልንጀራውን ሥጋ ይብላ፡” አልሁ።

10እኔም ከሕዝቦች ሁሉ ጋር የገባሁትን ቃል ኪዳኔን አፈርስ ዘንድ ውበት የተባለችውን በትሬን ወስጄ ቈረጥሁ።

11በዚያም ቀን ተሰበረች፤ እንዲሁም እኔን የተመለከቱ የመንጋው ችግረኞች የእግዚአብሔር ቃል እንደ ነበረ አወቁ።

12እኔም፦ “ደስ ብሎአችሁ እንደ ሆነ ዋጋዬን ስጡኝ፤ ያለዚያ ግን ተዉት፡” አልሁ። እነርሱም ለዋጋዬ ሠላሳ ብር መዘኑ።

13እግዚአብሔርም፦ “የተስማሙበትን የከበረውን ዋጋዬን በግምጃ ቤቱ ውስጥ አኑረው፡” አለኝ። እኔም ሠላሳውን ብር ወስጄ በእግዚአብሔር ቤት ባለው በግምጃ ቤቱ ውስጥ አኖርሁት።

14በይሁዳና በእስራኤል መካከል ያለውንም ወንድማማችነት እሰብር ዘንድ ማሰሪያ የተባለችውን ሁለተኛይቱን በትሬን ቈረጥሁ።

15እግዚአብሔርም እንዲህ አለኝ፦ “ዳግመኛም የሰነፍን እረኛ ዕቃ ውሰድ።

16እነሆ፥ በአገሩ ውስጥ እረኛ አስነሣለሁ፤ እርሱም የጠፋውን አያስብም፥ የባዘነውን አይፈልግም፥ የተሰበረውን አይጠግንም፤ የዳነውንም አይቀልብም፥ ነገር ግን የሰባውን ሥጋ ይበላል፥ ሰኰናውንም ይቀለጣጥማል።

17መንጋውን ለሚተው ለምናምንቴ እረኛ ወዮለት! ሰይፍ በክንዱና በቀኝ ዓይኑ ላይ ይሆናል፤ ክንዱም አጥብቃ ትደርቃለች፥ ቀኝ ዓይኑም ፈጽሞ ትጨልማለች።”

ማብራሪያ

11:1-3 የኢየሩሳሌም፣ የአይሁድ ቤተ ክርስቲያንና ሕዝብ ጥፋት በምሳሌያዊ አገላለጾች የተነገረ ሲሆን፣ ጌታችን ኢየሱስም ጊዜው ሲቃረብ ይህን በግልጽና በእርግጠኝነት ትንቢት ተናግሮ ነበር። ዝግባዎቹ ከወደቁ፣ ጥድ ዛፎች እንዴት ሊቆሙ ይችላሉ? ጥበበኞችና መልካሞች ወደ ኃጢአት መውደቃቸው፣ እንዲሁም ባለጠጎችና ታላላቆች ወደ ችግር መውደቃቸው፣ በሁሉም መንገድ ከእነርሱ በታች ላሉት ታላቅ ማስጠንቀቂያ ይሆናል። እረኞች ሊሆኑ የሚገባቸው ሰዎች እንደ አንበሳ ደቦል ሲሆኑ፣ ለሕዝብ በጣም የሚያሳዝን ሁኔታ ነው። የዮርዳኖስ ወንዝ ኩራት የዳርቻዎቹ ጥቅጥቅ ያሉ ቁጥቋጦዎች ነበሩ፤ ወንዙም ዳርቻዎቹን ሲያጥለቀልቅ፣ አንበሶች ከእነርሱ ውስጥ እያገሱ ወጡ። እንዲሁ የኢየሩሳሌም ጥፋት ሌሎች አብያተ ክርስቲያናትን ሊያስጠነቅቅ ይችላል።

11:4-14 ክርስቶስ በአስከፊ ሁኔታ የረከሱና የጠመሙ ለነበሩት የአይሁድ ቤተ ክርስቲያንና ሕዝብ ለፍርድ ወደዚህ ዓለም መጣ። ክፉ የሚያደርጉና ራሳቸውን በእርሱ የሚያጸድቁ (ትክክል አድርገው የሚቆጥሩ) ሁሉ አእምሯቸው በአሰቃቂ ሁኔታ የጨለመባቸው ናቸው፤ እግዚአብሔር ግን ራሳቸውን ንጹሐን አድርገው የሚቆጥሩትን ንጹሐን አድርጎ አይቆጥራቸውም። ሕገ ወጥ በሆነ መንገድ ሀብት ለማግኘት በረከትን ለመለመን ወይንም በእነርሱ ውስጥ ለተገኘው ስኬት ምስጋና ለማቅረብ እንዴት ወደ እግዚአብሔር ልንሄድ እንችላለን? በመካከላቸው የሃይማኖት አጠቃላይ መዳከም ነበር፤ እነርሱም አላስተዋሉትም።

ሙሉ ማብራሪያውን ያንብቡ ድምፅ፣ ሙሉ ማብራሪያ እና ከመስመር ውጭ ንባብ

ትርጉሞች8 · 6